9.12.19

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ሀላፊ አቶ ጃዋር መሐመድ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ከ LT-TV ጋር ባድረገው ቆይታ “ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ታሪክ የለንም ፣ ያለን የተናጠል ታሪክና  የጋራ አገር ነው “ ሲል የግል አስተያየቱን አንፀባርቀዋል ። በእኔ የኢትዮጵያ ታሪክ አረዳድ የኢትዮጵያ ህዝብ ከመጠን ያለፈ የጋራ ታሪክ ያለው ህዝብ ነው ። የጋራ ታሪክ ምን ማለት ነው ? ። የጋራ መግባቢያ ገንዘብ መጠቀም የጋራ ታሪክ አይደለም ወይ ? ፣ የቋንቋ መግባባት ፣ የባህል ውርርስ የጋራ ታሪክ አይደለም ወይ ? ፣ በጋራ አምርቶ በጋራ መጠቀም ታሪክ  ካልሆነ ምን ሊባል ይችላል ? ። የዘርና የሐይማኖት ገደብ ሳያግደው በጋራ መኖር ታሪክ አይደለም ወይ ? ፣ በአንድ መንግስትና ህገ መንግስት መተዳደር የጋራ ታሪክ ካልሆነ ምን ልንለው ይሆናል ? ።በተደጋጋሚ የውጭ ጣልቃ ገብነት በጋራ የመከተ ህዝብ የጋራ ታሪክ የለውም ከተባለ ለእውነት ተገቢው ሥፍራ ካለመሰጠት የመነጨ ይመስለኛል ። በተፈጥሮ ሆነ ሰው ሰራሽ ችግሮች የህዝብ የጋራ ታሪክ መገለጫ ተደርጎ ይታያሉ ።የአቶ ጃዋር መሐመድ የዘረኝነት ትርጉም የተረዳበት መንገድ የተዛባ ነው ። ተለዋዋጭ እና በእውነታ ላይ ያልተመሠረተ አሰተያየት በመሰጠት አቶ ጃዋር መሐመድን የሚያክል አክቲቪስት እስከዛሬ አላጋጠመኝም ። ዘረኝነት ከዘር ማንነት ጋር ተያያዥነት የለውም ። ዘረኝነት አመለካከት ነው ። ከእኔ ዘር በቀር ማለት ንጹሕ ዘረኝነት ነው ። ሁሉም የእኔ በእኔ ማለት ደረቅ ዘረኝነት ነው ። ሌላው የአቶ ጃዋር አሰተያየት “ በኢትዮጵያ የጎሳ ዘረኝነት የለም ፣ ያለው የብሔር ጥቅም ግጭት ነው “ የሚል አሰተያየት ነበር ። በእኔ እይታ በኢትዮጵያ የብሔር ጥቅም ግጭት አልነበረም ፣ አሁንም የለም ።የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም የነሳው ጥገኛ ዘረኝነት ነው ። ዘረኝነት ለመፍጠር የግድ በመልክ ቀለም መለያየት የለብንም ። ዘረኝነት ከሰው ዘር አይነት ጋር ምንም የሚያገናኘው ጉዳይ የለም ። ዘረኝነት የአስተሳሰብ ብልፅግና እጥረት አልያም ችግር ነው ። ዘረኛ ለመሆን ነጭ ሰው አልያም ጥቁር ሰው መሆንን አይጠይቅም ። ዘረኛ ለመሆን አሰተሳሰብ ብቻ በቂ ምክንያት ነው ። ዘረኛ አሰተሳሰብ ምን ማለት ነው ? ። አንዱ መነሻ ምክንያት የፖለቲካ ስልጣን (የመንግስት ) አወቃቀር ችግር ነው ። ለህግ ልዕልና የማይገዛ የፖለቲካ ሥርአት የመጨረሻ ግቡ አምባገነን እንዲሁም ከፍፍይ መሆን ነው ። በዘር ፖለቲካ መደራጀት የመጨረሻ ግቡ ልማትና ብልጽግና ሳይሆን ዘረኝነት ማስፋፋት ነው ። ዘረኝነት የተለየ ፍላጎት እና ጥቅም መነሻ ያደረገ ፣ የዘር መድሎ አልያም ጭቆና በአንድ አልያም ከአንድ በላይ የዘር ሐረግ ባላቸው ነገዶች ወይም ብሔረሰቦች ላይ የባህልና የአስተዳደር ጫና መፍጠር ፣ ፍትሐዊነት የጎደለው የኢኮኖሚ አሻጥር መፈፀም አልያም እንዲፈፀም ፖለቲካዊና ስልታዊ ጫና ማድረግ ፣ የጎሳ ቋንቋ አፈና ማድረግ ፣ የዜጎች የዜግነት መብቶችና አለም አቀፍ የሰብአዊና መብት ድንጋጌዎች መጣሰ እንዲሁም ዜጎች የአስተዳደርና የስልጣን ተሳታፊ እንዳይሆኑ መከልከል ላይ ያተኮረ ፖለቲካ ሥርአት ውጤት ነው ። በኢትዮጵያ ዘረኝነት ሆነ ዘረኛ አመለካከት እና አሰተሳሰብ የለም ብሎ መደምደም የሚያስችል እውነታ የለም ። በዘር ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ ሥርአት ባለበት አገር ዘረኝነት የለም ብሎ መናገር ሀላፊነት የጎደለው ሰው መሆን አለበት የሚል እምነት አለኝ ። አማራ በዘሩ ከደቡብ ፣ ከቤንሻንጉል እንዲሁም ከኦሮሚያ ተፈናቅለዋል ። የትግራይ ህዝብ በዘሩ ምክንያት ከጎንደርና ወልቃይት ተፈናቅለዋል ። የጌዴኦ ማህበረሰብ በዘሩ ምክንያት ከጎጂተፈናቅለዋል ። የኦሮሞ ህዝብ ከሞያሌ እንዲሁም ከሶማሌ ክልል በዘሩ ምክንያት ተፈናቅለዋል። ታድያ ይህ የዘረኝነት ተግባር ካልሆነ ምን ሊባል ይችላል ? ። በአጠቃላይ ላለፉት 20 አመታት ከ 3.5 ሚሊዮን ህዝብ የተፈናቀለው በተፈጥሮ አደጋ ወይም በድርቅ አልነበረም ። በጦርነት አልያም በሰፈራም አልነበረም ። ዘር ተኮር የግድያ ጥቃት ሲፈፀም መነሻው የዘር ጥላቻና ዘረኝነት እንጂ የጥቅም ግጭት አልነበረም ።ለተፈናቀሉት ዜጎች ዋና ምክንያት ዘረኝነትና ጥላቻ ነበር ። ይህ የማይካድ እውነታ ነው ። ዘረኝነት ለማሳየት በቆዳ ቀለም ካየነው ስህተት ነው ። ምክንያቱም ዘረኝነት የቆዳ ቀለም የለውም ። ዘረኝነት የአስተሳሰብና አመለካከት ከባድ በሽታ ነው ። አቶ ጃዋር መሐመድ በሌላ አስተያየቱ ላይ ደግሞ ይህንን አሰተያየት አስፍረዋል “ ከጠባብነት ወደ ዘረኝነት እየተደረገ ያለ ጉዞ ሆን ተብሎ የኦሮሞ ህዝብ ለማሸማቀቅ ነው “ የሚል ነው ። ይህ አሰተያየት በራሱ ዘረኝነት ነው ። የኦሮሞ ህዝብ የሚያሸማቅቅ ምን ጉዳይ ተገኘ ? ። ይህ አሰተያየት በዘረኝነት አመለካከት ያበዱ ደካሞች የሚሰጡት አሰተያየት ነው ። የኦሮሞ ህዝብ በዜግነቱ የሚኮራና የሚወከል ህዝብ በአክራሪ እንዲሁም ዘረኛ የኦሮሞ አክቲቪስቶች የሚጠራ ህዝብ አይደለም ። የኦሮሞ ህዝብ የዳበረ የአብሮነት ባህል ባለቤት ህዝብ እንጂ በሜጫና ገጀራ የሚመካ  ህዝብ አይደለም ። የኦሮሞ ህዝብ አቃፊ እንጂ አዲስ አበባ ከተማ የኦሮሞ ነው የሚል ህዝብ አይደለም ። በኦሮሚያ ክልል መኖሪያ ቤት የሚገነቡ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ቤት እንዲሰሩ አልፈቅድም የሚል ህዝብ አይደለም ። አቶ ጃዋር መሐመድ ወጣት ቢሆንም የበሰለና የለውጥ ሀሳብ አመንጪነት ላይ በርካታ እጥረት ይታይበታል ።ከስሜታዊነት ፣ ጥላቻ ፣ ዘረኝነት ፤ እንዲሁም ራሰን አግዝፎ የማየት ጉዳይ በስፋት ይስተዋልበታል ። ለመጪው ትውልድ የሚሆን የዳበረ ሀሳብ ለማፍለቅ ከመስራት ይልቅ ባላፈው የታሪክ ግድፈቶች ላይ ማተኮር ለነገ የሚሆን ሀሳብ አይሆንም ። በኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚ የተፈጠሩ በርካታ የታሪክ ስህተቶች አሉ ። ነገር ግን የታሪክ ስህተቶች ላለመድገም መሰራት እንጂ ስህተቶች ላይ መዘፍዘፍ ሆነ መወቃቀስ የሚያመጣው አንዳች ጥቅም የለም ። የጋራ ታሪክ ባይኖር ኖሮ የታሪክ ስህተቶች አይኖሩም ነበር የአክሱም ታሪክ የአክሱማውያን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ታሪክ ነው ። የገዳ ማህበራዊ ሥርአት የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ታሪክ ነው ። የአባይ ግድብ የቤንሻንጉል ክልል ህዝብ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ስያሜ ነው ። የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ስኬት ነው ።  