መስከረም 19 2012 . .

የቅማንት ህዝብ በማንነቱ ዙርያ ህገመንግስታዊ የመብት ጥያቄ በማንሳት ህጋዊ በሆነ መንገድ እንዲመለስለት ህጋዊ አካሄዶች ተከትሎ በመሄድ ጥያቄዎቹ እያቀረበ እንደነበር ለማንም ግልፅ ነው፡፡ በመሆኑም የአማራ ክልል ምክርቤት እንደ አንድ ህጋዊና ትክክለኛ ጥያቄ ነው ብሎ ህጋዊ እውቅና በመስጠት ጥያቄዎቹን ለመመለስ ጥረት ሲያደርግ እንደነበር ሁሉም ይገነዘበዋል፡፡ በዚህ መሰረት የአማራ ክልል ምክርቤት የቅማንት ብሄረሰብ ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት ልዩ የዞን አስተዳደር እንዲኖረው በመወሰኑ፣ ውሳኔው ተግባራዊ ለማድረግ በሂደት ላይ እንደ ነበር ይታወቃል፡፡

ይህ የአማራ ምክርቤት ውሳኔ እንደ መልካም ጅምር ቢወሰድም፣ የህግ አስፈፃሚው ውሳኔውን አተገባበር ላይ የብሄሩን ጥያቄ በተሟላ መንገድ መመለስ ስላቃተው፣ ጥያቄውን ያቀረቡት የብሄሩ ተወካዮች ለጥያቄያቸው የተሰጠ ምላሽ የተሟላ መፍትሄ እንዳልሆነ በመግለፅ የህዝቡን ጥያቄ ህጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማቅረብ በመወሰን እንቅስቃሴ መቀጠሉም ይታወቃል፡፡ በአማራ የብዙሀን መገናኛ ተቋማት ይገለፅ እንደነበረው፣ ያልተመለሱ ተብለው በቅማንት ህዝብ እየተነሱ ካሉት ጥያቄዎች አንዱ፣ የቅማንት ብሄረሰብ የሚገኝባቸው የተወሰኑ የገጠር ቀበሌዎችም ወደ ቅማንት መካለል ሲገባቸው ገና ያልተካለሉ እንዳሉ፣ ይህም ህጋዊ በሆነ አገባብ ጥያቄ መቅረብ እና መልስ መሰጠት እንዳለበት በክልሉ መንግስት እና በቅማንት ህዝብ ተወካዮች መግባባት ላይ መደረሰም ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ በአማራ ክልል መንግስት ውስጥ ተሰግስገው የገቡ፣ በብርጋዴር ጀነራል አሳምነው የሚመራው የፅንፈኛው አሀዳዊ ስርዓት አፍቃሪ ግለሰቦች፣ ይህን የክልሉ መንግስት እና የቅማንት ብሄር የተደረሰውን መግባባት ወደጎን በመተው፣ የቅማንት ህዝብ ጥያቄ በአፈሙዝ ለመቀልበስ እና በፀረ ህዝብ አካሄድ መልስ ለመስጠት በቅማንት ህዝብ ላይ ጦርነት በማወጅ ከፍተኛ የህዝብ ጭፍጨፋ እንዲካሄድ ኣድርጓል፡፡

ይህ በአማራ ክልል የመንግስት መዋቅር ተሰግስጎ የሚገኘው ፅንፈኛው ሀይል የቅማንትን ህዝብ ብቻ ሳይሆን የጨፈጨፈው የከምሴ ኦሮሞ፣ የአጎራባች ክልል የሆነው የቤንሻንጉል ጉምዝ ህዝብ ጭምር የአማራ ክልል ልዩ ሀይል በማሰማራት ከፍተኛ ጭፍጨፋ እና በደል መፈፀማቸው ይታወቃል፡፡ ይህን ጭፍጨፋ መፈፀሙ በብዙዎች ዘንድ ወገዛ የደረሰበት ሲሆን፤ የፌደራል መንግስትም ይህንን በአማራ ክልል መንግስት የተፈፀመው አሰቃቂ በደል ለማጣራት ከአማራ ክልል የፀጥታ እና የደህንነት ቢሮ እውቅና ውጭ ጉዳይ የሚያጣራ

