ጌታቸው መስርያቤቱ የኢህአዴግ ሳይሆን የህገመንግስቱና የህዝብ ጠበቃ ሆኖ እንዲገነባ በትምህርትም በተግባርም ጥረት አድርጋል።ህገመንግስትና ህግ የሚጥስ ማንኛውም ወገን ኢህአዴግም ይሁን ኦፌኮ የመንግስት ባለስልጣን ይሁን የጠገበ ነጋዴ የፈለገው ብሄር ይሁን በመስርያቤቱ እኩል መስተናገድ አለበት ብሎ ያምናል መስርያቤቱም በዚህ ተመርቶ ስራውን እንዲሰራ ለመገንባት በተግባር በተደገፈ ጥረት አድርጋል።በፀረ ሙስና ትግሉ ወቅት፣ በከፍተኛ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ ሰብኣዊ ጥሰት፣ መልካም አስተዳደር ጉድለት፣ በሽብርተኝነት ጥናትና መረጃ ለመሰብሰብ እቅድ ሲወጣ ቁንጮ ላይ ትኩረት እንዲደረግ ታች ያሉ ተባባሪ ወንጀለኞች ያተኮረ ጥናትና መረጃ ብቻ እንዳይመጣ አጥብቆ ይታገል ነበር። የወንጀል ዋና አፍላቂ ጭንቅላት ትተን ተላላኪ ብቻ ጥናት ማድረግ ወንጀልን አያደርቅም።ከባዱ ስራ ትተን ዳር ዳር ለስላሳው ላይ ማትኮር የለብንም ብሎ ያምናል።ይህ ጌታቸው አሰፋን ይሁን ድህንነት መስርያቤቱንእንዲፈራ እንዲጠመድ አድርጎታል። በማን? በራሱ በኢህአዴግ ባለስልጣናት።በወንጀለኞች።ብዙ የስራ አስፈፃሚዎች እኛ የማንመራው መስራያ ቤት ነው።ስራ አስፈፃሚና ካድሬ ዝም ብለው እኛ ሳናቀው መረጃ ተሰብስቦባቸው እንዲታሰሩ እንዲከሰሱ ተደረገ ብለው ያማሉ።ያማርራሉ።ፓርቲና መንግስት የተለያየ ነው።መስርያቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትሩና በፓርላማ የድህንነትና የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ነው የሚጠየቁት ሲባሉ አይዋጥላቸውም።ህዝቡ ደግሞ ነፃ የሆነ መስርያ ቤት ይህ ነው ብሎ በሚስጥር በዙ መረጃዎች በስልክ በደብዳቤ በአካልም ወደ መስርያቤቱ ያጎርፈው ነበር። የመጣ መረጃ ሁሉ ሳያጣራና ማረጋገጫና ማስረጃ ሳይገኝበት ምንም ስለማይደረግ አንዳንድ መረጃ ያቀበሉ አላዳመጣችሁንም ብለው ተጨማሪ መረጃና ስሞታ ያቀርባሉ።ማስረጃ ያልተገኘበት የስንት ባለስልጣን ጉዳይ ለዛውም ስራ አስፈፃሚ መረጃ የያዘ መስርያቤትና የመስርያቤቱ ሃላፊ እንዴት ብሎ ሊወደድ ይችላል? ሳይታሰር እንመርማለን ማለት ይህ መሰለኝ።

መረጃና ማስረጃ ተሟልቶ ሲገኝ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔ መሰረት ከሚመለከታቸው መስርያቤት ከፀረ ሙስና፣ ከፌደራል ፖሊስና ከዐቃቤ ህግእንደወንጀሉ ዓይነት በመቀናጀት ስራውን ይሰራል። ጥናቱ የተሟላና ማስረጃ የማያወላዳ ይዞ ስለሚጀመር ተጠርጣሪዎች የማሳመን ችግር ብዙም አይገጥምም። ታድያ ድብደባ ምን ያመጣዋል። አንዳርጋቸው፣አንዷለም፣መራራ ወዘተ ተደበደቡ? ወይስ ለክብራቸው ሲባል ቢደበደቡም አይገለፅም።

ኤርትራና መንግስት አልባዋ ሶማልያ ሰፍረው የነበሩ ሽብርተኞችን የመከታተሉ ብቃት ለብዙ ዓመታት በአገራችን ኢትዮጵያ የሽብር ተግባር ጥቃት እንዳይፈፀም አስችላል።በዋነኛነት የሽብር ድርጅቶን ድብቅ መዋቅራዊ መርበብ ውስጥ ሰርጎ በመግባት ከላይ የሚያቅዱትን ቀድሞ በማወቅ ቀድሞ ማክሸፍና በአገርቤት የፈጠሩት ድብቅ መርበብ ሽባ እንዲሆን በማድረግ ከፍተኛ ስራ ተሰርቷል። ስራውን ከፌደራል ፖሊስ ከክልል ፖሊስና መከላከያ ሃይላችንና ከህዝቦች ተቀናጅቶ ይሰራ ስለነበረ አንዱና ትልቁ የስኬት ሚስጥሩ ነው። በኃላ በኃላ በወንጀል የሚጠረጠሩ በኢህአዴግ ባለስልጣናት በራሳቸው ሳቮታጅ መደርግና ኔትወርክ ተደራጅተው ጥቃትና ስም ማጥፋት ስለጀመረ ችግሮች ተፈጠሩ። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስተር የነበሩት ሃይለማርያም ደሳለኝም የከዱት መስርያቤት ነው ብዬ አምናለሁ። ይህ የግሌ ግምገማ ነው። ይህ የግሌ ግምገማ ሌሎች የመስርያቤቱ ባልደረቦችም ሳነሳላቸው የተጋሩት ነው።

በኢህአዴግ ባለስልጣን በራሳቸው ሳቮታጅ ለምን ተደረገ ወይም ተጀመረ? መቼስ ነበር የተጀመረው? ነብሱ ይማርና ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ በግምሩክና በአገርውስጥ ገቢዎች መስርያቤት ጥልቅ ጥናት እንዲደረግ አዘው መስርያቤታችንና ፀረ ሙስና በየፊናቸው ጥናት ያደርጋሉ። ጥናቱ ቢያልቅም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሞት ስለተለዩ መክሰስ ትችላላቹሁ የሚል ውሳኔ ዘግይቶ በአቶ ሃይለማርያም ነበር የተወሰነው።በጥናቱ መሰረት እርምጃ ተወሰደ።ህዝቡ ደስ አለው። ከጫፍ እሰከ ጫፍ ደገፈው።ለጠቅላይ ሚኒስትሩም ለኢህአዴግም በባህርዳር ጉባኤው ውሳኔ መሰረት በቃላቸው ተገኝተው መወስናቸውና በተግባር በራሳቸው ከፍተኛ አመራርና ካድሬዎችና አጭበርባሪ ነጋዴዎች እርምጃ መውሰዳቸው ትልቅ እርምጃና ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብሎ ህዝቡ በሁሉም ማእዝን ድጋፉን አሰማ።ተስፋ ቆርጦና ኢህአዴግ ከራሱ ጋር መቆራረጥ እንደ ድሮው አልቻለም ብሎ ሲያማው ስለነበር በዚህ ርምጃ ተስፋው እንደገና አቆጠቆጠ።

በኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚው ከጥቂቶች ስራ አስፈፃሚ በስተቀር ድርጊቱን በውስጣቸው ኮነኑት።ፀረ ሙስናው እርምጃ ደስታ ሳይሆን ስጋት ፈጠረባቸው።ትንሽም የቀመሰ፣ትልቅም የህዝብን ሃብት የገነደሰ እኩል ተጨነቀ።እርምጃው አደገኛና ቀጣይ ወዴት ሊያመራ እንደሚችል ተገንዝበው እርምጃውን ትግሉን ቀዝቃዛ ውሃ ለመቸለስ ቆርጠው ብልባቸው የወሰኑበት ቀን ይመስለኛል። በዚህ መቸለስ ቀንደኛ ተዋንያን የነበሩት ሌላ ጊዜ እመለስበታለህ።ራሱን አስችዬ። ህወሓትና ብአዴን እኛ ስራ አስፈፃሚ ሳናቅ ብለው ጠቅላይ ሚኒስተሩን ወቀሷቸው።በወቅቱ እንደሰማንው ሃይለማርያም የመለሱት ስልጣኔ ነው ብለው ነበር።ይህ የፖሊስ ስራ ነው።እንትና ይታሰር እንትና ይፈታ ወይ ብዬ ልጠይቀቹህ አልችልም።ፓርቲው በጉባኤው ሙስናን እንዋጋ ብሎ የለ በሚል መልስ ሰጥተው ታለፈ።ጥሩ ጀምረው ነበር።አልቀጠሉበትም እንጂ ጠቅላይ ሚኒስተሩ።በብርበራ የተገኘ የውጭና የአገራችን ገንዘብና ሌሎች ነገሮች በኢትዮጵያ  ቴሌቭዥን በዜና ሲተላለፍ የትግራይ ሚድያ ሳያስተላልፈው ቀረ።እንዳታስተላልፉ ተብለው።በትግራይ ህዝቡ ከጫፍ ጫፍ የተቀበለውና መለስ አልሞተም በሙስና ላይ እርምጃ መወሰዱ ሃይለማርያም እውነትም መለስን መተካት የሚችል መሪ ነው የሚል ድጋፍ ሰጠ።የህወሓት በተለይም አንዳንድ ስራ አስፈፃሚ አባላት ፀረ ሙስናእርምጃው አስመልክቶ ዜና ወድያውኑ እንዳይተላለፍ ከማድረግ አልፈው የትግራዩ ባለስልጣን ቤት ሲፈተሽ የተገኘውን አጉልቶ ዜና መተላለፉ ጥሩ አይደለም ብለው የፈዴራል ሚድያን የወቀሱ ነበሩ።ይህ ፀረ ሙስና ትግል ወደ እንትና የሚቅጥል እንዳይሆን ምን ያህል ነፃ ጥናት ነው ብለው ውስጥ ውስጡን ተንቀሳቀሱበት።

የብአዴን ማ/ኮሚቴም ስራ አስፈፃሚ ሲታሰር እንዴት ድርጅቱ አልተነገርውም ብለው ተቆጡ።መራራ ከኦነግ ጋር ሲገናኝ ማስረጃ አለንና ሊታሰር ነው ብሎ መንግስት ለኦፌኮ ድርጅት ማሳወቅ ነበረበት ብሎ ዓይነት ክርክር አደረጉ ብአዴን አመራር። በራሳቸው የውስጥ ትግል ነገሩ አዛው በረደ።ግን ጠቅልሎ ሳይጠፋ ተዳፍኖ ነበር የቆየው። ሁሌ የታሰሩት ብፖለቲካ ነው እያሉ የሚያለቃቅሱ ነበሩ።ነገ በኔ ብለው የሚሰጉ ማስረጃ ያልተገኘባቸው ሙሰኞች ተብለው የሚታሙት።በክልሉ ህዝብ ግን ድጋፍ ያገኘና ቀጥሉበት እንዳይቃረጥ የሚል ነበር።

ከዚህ በኃላ ነው ህወሓት ትግሬዎች በዙ ሲል፣ብአዴን አማራ ላይ ያነጣጠረ ነው ተብሎ ፀረ ሙስና እርምጃው ላይ የማጥቆር ዘመቻ በራሱ በገዥው ፓርቲ ውስጥ ውስጡን ተጀመረ።አማራ ትግሬ ምን አመጣው። የዚህ ድብቅ እንቅስቃሴ መሪው ደግሞ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ አባላት ነበሩ።የኦሮሞና የደቡብ ህዝቦችም በወቅቱ እርምጃውን ደግፈው የእርምጃው ቅድመተከተል ስህተት አለበት ዋነኞቹ የኢህአዴግ ባለስልጣን ሌቦች እኛጋ ያሉት ናቸው በኛ አካባቢ መጀመር ነበረበት አለ።የኦፒዲኦና የደህዴን በወቅቱ የሚታሙትና የተደናገጡት አመራሮች የተወሰደውን እርምጃ ላይ አስተያየት ባይሰጡም ደስተኛ ነበሩ ለማለት አይቻልም።

