Back to Front Page

ሁለት ሰዎች ተመሳሰልቡኝ ፡- ክፍል 2

ዘመድኩን ዘሪሁን 9-21-19

ከዚህ በፊት በግንቦት  ወር  ሁለት ሰዎች ተመሳሰልቡኝ በሚል ርዕስ በሌ/ኮሎኔል መንግሰቱና ሌ/ኮ አብይ ፅሁፍ አቅርቤ ነበር፡፡ አሁንም ግን ከመመሳሰል አልፎ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ዋናው ነገር  ወደ ኃላ መለስ ብሎ የሌ/ኮ  መንግሰቱ ባህርያት ማየትና አለማየት ካልሆነ በሰተቀር ሰዎቹ ልዩነት የላቸውም፡፡ፍርዱን ግን ለአንባቢ እተወዋለሁ ፡፡ ሙሉ ድምዳሜ ለመደረስ ያዳገተው ሰው ካለ ክፍል አንድ መለስ ብሎ ማየት ጠቃሚ ነው፡፡

1. ዘረኝነት  እየሰበኩና ህብረ ብሄር በማጠልሸት ስለ አገር አንድነት ማቀንቀን

ሌ/ኮ መንግሰቱ ወደ ስልጣን በወጣ በማግሰቱ  የከፈተው ዘመቻ የብሄር ጭቆና ይወገድ ያሉና የራስ አስተዳደር (self administration) የጠየቁ ህዘቦች የተለጠፈላቸው ታርጋ “ጠባብ አስተሳሰብና  እና የጎሳ ልይነቶች ይውደሙ ’’ ነበር ፡፡  የሌ/ኮ  መንግስቱ ትግላችን መፅሀፍ ገፅ 321 ያለው መፈክር መመልከት ይቻላል ፡፡ ኢህአዴግ መሀል አገር ሲደርስ  ሌ/ኮ መንግሰቱ ሸዋ ይዘምታል እንጂ አይዘመትበትም በማለት አንድ ህዝብ ከሌላኛው ህዝብ ለማጋጨት ዘረኝነትን ይቀሰቅሱ ነበር ፡፡ የሚገርመው ይህ ዘረኝነት የሚሰበከው አንዲት ኢትዮጵያ ወይም ሞት በሚል የሌ/ኮ/ል መንግሰቱ በአንድነት ስም ጨፍላቂ/አሃዳዊ አስተሳሰብ ነበር ፡፡ አሁንም እነ ሌ/ኮ አብይ እየዘመሩ ያሉት ተመሳሳይ ነገር ነው፡፡ ሆኖም በዚህ ፍልሰፍና ኤርትራ ስትገነጠል ሌሎች ህዝቦችም በ30 አመት የእርስበርስ ጦርነት ብዙ ፍዳ አይተዋል ፡፡ የኢ/ያ ህዘብ ማወቅ ያለበት አምበገነኖች የማይጨበጥ መፈክር የሚያስተጋቡ ፈሪዎችና ዘረኞች ናቸው፡፡

ሌ/ኮ አብይ በተመሳሳይ ዘረኝነት እያራመደና ህብረ ብሄራዊነትን እያንኳሰሰ ህዘቡን በማሸማቀቅ በስጋት  እንዲኖር እያደረገ ነው ፡፡ ልክ ሌ/ኮ መንግሰቱ ከሌለ አገር ትፈርሳለች ሲሉ የነበሩ ጁንየር የደርግ አባላት እነ ፶ አለቃ ለገሰ አስፋው ጨምሮ እጅግ ብዙ ነበሩ፡፡ በተመሳሳይ  መልኩ ከአብይ ውጪ አገር ትፈርሳለች የሚሉና ሲያስነጥሱም  የዶ/ር አብይ  ለውጥ ይማረኝ የሚሉ በርካታ ጁንየር ሴት ባለስልጣናት ተፈጥረዋል ፤የወንዶች እንደ ተጠበቀ ሆኖ፡፡ ከሌ/ኮ አብይ የዘረኝነት መገለጫ ዉስጥ  ለምሳሌ  እኔ አንድ ነገር ከሆንኩ  ወይም ስልጣን ከወረድኩ  አለቀልህ  በአንድ ቀን 100 ሺህ ሰው ያልቃል በማለት በም/ቤት ፊት ሽብር ለቋል፤ የሚገርመው ነገር ደግሞ በኦሮምያ ምደር አደጋ ከደረሰብኝ  ኦሮሞ እርስ በራሱ ይተላለቃል ፤ ወታደሮቹ  ቤተ መንግሰት  “ለመፈንቅለ መንግሰት” ሲገቡ  መንግሰታችን ተጠቃ ብለው ወጣቶች ከቡራዩ፤ ሰበታ፤ለገጣፉ  ወዘተ  ወደ አዲስ አበባ  መጥትተው  የአዲስ አበባ ህዘብ ሊጨርሱት ነበር እኔ ተው ብይ ነው እንጂ  አይነት መልዕክት በምክር ቤት አስተላልፋል ፡፡ አሁን ይህ ሽንገላ የሚያመለክተው  ህዘቡን እርስ በርሱ በማጋጨት ስልጣን ላይ ለመቆየት የሚደረግ የ(double standard) አካሄድ ነው፡፡  በመጨረሻም የአመቱ  የህብረ ብሄራዊ የማንኳሰስና ዘረኝነት ዘመቻ ማሳረግያ ደግሞ በአንዲት ታዳጊ  በግጥም መልክ  በቤተ መንግሰት የቀረበው ድራማ ነበር፡፡ (ደራሲ የቤት መንግሰት ባለሟል ዳንኤል ክብረት፤ ዳይሬክተር ሌ/ኮ አብይ፤ ተዋንያን አዴፓ/አብን አባላት፤ ከአብን ጋር የተደመሩ ኦዴፓ አባላት ናቸው ፡፡ ክብርት ፕሬዝደንትዋ ተጋባዥ ተመልካች ነበሩ፡፡

