ም በኢትዮጵያ የተከሰተ ጉዳይ ያልተገመተና ለማመን የሚያዳግት እንዲሁ አስደንጋጭ ሆኖ በታሪክ ማህደር ሰፍሯል ። እንደ መንግስት አገላለጽ የኢትዮጵያ መከላከያ ጦር ባልደረባ የነበሩ ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ፅጌ የተቀነባበረ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የመግደል ተግባር መፈፀሙ የኢትዮጵያ ህዝብ ያሳዘነ ክሰተት ነው ። የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕስ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮነን ፣ እንዲሁም ከፍተኛ የክልሉ የሥራ አመራር ነበሩ አቶ አዘዝ ዋሴ ፣ እንዲሁም አቶ ምግባሩ ከበደ የግድያ ሰለባ ሆነዋል ። በተመሳሳይ ጊዜና ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ መኖሪያ ቤታቸው እያሉ በጠባቂዎቻቸው አማካይነት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጦር ኢታማጆር ጀነራል ሰዓረ መኮነን እንዲሁም ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ ተገድሏል ። ድርጊቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ያሳዘነ ሆኗል ። በግሌ ለሟች ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን ስመኝ ለሟቾቹ ነብስ ይማራሉ እላለሁ ።
Full Website