24/7/19

ከአንድ አመት በላይ ያስቆጠረው የአገራችን ቀውስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ በተለይ በአሁኑ ሰዓት ሁኔታዎች ከመንግሥት ቁጥጥር እየሆኑ በመምጣታቸው በግልፅና በህግ ባልታወጀ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚል ሽፋን ከትግራይ ክልል ውጪ ያሉ ክልሎች ይብዛም ይነስም በፌዴራል የተላከ የፀጥታ ሃይል እጅ ወድቀው ይገኛሉ ፡፡ የአገሪቱ ቀውስ መነሻውና መፍትሔው በግልፅ ለይቶ መፍታት ያቃተው በስልጣን ላይ ያለው ጥገኛው ቡዱን ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ራሱ በሚፈፅመው ህገመንግስታዊ ጥሰት በአብዛኛው ራሱ የግጭት መነሻ እየሆነ በመሄዱ እስከ አሁን የአገሪቱ ችግር መፍትሔ ሊያገኝ አልቻለም ፡፡ በቀጣይም ይሀው በተግባር እንደሚታየው ይብሳል እንጂ የሚመጣ ኣንዳችም ለውጥ እንደሌለ እያንዳንዱ ዜጋ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ መገመት አያስቸግረውም ፡፡ በዚህ ከአንድ አመት በማይበልጥ ጊዜ በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል የተጀመረው ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ ወደ አብዛኛዎቹ ክልል በመዛመት አሁን አድማሱን በማስፋት የደቡብ ክልል በማዳረስ እንሆ ተራው ደርሶ እንደ ክልል ሁሉም ነገር ከቁጥጥር ውጪ በመሆኑ በቀጥታ በወታደራዊ ጣልቃ ገብነት የክልሉ መዋቅር ከጥቅም ውጪ በማድረግ የፌዴራል የፀጥታ ሃይል እንዲያስተዳድረው ተወሰኖ ወታደሩ በይፋ ስራውን እንደጀመረ በይፋ ታውጀዋል ፡፡ ከትግራይ ክልል ውጪ ያሉ አብዛኛዎቹ ክልሎች ወደዱም ጠሉም በቀጥታ ከፌደራል መንግስት ባለሥልጣናት በሚመጣ ቀጭን ትእዛዝና መመርያ ብቻ ከመመራት ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላቸውም በግልፅ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፊት ሳይቀር ማስጠንቀቅያ አዘል መልእክት እንዲተላለፍ መደረጉ ፅንፈኛው ቡዱን ከዚህ በሃላ የመጨረሻ አማራጩ ወታደራዊ ሃይል በመጠቀም ኣገሪቱን ለማስተዳደር እንደወሰነና ይህን የማይቀበል ማንኛውም ሃይል የኢትዮጵያ ሶማሌ ዕጣ እንደሚደርሰው በግልፅ ተነግረዋል ፡፡ የፀጥታ መዋቅሩ ስራ በህግ ተገድቦ እስካልተሰጠውና የክልሉ መንግሥት እጁን ለዚህ ኮማንድ ፖስት ተብሎ ለተሰየመው አካል እስከሰጠ ድረስ ሁሉም ነገር በፌዴራል ውሳኔና ፍላጎት ብቻ እንደሚወሰንም ምንም ጥርጥር የለውም ፡፡ የፀጥታ መዋቅሩ በሃይል የገባቸው ክልሎች ለአንዴና ለመጨረሻ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በወታደራዊ ሃይሉ ብቻ ነው የሚታዘዙት ፡፡ ተጠሪነታቸው ለዚህ ኮማድ ፓስት እስከሆነ ድረስ እንደ ትናቱ መንግሥትን መቃወም ለውጡን ኣለመቀበል በፍፁም አይቻልም እያለ የፈለገውን ሃይል ያስራል ይቀጣል ከስልጣን በማውረድ የፈለገውን ሃይል ይሾማል ፡፡ በተግባር እየታየ ያለውም ከዚህ የተለየ ኣይደለም ፡፡ የፀጥታ መዋቅሩ የፈለገውን እንዲያደርግ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃላፊነትና ውሳነ ብቻ ሙሉ ስልጣን ተሰጥቶታል ፡፡ ይህን የማይቀበል ክልል ካለ ፀረ ለውጥ እየተባለ ወህኒ ቤት እንደሚወርድና የማስመሰያ የፌክ ፊልም እየተሰራ አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣ ያው የኢትዮጵያ ሶማሌ አመራሮች የደረሳቸው ቅጣት አይነተኛ ምሳሌ ነው የሚሆነው ፡፡ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልን በሃይል በማፍረስ መጨረሻው የፌዴራል ተቀጥያ መዋቅር እንዲኖር እንደተደረገም ሁሉም የሚያውቀው ሃቅ ነው ፡፡ በቃ መልእክቱ እያንዳንዱ ክልል ከዚህ ውጪ መሄድ ኣይፈቀደም ያስቀጣል ተብሎ እስከተነገረ ድረስ ወይም መቀበል ወይም ይህ ኢ ስለዚህ የፌዴራል መንግሥት ክልሎች የመቆጣጠር ዋነኛ አላማው ሲታይ ራሱ ሆን ብሎ ገንዘብ በመመደብ እሳቱን የሚለኩሱት የራሱን ተለላኪዎች በማሰማራት ግጭት እንዲፈጠር በማድረግ ይህን እንደምክንያት በመጠቀም በቀጥታ ክልሎች በሃይል በመቆጣጠር ክልላዊ መዋቅሩን በማፍረስ የክልሎች ህልውና እንዲያከትም በማድረግ ወደ አሃዳዊ ስርዓት ለሚደረገው ሽግግር የተመቸ ሁኔታ በመፍጠር የመጨረሻው ህገመንግስታዊ ስርአቱ የማፍረስ ግቡን ለማሳካት የሚያደርገው ሩጫ መሆኑም ለማንም ግልፅ ነው ፡፡ ይህ አደገኛ ስልት ደግሞ ፀረ ህዝብ ሃይሎች ህዝብን የሚያሰልፍ አጀንዳ ቀርፀው ማሰለፍ ስለማይችሉ በስልጣን ላይ ለመኖር ያላቸው ወታደራዊ ሃይል በመጠቀም ህዝብን በሃይል ለማስተዳደር የሚጠቀሙበት የመጨረሻ ምሽግ መሆኑ ያው በአጠቃላይ በአፍሪካ በተለይ በአገራችን ትናንት ተሞክሮ የወደቀ የተለመደ የማይሰራ ስልት ነው “የዘመኑ” ፅንፈኞችም እየተከተሉት ያሉት ፡፡ ግን ያዋጣቸው ይሆን
Full Website