ይህ ከፌደራል የተላከው አጥኚ ቡድን ዝርዝር የማጣራት ስራውን ማጠናቀቁ የሚታወቅ ሲሆን በማጣራቱ ሂደት የተገኙ ግኝቶች ግን እስከአሁን ለህዝብ ይፋ አልተደረገም፡፡ ነገር ግን ወንጀሉ ፈፃሚዎች ያደረጉትን ወይም የፈፀሙትን ወንጀል በደንብ ያውቃሉና፤ የማጣራቱ ግኝት ምን ይዞ እንደሚመጣ ስለተረዱ፣ ከመቀደማቸው በፊት ለመቅደም የመንግስት ግልበጣ ስውር ዕቅድ በማዘጋጀት የአማራ ክልል ርእሰመስተዳድር ጨምሮ 3 የክልለሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም የአገር መከላከያ ኢታማጆር ሹም ጨምሮ 2 ጀነራሎችን መግደላቸው እና በስተመጨረሻ የዕቅዱ ዋና ፈፃሚ ብ / ጀ አሳምነው ጨምሮ በርካታ ሰዎች በፀጥታ ሀይሉ መገደላቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህ አሳፋረሪ የአመራር ግድያ በስተጀርባ እጃቸው አለባቸው ተብለው የተጠረጠሩ በርካታ ግለሰቦች ታድነው እየታሰሩ ወደ ህግ እየቀረቡ እንዳሉም ይታወቃል፡፡

ይሁን እና በአማራ ክልል የመሸገው ይህ ፅንፈኛ የአሀዳዊ ስርዓት አራማጅ አካል፣ እየፈፀመ ያለው ኢህገመንግስታዊ አካሄድ አደብ እንዲገዛ ባለመደረጉ እና ችግሩ ከስረመሰረተ ለመፍታት እርምጃ ባለመወሰዱ፣ ችግሩ እንደገና አገርሽቶ በቅማንት ብሄረሰብ ላይ ዳግም ጦርነት በማወጅ ህዝቡን በመጨፍጨፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከሁሉ የሚገርመው ደግሞ የብ / ጀ አሳምነው ፅጌ ቦታን የወረሱ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ ብ / ጀ አሳምነው ፅጌ ያሰለጠኑት የክልሉ ልዩ ሀይል በመጠቀም ዳግም የቅማንት ህዝብን መጨፍጨፍ ስራዬ ብለው ተያይዞውታል፡፡

አቶ አገኘሁ ተሻገር በአብዮታዊ ዴሞክራሲ አቋማቸው እና ጥንካሬየቸው በሚያደርጉት ንግግር ይታወቁ ስለነበር በአማራ ክልል የኢህአዴግን አቋም የሆነውን አብዮታዊ ዴሞክራሲ ሲያሰለጥን የነበረውን የአማራ ክልል አመራር አካዳሚ ዳይሬክተር ሆኖው ሲሰሩ እንደነበር እና አሁን ደግሞ የፀጥታ ቢሮ ሀላፊ ሆኖው መሾማቸው የሚታወቅ ነው፡፡ እንደሚታወቀው የአዴፓ ከፍተኛ አመራር ፣ ለሆዳቸው ብቻ የሚኖሩ፣ ህዝባዊ አቋም የሌላቸው፣ ስልጣን ለማግኘት ብሎ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ እምነት ከጳጳሱ በላይ ሆኖ መታየት፣ በአሀዳዊ ስርዓት እምነትም ከጳጳሱ በላይ ሆኖ መታየት ዋነኛው መለያ ባህሪያቸው ነውና እነሆ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ እምነት የተካኑ እየተባሉ ይጠሩ የነበሩት አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ አሁን የፀጥታ ቢሮ ሀላፊ ተብለው ከተሾሙ ቦሀላ አክሮባት በመስራት ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ እምነት ባፈነገጠ አካሄድ ልዩ ሀይል አሰማርተው የቅማንት ህዝብን በገዛ አገሩ እንደ ሁለተኛ ዜጋ በመቁጠር ማሰቃየት ጀመሩ፡፡