ሙስና ፈፅመዋል በተባሉ ተጠርጣሪ ባለስልጣንና ሌሎች ሰዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን በብዙሃን መገናኛ ዜና የተላለፈውና የፀረ ሙስና ኃላፊም መግለጫ የሰጡት የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ በወቅቱ ስብሰባ እያለ ነበር።የሚገርመው ነገር ይህን ህዝቦች የተደሱበትና ኢህአዴግ ላይ ተስፋቸው እንዲለመልም ያደረገ እርምጃ መወሰዱ ላይ ያለው አስተያየት የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ መግለጫ ላይ አለመካተቱ ህዝብም ሳይቀር በወቅቱ ታዝቦታል።ጉዳዩ በአንድ የኢህአዴግ ስብሰባ ከካድሬዎች ለምን ስራ አስፈፃሚው በመግለጫው አላከተተውም ተብሎ ሲጠየቅ‘’ቀድሞ አናቅም ነበር አልተነገረንም’’ የሚል አኩርፈን ነው ዓይነት መልስ በመስጠታቸው ድሮም መሪዎቻችን ተበላሽተዋል ብሎ በሚጠረጥረው ካድሬ ዘንድ መልሱ አላረካውም።ህዝብና የኢህአዴግ አመራር ለምን በዚህ እርምጃ ተለያዩ? መልሱ የሰረቀና የተሰረቀ ለምን አይለያይም ይመስለኛል።

የኢህአዴግ ባለስልጣን አንዱ አንዱን እንደድሮው እንዲቆጣጠረው አይፈልግም።እንከባበር ወይም በአንድ ላይ አንሄድም በሚል ራሱ ለመከላከል ወንጀሉን ለመደበቅ ኔት ዎርክ ዋነኛ መድሓኒት አድርጎ በየድርጅቱ አልፎ በኢህአዴግ ደረጃም በጥቅም ዙርያክልላዊና ሀገራዊ ደረጃ ኔትዎርክ በመፍጠር ሁሉም ነገር ከስብስባ በፌትና በኃላ ቀድሞ ወስኖ የሚገባና የሚያስወስን በኃላም የሚገመግም ሃይል ከሞላ ጎደል በሁሉም የኢህአዴግ ግምባር አባላት ብድብቅ ተደራጀ።መጀመርያ ራሱን ለመከላከል የተቃቃመ ነበር።ይህ በሂደት መልኩ እየቀያየረ እየተጠናከረ ዓላማውም እያሻሻለ መጥቶ ስልጣን ላይ ለመውጣት ጠቅሟል።በአራቱ ብሄራዊ ድርጅቶች ጉባኤ ሲደረግ በዚህ ኔትዎርክ ወደ ማ/ኮሚቴ ተመርጠው የመንግስትን ስልጣን መቆጣጠር ችለዋል።ህዝብን ለማገልገል ሳይሆን ራስን ከፍ አድርጎ ለመገልገል።

ይህ ነበር ህዝቡ አገልግሎት የሚሰጠው አጥቶ ጥያቄ እንዲያነሳ ያደረገው።ትምህርት ቤቶች ተስፋፍተው በየዓመቱ የሚመረቀው ወጣት ቁጥር እየበረከተ ሲመጣ ስራ መፍጠር የሚጠበቅበት ባለስልጣን ከመገልገል ወጥቶ ህዝቡን እንዲያገለግል ለወጣቱ ስራ እንዲፈጥር ሲጠይቅ የሚሰማው አጥቶ ስለ ተኛበትና አልሰማ ሲል መብቱን ለማስከበር ሲስለፍና ግርግር ሲፈጠር በኔትዎርክ ስልጣን ያገኘው ሃይል በጥልቀት ታድሶ የህዝብን ጥያቄ መመለስ ሲገባው ጀሮ ዳባ አለ። ውስጥ ውስጡን የወጣቱን ጥያቄ ቀልብሶ ወያኔ ነው ያልመለሰልህ።እኛ ምንም ማድረግ አንችልም።ኦሮሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኖ አያቅም።ወያኔ ኦሮሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር እንዲሆን አይፈለግም።ኦሮምኛ የፌደራል ቃንቃ ይሁን።አዲስ አበባ የኛ ናት።ልዩ ተጠቃሚዎች እንሁን።አማራና ኦሮሞ ትልቅ ብሄሮች እያሉ ሁሉንም ስልጣን የተቆጣጠረው ትግሬ ነው።ትግራይ በልዩ ስትለማ አንተ ግን አልለማህም።ኦሮማራ ፈጥረን ወያኔን ትግሬን እንጠራርገው።ጥልቅ ተሃድሶ አላደራጋችሁም ሲባሉ ይህን ራሳቸው በህዝቡ ያስተጋቡትን አጀንዳ ህዝቡ እንዲህ እያለ ነው ስብሰባ ማድረግ ማረጋጋት አስቸገረን ብለውበኢህአዴግ ስብሰባም ሳይቀር ያነሱ ነበር።ግርግሩን ራሳቸው ይመሩት እንደነበር በኃላ ግልፅ ሆኗል።