2. በዘመቻ መልክ የአለም ቀልብ እየሳቡ  በአገርቤት አመባገነን  መሆን

የሌ/ኮ መንግሰቱ የመሰረት  ትምሀርት  ዘመቻ  ፡- አዛውንትን ሁሉ  በቀበሌ አዳራሽ ሰብስቦ አበበ በሶ በላ እያለ ፊደል እያስቆጠረ በአለም ጉድ የተባለና ቀልብ የሳበ ዘመቻ  አደረገ ፡፡ በሌላ መንገድ ደግሞ ከሜኤሶን ጋር አብሮ እጀግ በጣም የተማሩና ተራማጅ ወጣቶች ፀረ አብ ት እያለ አስወግደቸዋል፡፡ ማለትም  በአንድ በኩል ማይምነት አጠፉሁ እያለ በሌላው መንገድ ደግሞ የተማረው ወጣት በቀይሽብር ጨረሰው  ( በወቅቱ  ደርግ ዛፍ ቆርጦ  የማይፀድቅ ችግኝ  ይተክላል ተብለዋል) ፡፡ ሆኖም እንዲህ አይነት ቀውስ እየፈጠረ በወቅቱ የአለም ሚድያ እወቀና አግኝቷዋል ፡፡ በማስከተልም በአጭር ጊዜ ከወዳጅ አገር አብዮታዊ መሪ ተብሎ በርካታ አለም አቀፍ ሽልማትና ኒሻን ተቀብሏል ፡፡ የወዳጅ አገር አለም አቀፍ ድጋፉ ለጊዜውም ቢሆን የአገር ውስጥ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ለመጨፍለቅና ለማደብዘዝ ድጋፍ አለኝ ብሎ ለማወናበድ አግዞታል፡፡

ሌ/ኮ አብይ የለውጥና መደመር ዘመቻ፡- ሁሉም አይነት ሰው/ፓርቲ/ቡዱን በየአዳራሹና ስቴድዮሙ እየሰበሰበ “የመድመር መርህ” እያለ ከያሉበት ሲመጡ ደማቅ አቀባበል ተቀበላቸው፡፡ በዚህም ለጊዜው በአገር ቤትና የአለም  ቀልብ መሳብ ችልዋል፡፡ የአለም ሚድያም ብዙ እወቅና በማግኘቱ የለውጥ መሪ ተብሎ በማግሰቱ ኒሻንና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡ ሽልማቱም ለቀጣይ ጥሩ አሽከር ይሆናል በሚል ነው፡፡ ሆኖም ጊዚያዊ እወቅናው ልክ እንደ ሌ/ኮ መንግሰቱ  አይነኬ ሆኖ ለዕብሪትና ለማሰፈራራት ተጠቀመበት፡፡  ለምሳሌ በውጭ የነበሩ ቡዱኖች እንደገቡ ተቀባይነታቸውን በመስጋት ያለምንም ማሰረጃ መሰከረም 2010 ዓ.ም ቡራዩ ላይ የተፈጠረው ቀውስ ጊዜ ሳይወስድ ኦነግና ግንቦት ሰባት ናቸው ብሎ በፌደራል ኃላፊ ፖሊስ ዘይኑ ጀማል መግለጫ ተሰጠ፡፡ ይህን ተከትሎ ሰኞ እለት በአዲሰ አበባ ከተማ  በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ  ሰልፎኞች መሳርያ  ሊቀሙ ሲሉ 28 ሰዎች ተገድለዋል በማለት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ደግፌ በዴ መግለጫ ተሰጠበት፡፡ ሌሎች ምንጮች የሞቱት ሰዎች ቁጥር 45 ነው ብለዋል፡፡ ሆኖም በነበረው የለውጥ ዘመቻና ፕሮፓጋንዳ ለጊዜውም ቢሆን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቱ ተድበሰብሶ አልፋል ፡፡

አሁን  በአመቱ መስከረም 2012 ደግሞ ቡራዩ የተከሰተው የቦምብ ፍንዳታ ሌ/ኮ አብይ ከግም ሰባት/ኢዘማ (የቤት መንግሰት ቤተኛ) በመመሳጠር ልክ እንደ አምና በሌ/ኮ አብይ  ተዘጋጅቶ በፖሊስ በተሰጠ መግለጫ  ተጠያቂ ኦነግ ነው ተብላል፡፡ ግም ሰባት/ኢዜማ ግን አሁን ከሌ/ኮ አብይ ጋር ስለተደመረ ከክሱ ነፃ ሆናል፡፡ ከዛም አልፎ ወደ ከሳሽነት ተቀይረዋል (ልክ እንደ ሚኤሶንና ደርግ የነበረው ጥምረት)፡፡