በመሆኑም የኦሮሞ ህዝብ ነጥሎ የሚያገል ፣ የሚበድል ፣ የሚጠላ ካለ ለኦሮሞ ህዝብ ጥቅም የሚያስቡ የሀሳብ ግዞተኞችብቻ ይሆናሉ የሚል አመለካከት አለኝ ። ለመሆኑ የኦሮሞ ህዝብ ጥቅም ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝቦች የተለየ ነው ? ። የኦሮሞ ህዝብ ህጋዊ ወኪል ማን ነው ? ጃዋር መሐመድ የኦሮሞ ህዝብ ውክልና ወረቀት አለው ? ።

አቶ ጃዋር መሐመድ የኢትዮጵያ ህዝብ የኢህአዴግ ሥርአት እንዲቃወም የማሰብያ ማሽን የገጠምኩለትእኔ ነኝ ሲል በተደጋጋሚ ይደመጣል ። ሲቀጥልም የኦሮሞ ህዝብ ሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ መሪዎች ክቡር የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ኦቦ ለማ መገርሳ ፣ የአሁኑ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ እና እኔ ነን ይለናል ። በእኔ አረዳድ የኦሮሞ ህዝብ መሪ የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲ (OPD) መሆኑ ብቻ ነው የማውቀው ። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መሆናቸው አውቃለሁ ። ነገር ግን  አቶ ጃዋር መሐመድ ራሱ የሾመ ካልሆነ በቀር የኦሮሞ ህዝብ መሪ መሆኑን በጋህድ አላውቅም ። ነገር ግን አቶ ጃዋር መሐመድ የብዙሃን መገናኛ መሥራች እና ባለቤት መሆኑን በበረራ እሰማለሁ።  ኦቦ ለማ መገርሳም የኢትዮጵያ መከላከያ ሀላፊ ሆኖ አገራቸው እና ህዝባቸው በማገልገል ላይ መሆናቸው አውቃለሁ ። ለአቶ ጃዋር መሐመድ የሚያሳስበው የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎት እና ጥቅም ሳይሆን የጀመረው የንግድ ጥቅም ማስቀጠል ነው ። አቶ ጃዋር መሐመድ በተመሳሳይ ጊዜ ሁለት ምላጭ የሚጠቀም አወናባጅ እና አጭበርባሪ ሰው ነው ። በህዝብ የሚቀልድ የዘረኝነት ዋና ምንጭ ሰው ነው ። አገር እና ህዝብ ለተሻለ እድገት እና ብልፅግና ፣ ለሰላም እና መረጋጋት ፣ ለአብሮነት እና መከባበር የሚበቃ በኢትዮጵያ ህዝብ ተቀባይነት ያገኘ ብስል ሀሳብ የለውም ። አገር በህግ ልዕልና እንጂ በጎበዝ አለቆች አትመራም ። በእርግጥ የኦሮሞ ወጣቶች ሥራ አጥነት እና ብልሹ የመንግስት አሰተዳደር በመቃወም ታሪክ የሠሩ ጀግኖች ናቸው ። ሆኖም የኦሮሞ ወጣቶች የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆች ናቸው ። የፈፀሙት ተግባርም ከኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎት ውጭ አልነበረም ። መንግስት መቃወም የማህበረሰብ ባህሪ እንዲሁም ተገቢ ነው ። ነገር ግን በስሜት ሳይሆን በምክንያት መሆን አለበት ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሆኑ ኦቦ ለማ መገርሳ ደግሞ ከአቶ ጃዋር የማሰብያ ማሸን የሚያስፈልጋቸው አይመስለኝም ። በእኔ አረዳድ አቶ ጃዋር መሐመድ የጥፋት ሀሳብ አፍላቂ እንጂ ለአገር ግንባታ ሆነ ለማህበረሰብ ትስስር ማዳበሪያ የሚሆን ሀሳብ ሲያፈልቅ የታዘብኩት ጊዜ በውል አላስታውስም ። በኢትዮጵያ የሚካሄደው ማንኛውም ለውጥ እኔ ካልመረመርኩት ውድቅ አልያም አይታሰብም የሚል አመለካከት የተጠናወተው አቶ ጃዋር መሐመድ እንደ ወጥ ቤት ሠራተኛ ሁሉም ልቅመሰ ባይነት ሰሜት ያለው ሰው መሆኑ እጅግ ግብዝ ሰው እንደሆነ ለመገንዘብ ችያለሁ ። የፖለቲካ ፣ የማህበራዊ ፣ የፍትህ ፣ የኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ በአቶ ጃዋር መሐመድ ካልተፈተሸ ተግባራዊ አይሆንም የሚል የሌብነት ሥራ ከየት መጣ ነው ? ። ኢትዮጵያ በጃዋር መሐመድ አመራር ትመራ ያለሰ ማን ነው ? ። አቶ ጃዋር መሐመድ በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ፍላጎቱ አይደለም ። የኢትዮጵያ ሰላም  ፣ ልማት ፣ እና ብልጽግና የአቶ ጃዋር መሐመድ ተልዕኮ አይደሉም ። አቶ ጃዋር መሐመድ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈይድ ሰው ሳይሆን ድብቅ የአረቦች ለማሳካት የሚንቀሳቀስ አደገኛ ሰው ነው ። በኢትዮጵያ የእምነት ግጭት እንዲነሳ የሚሻ ሰው ብቻ ሳይሆን ራሱ ግጭት ቀስቃሽ ነው ። በመሆኑም የአቶ ጃዋር መሐመድ እንቅስቃሴ በአግባቡ መጤን ይኖርበታል የሚል የፀና እምነት አለኝ ። ከሰላም መደፍረሰና ግጭት አቶ ጃዋር መሐመድ አትራፊ ነው ። ተልዕኮውም እሱ ነው ። የኢትዮጵያ ቀጣይ አብይ አደጋ ድህነት ሳይሆን የሐይማኖት ግጭት ይሆናል ። ለዚህ ተግባር የተሰለፉ እንደ አቶ ጃዋር መሐመድ የመሳሰሉ አፈቀላጤ የዘመኑ ጉልበተኞች ቀጣይ ተግባራቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ቤተ እምነት እንዳትረጋጋ ማድረግ ነው ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ቤተክርስቲያን በራሷ ውስጣዊ ችግር ምክንያት ፈተና ላይ ናት ። አንዱ የቤተክርስቲያኗ ችግር የንጽሕና ችግር ነው ። መንፈሳዊ ተግባር በቅጡ ማስተናገድ ችግር ብቻ ሳይሆን የአስተዳደር እንዲሁም የአስተሳሰብ ለውጥ አመክንዮ ያላቸው ግልጽ ችግሮች ያላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ የፖለቲካ ችግር ተጠቂም ጭምር ናት ። የዘር ፖለቲካ ቤተ እምነት ደብር ድረስ ዘልቆ በመግባቱ የእምነቱ ተከታዮች ተከፋፍሎ ከርመዋል ። ቤተክርሰቲያኗ ያላት ሀብት በውል ባይታወቅም በኢትዮጵያ በልማቱ መስክ ያላት ተሳትፎ ዝቅተኛ ነው ። በትምህርት ተደራሽነት ቢሆንም ከቁጥር የሚገባ ተግባር የላትም ። የውጭ የትምህርት እድል አሰጣጥም አጥጋቢ አይደለም ።በአስተሳሰብ ልማትም ቢሆን ቤተክርስቲያኒቱ ገና በርካታ ሥራዎች ይጠብቃል ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ቤተ እምነት የፖለቲካ ተፅዕኖ እንጂ የልማት ተፅዕኖ ታሪክ የላትም ። የራሷን ውድ ህንፃዎች ከመገንባት ውጭ ለትውልድ የሚጠቅም አንድ ቤተመፃህፍት ህንፃ ገንብታ ለትውልድ ያበረከተቹ በረከት የለም ። የአቅም ችግር የሚያጋጥማቸው የእምነቱ ተከታዮች የምታግዝበት የአስተዳደር ስልት የላትም ። ሣላሳ ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ አማራጭ የክርስትና  ( ወንጌላውያን ) እምነት ተከታይ ነው ። ይህ ህዝብ በአንድ ወቀት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የነበረ እንደነበር ይታወቃል ። ችግሩ ማን ምን እምነት ይከተላል አይደለም ።