ለማ ቲም /ኔትዎርክ/ በዚህ መንገድ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኃላ እንዴት ብሎ ነው ከነጌታቸው አሰፋና ድህንነት መስርያቤቱ ጋር መስራት ፍላጎት የሚኖረው? እንዴት ብሎ ነው ከፌደራል ፖሊስ ጋር መስራት የሚዋጥለት? እንካን ከነዚህ መስርያቤት ይቅርና አታለውና ሸውደውት ወደ ስልጣን ያበቃቸው ኢህአዴግ ፕሮግራምና አስራር ጋር መሄድም ፍላጎትም ሙከራም ከመጀመርያው ጀምሮ አላደረጉም።

ስልጣኑ ከተገኘ በኃላ ቀጥሎ ስልጣኑ ባስተማማኝ እንዴት ይዘን እንቆይ ነው? ዋናው አጀንዳ ያደረጉት።የመደመር መፈክርና ማደናገርያ ተነድፎ ለጊዜውም የጫጉላ ሽርሽር እስኪያልቅ ድጋፍ አስገኘላቸው።ህዝብ ግን በንግግር ተስፋ ያደርጋል እንጂ እምነት የሚያሳድረው በተግባር ጥቅም ሲጠቀምና ለጥያቄው መልስ ሲያገኝ ነው። ሰላም ሲያገኝ፣ስራ አጥነት ተፈትቶ ስራ ሲያገኝ፣መልካም አሠራር ይስፈን ጥያቄው ተመልሶለት ፈጣን አገልግሎት ሲሰጠው፣ችግሩ ሲፈታለት ያኔ እምነት ያድርበታል። መሪዎቼ ብሎ ይቀበላል። በባዶ ቃልና ተስፋ ግን ተስፋ እንጂ እምነት አይፈጠርም።ተግባር ሲያጣ ደግሞ ድጋፉ እንደ ጉም በንኖ ጠፋ።

ለማ ቲም አገር ማስተዳደር ሳይችል ሲቀር የራሱን ብቃት መፈተሽ ሲያቅተው ጣቱን በሌሎች ላይ አሁንም ቀሰረ።ስልጣን ላይም ወጥቶ።ከሚልዮች የኦሮሞ ህዝብ ሙሁር ለማና አብይ ናቸው ብቁ? እንካን ከህዝቡ ከኦሆዴድ አመራር ከነበሩት እነዚህን በስንትና ስንት የሚበልጡ ታጥተው ናቸው እነዚህ በቅጡ ያልተማሩና ያልተመረቁ ኦሮሚያን መካን የሚያሰኙ እንካን ሀገርንና ኦሮሚያን አንዷን ደምቢደሎ ከተማን ማስተዳደር የማይችሉ ስልጣን የተቆጣጠሩት? በኔትዎርክና በውጭ ተመልምለው ሀገርና ህዝብ ጥቅም ሊያሳልፉ ተዋውለው ብቻ ለስልጣን የበቁ።ስልጣኑ ከሩቅ ሲያዩት ያምር ሲይዙት ያደናብር ሆኖባቸው ካጫፍ ጫፍ ሰላም ጠፍቶ ህዝቦች ለሞት ለመፈናቀል ለንብረት ውድመት ሲዳረጉ መጀመርያ ተገኝቶ የነበረው ድጋፍ ሲታጣ በድጋፉ ፋንታ የተበታተነ ቢሆንም ተቃውሞዎች ሲበራከት ጆኖሳይድ ሲፈፀም የለማ ቲም ምን ያድርግ።በመቀሰር ስልጣን ወጥቶ ስልጣን ላይ ለመቆየትም መቀሰር አዋጪ መስሎት አሁንም በሌሎች ይቀስራል። አንዴ በትግራይ ህዝብ፤አንዴ በህወሓት፣አንዴ በነባር የኢህአዴግ አመራር አንዴ ደግሞ በፌደራልፖሊስና በድህንነት መስርያቤቱና በኃላፊው ያሳብባል።