የፅንፈኞች እና ፀረ ህዝቦች ነገር ሁሌም ባህርያቸው ህዝብን መናቅ፣ ሁሉም ነገር በሀይል ወይም በአፈሙዝ መፍታት ይቻላል ብለው ስለሚያምኑ፣ እነሆ በአማራ ክልል በቅማን ህዝብ አሰቃቂ ግፍ እያደረሱ ይገኛሉ፡፡ ምን ያክል የህዝብ ንቀት እንዳላቸው የሚያሳየው፣ በአማራ ክልል ሚድያ ቀርበው የሰጡት መግለጫ ነው፡፡ አቶ አገኘሁ እንደተናገሩት የቅማንት ህዝብ ህገመንግስታዊ የመብት ጥያቄ የሶስተኛ ወገን ግፊት እንደሆነ፣ በባጀትም በመሳሪያም የሶስተኛ ወገን ስፖንሰር እንደሆነ፣ በኣጠቃላይ አሁን እየተካሄደ ያለው ጦርነት የስፖንሰር ጦርነት እንደሆነ በአይነ አውጣነት አገላለፅ ገልፀዋል፡፡

የቅማንት ህዝብ የመብት ጥያቄ የሶስተኛ ወገን ስፖንሰር ነው ማለታቸው፣ የህዝቡን ህገመንግስታዊ የመብት ጥያቄ ለማዳፈንና ለመጨፍለቅ በመፈለግ የተሰጠ መግለጫ ነው፡፡ የቅማንት ህዝብ ህገመንግስታዊ ጥያቄ በክልሉ ምክርቤት ህጋዊ እውቅና ሰጥቶ፣ አጥጋቢ ባይሆንም ህጋዊ ምላሽ በመስጠት አንድ እርምጃ ወደፊት መሄዱ ይታወቃል፡፡ የቀረ ያልተመለሰ ጥያቄ ካለም ህጋዊና፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲፈታ በክልሉ መንግስት እና በቅማንት ህዝብ ተወካዮች መግባባት ላይ ተደርሶ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን፤ የብ / ጀ አሳምነው ፅጌ ቦታ የወረሱት አቶ አገኘሁ፣ ቦታ ብቻ ሳይሀሆን አመለካከቱም፣ ተግባራቱም፣ ፀረ ህዝብነቱም በመውረሳቸው የህዝቡን ጥያቄ የስፖንሰር ጥያቄ ነው የሚል ምክንያት በመስጠት ጦርነት አውጀው ህዝብን መጨፍጨፍ ተያይዘውታል፡፡ የቅማንት ህዝብም ባገኙት አጋጣሚ የድረሱልኝ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡

አቶ አገኘሁ፣ የቅማንት ህዝብ እንዴት ሲንቁት ነው በሶስተኛ ወገን እየተዘወረ ነው ያሉት ? አቶ አገኘሁ የቅማንት ህዝብ ብቻ አይደለም የናቁት፣ ወደ ስልጣን ያመጣቸው ወይም የሾማቸው የአማረ ክልል ምክርቤትም ጭምር እንጂ፡፡ ምክንያቱም የቅማንት ህዝብ ጥያቄ፣ ህጋዊና ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ ነው ብሎ መልስ መስጠት የጀመረውን የክልሉ ምክርቤት፣ በአቶ አገኘሁ አባባል የምክርቤቱ መልስ ለህዝቡ ጥያቄ ሳይሆን ለስፖንሰሮች ጥያቄ ነው ማለታቸው ስለሆ ነ፡፡

አሁንም የቅማንት ህዝብ ይሁን የማንኛውም ህዝብ ህገመንግስታዊ የማንነት እና የመብት ጥያቄ ህጋዊ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገ እንጂ በአፈሙዝ የሚፈታ አይደለም፡፡ ስለዚህ የክልሉ ምክርቤት እንደጀመረው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ህጋዊ በሆነ አገባብ የተሟላ መፍትሀሄ በመስጠት መፍታት አለበት፡፡ በተጨማሪ የወንጀለኛው ብ / ጀ አሳምነው ፅጌ ዳና በመከተል ሰራዊት አዝምቶ ህዝብን በመጨፍጨፍ ላይ ያሉትን ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር ላይ በማዋል ወደ ፍርድ መቅረብ አለባቸው፡፡ በአማራ ክልል የመንግስት ባለስልጣናት የተፈፀሙት ዘር የማጥፋት ወንጀሎች ተጣርተው አስፈላጊውን እርምጃ ባለመወሰዱ፣ እነሆ ችግሩ እንደገና አገርሽቶ ህዝብን እንደ ህዝብ በመሰቃየት ላይ ይገኛል፡፡ ፌደራል መንግስት ያደረገውን የማጣራት ስራ ለህዝቡ ይፋ በማድረግ በወንጀለኞች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡

Full Website