ጉዳዩ የኦርቶዶክስ እምነት እንዳይቀጥል የመግታት አልያም የማዳከም ተግባር መጀመሩ ነው ። የቤተክህነት እና ቤተእምነት ደካማ ውስጣዊ አሰተዳደር መነሻ በማድረግ እምነታዊ ግጭት ለማስነሳት ፣ ለመከፍፈል በአክራሪና ዘረኛ ወገኖች የተግባር ሥራ ተጀምሯል ። ይህ ጉዳይ ጥንቃቄ የሚሻ ጉዳይ ነው ። የእምነት ግጭት እንዳይነሳ ከፍተኛ ሥራ መሠራት አለበት ። ቤተክርስቲያን ያላትን ውስጣዊ አቅም ተጠቅማ የማህበረሰብ ልማት በስፋት ተሳትፎ ማድረግ አለባት ። ራሷም ከውስጥና ከውጭ ጠላት ለመከላከል አቅም ማጎልበት አለባት ። የእምነት መከባበር በመንፈሳዊ ሐይል ሳይሆን በህግ መረጋገጥ ይኖርበታል ። የእምነት ነፃነት የሚፈታተኑ የዘረኝነት እና የአክራሪነት መሰናክሎች መጋፈጥና መመከትና ሐይማኖታዊ ተግባር ነው ። የእምነት ነፃነት በፆም ፀሎት ብቻ ችግሮች መፍታት አይቻልም ። የማህበረሰብ ልማትና አስተምህሮ ያልታከለበት የሐይማኖት ተቋም በርካታ ሰው ሰራሽ ፈተናዎች እንደሚያጋጥም የሚያጠራጥር አይሆንም ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ቤተእምነት የእምነት አገልግሎት አድማስ ለማስፋት በርካታ ውስጣዊ የአሰራር ለውጦች ማከናወን ይጠበቃል ። በተእምነቷ የአገልግሎት ንፅህና እንዲኖራት እጅግ አሰፈላጊ ብቻ ሳይሆን እምነታዊ ግዴታም ጭምር ነው ። ራሱን የኦሮሚያ ቤተክህነት በማለት ከቤተክርስቲያኗ አሰራርና መመሪያ ውጭ የአፍራሽነት ተልዕኮ የጀመረው ዘረኛ የአቶ ጃዋር መሐመድ ቡድን በእምነት ተቋማት ላይ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም ምክር ሳይሆን ህጋዊ የህግ እርምጃ መወሰድ ያሰፈልጋል ። የአረቦች ተልዕኮ ጉዳይ አስፈፃሚ የሆኑ የኢትዮጵያ ዜግነት ሰም ያነገቡ የእምነት ግጭት ቀስቃሾች የኢትዮጵያ ህዝብ በንቃት ክትትል ማድረግ ይኖርበታል ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ቤተእምነት ማዳከም ሳይሆን ማጥፋት የአረቦች የዘወትር ተግባርና ሥራ ነው ። ለዚህ ተግባር የተመለመሉ በአቶ ጃዋር መሐመድ የሚመራ ሚስጥራዊ ቡድን እንዳለ ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት የለበትም ። የእምነት ግጭት ቀስቃሾች የመንግስት ድጋፍ ማግኘት የለባቸውም ። በኦሮሚያ እንዲሁም በደቡብ በመንግሥት ሀላፊነት ላይ ያሉ ግለሰቦች ለእምነት አክራሪዎች እና ዘረኞች ድጋፍ ሆነ ከለላ የሚያደርጉ እንዳሉ ቤተክርስቲያን መረጃ እንዳላት በቅርቡ ለህዝብ ጀሮ ደርሷል ። የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሽግግር ሂደት የሚያደናቅፉ ፣ ቤተእምነት በእሳት የሚያነዱ ፣ የእምነት ነፃነት የሚገድቡ ፣ የእምነት ተቋማት ለማጥፋት በህቡዕ ከውጭ ጠላት ጋር የሚሠራ የእምነት አክራሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ተገቢ ይመስለኛል ። የኦሮሚያ ቤተክህነት ለማቋቋም የተዋቀረ ኮሚቴ በምክር ሳይሆን በህግ መታገድ እና መገለል አለባት ። ሁሉም የእኛ የሚሉ የኦሮሞ ዘረኛ ቡድኖች የሚከተሉት የጥላቻ እና የዘረኝነት ጉዞ ቆም ብሎ ማሰብና ማሰላሰል ይኖርባቸዋል ።
Full Website