ይህን የአመጣጣታቸውንጉድ የሚያቅና ማስረጃ የያዘ መስርያ ቤትና ኃላፊውን ጌታቸው አሰፋን መጥመዳቸው እኔም በነሱ ቦታና ጫማ ሁኜ ትክክለኛ ውሳኔ ነው እላለሁ።ጌታቸው አሰፋ የሚመራውን መስርያቤት አባላት ሁሉንም ህዝቦች እኩል እንዲያዩ ሁሌም ይናገራል ብቻ ሳይሆን በተግባርም ጥረት ያደርጋል። መጀመርያ መስራያ ቤቱን መምራት እንደጀመረ ብዙ ሳይቆይ ምክትሎች ማድረግ አለብኝ ብሎ አቶ ወልደማርያም ዋቆና አቶ ኢሳያስ ወልደጀዮርግስን አደረገ። በሌሎችም ዋና መምርያና መምርያዎች ብዙ አዳዲስ ሰዎችን ከትግራይ ውጭ የሌላ ብሄር ተወላጆችን ኃላፊ አድርጎ ሾመ።ኢህአዴግ አባል ያልሆኑ ሞያ የነበራቸውን ስልጣን ሰጠ።በምልመላም ፖሊሲ በመቅረፅ ከሁሉም ብሄረሰቦች እንዲያካትት ሴቶችም የሚሳተፉበት ሁኔታ ለመፍጠር የሚያስችል ሆኖ እንዲቀረፅ አስደረገ።ለአስተዋፅኦ በሚል ብቃት የሌለውን ማግበስበስ የለብንም ብሎ ያምን ነበር።ብቃት መፍጠር ላይ መትጋት አለብን ችግሩን ለመቅረፍ በሚል ላይ ያየንውን የስልጠናና ትምህርት ፕሮግራም እንዲቀረፅ ያስደረገው ለዚህ ይመስለኛል።በአቅራቢያው የሚሰሩ ሙሁራዊ አቅም አማጦ መጠቅም የጌታቸው አሰፋ ልዩ ችሎታ ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም።በተግባር አይቸዋለሁ።መፅሓፍ አይለይም።ያነባል።ያነበበውን ለመስርያቤቱ እንደሚጠቅም አድርጎ ይገለገልበታል።በርሃ እያለ ምን አቅም እንደነበረው ብዙ ባላቅም ከመለስ ጋር ለብዙ ጊዜ መስራቱ ጠቅሞታል ብዬ እገምታለሁ።ታድያ እንደዚህ ያለ ንቁ የኢህአዴግ ‘’ቁራጭ’’ እነ አብይ ለማ ገዱ ደመቀ ማሳደዳቸው ምኑ ላይ ነው ስህተታቸው? ተሳስታቹሃል።ወንጀለኞች ናቹህ? ከአብዲ የምትለዩት ነገር የላቹህም የሚላቸውን ጌታቸውን በምን ሂሳብ ርኅራኄ ይምጣላቸው? አብዲን የሶማሊን ህዝብ እየበደለ ነው።እየገደለ ነው።የኦሮሞን መንደሮች በወሰን አሳብቦ እያጠፋቸው ነው።ኦሮሞዎች ፖሊሶችና ሚሊሻዎችን እየገደለ ነው ብሎ ከኦህዴድ በፊት እንዲከሰስ የጠየቀው ጌታቸው አሰፋና መስርያቤቱ ነበሩ።
Full Website