የሌ/ኮ መንግሰቱ መፈክሮች ፡- አብዮዊት ኢትዮጵያ ወይም ሞት ፤አድኃርያን ብቻ ሳይሆን ተፈጥሮን  በቁጥጥራችን ስር እናደርጋለን፤ ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር፤ ማን ይፈራል ሞት ወዘተ ሌ/ኮ መንግሰቱና ተከታዮች ዘውትር ሲያሰተጋቡ የነበሩ መፈክሮች ናቸው፡፡ ፡፡በመጨረሻም አንድ ጥይትና አንድ ሰው እሲኪቀር “ለኢትዮጵያ አንድነት እንዋጋለን /እንሞታለን ” እያለ  ሲያቅራራ ቆይቶ ቤተሰቡን አስቀድሞ በማሽሽ አገርና ህዘብ ከድቱዋል፡፡ እሱ ሞት ይቅርና እሾህ ሳይወጋው 17 አመት ሙሉ  ህዘቡን ሲያፈናቅልና በጅምላ ሲገድል ቆይቶ አገር ጥሎ ሄደ ፡፡

ሌ/ኮ አብይ መፈክሮች፤- በተመሳሳይ ሁኔታ ከሞት ጋር ተያይዞ የተለያዩ መፈክሮች  በየጊዘው እየፈጠረ ይገኛል ፡፡ለምሳሌ፡- ስንኖር ኢትዮጵያዊ  ስንሞት ኢትዮጵያዊ ፤ ኢትዮጵያዊ ሆኖ መሞት፤ ሞት አልፈራም እንድያውም እሱ እኔን ይፈራኛል  ፤ በመደመር ፍልስፍና ሁሉም ነገር ወደፊት ሆኖም ሁሉም እየተቀነሰ ይገኛል፡፡ ህዘቡን  ማፈናቀል፤ ማሰር፤በስውርና በግልፅ መግደል፤ ግጭት መፍጠርና ጣልቃ መግባት ተያይዞታል፡፡ ሆኖም  ኮሽታው ከጨመረ  እንደ ሌ/ኮ መንግሰቱ ልጆቹን ለመላክ ቪዛ ተዘጋጅታል (ሶስት ልጆቹና ሚሰቱ የአሜሪካ መኖርያ/ዜግነት ቪዛ አላቸው ) ፡፡

አሁን ደግሞ ልክ እንደ ሌ/ኮ መንግሰቱ  በደርግ  ሸንጎ ፊት የኢ/ያ ህዘብ ትግል  ለመጨፍለቅ ያሰማው ቀረርቶ “አንድ ሰውና አንድ ጥይት  እሲኪቀር ለኢትዮጵያ አንድነት እንዋጋለን ብሎ እንዳቅራራ ሁሉ ሌ/ኮ አብይ በተመሳሳይ መልኩ የኢህአዴግ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ፊት በተመሳሳይ አዳራሽ ከሲዳማ የክልል ጥያቄ አያይዞ በዘፈነው ቀረርቶ “ ለኢትዮጵያ አንድነት ክላሽ ይዘን እንዋጋለን ” ሲል ገልፀዋል፡፡ ይህ የደርጋውያን ፍልስፍና ነው እንግዲህ አገር እያፈረሰ  ያለው፡፡

ይህ ምን ማለት ነው ? የትኛው የውጨ ወራሪ መጥቶ ነው መብት ለጠየቀ ህዘብ አንድ የአገር መሪ ክላሽ ይዤ እዋጋለህ ብሎ ማስፈራራት ምን አመጣው ፤ ለመከላካያ ሰራዊትስ ምን አይነት መልዕክት ነው ያስተላለፈው? መብት ለጠየቀ ልክ እንደ ደርግ “እንቢ ያለ ሰው ጥይት አጉርሰው” የሚል ነው ፡፡ ከዚህ ተከትሎም በሌ/ኮ አብይ ሆን ተብሎ ግጭት የተፈጠረባት ተረኛዋ ሲዳማ የመቶዎች ሂዎት አልፈዋል፤ በጅምላ ታስረዋል፤ ሰብአዊና ዲሞከራሰዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ ታግደዋል ፡፡

3. ኮማነድ ፖስት/አስቸኳይ ጊዜ ፡-ሌ/ኮ መንግሰቱ ወታደራዊ ዘመቻ፡- መብት ለጠየቁ ህዘቦች  በወቅቱ ይሰጠው  የነበረው  መልስ በተለይ ግጭት የነበረበት አከባቢ ሙሉ በሙሉ በወታደራዊ አገዛዝ ስር  ማድረግ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት ወታደሩ ከህግ ውጪ ያልተገደበ ስልጣን  ተሰጥቶት ሲያስር፤ ሲገድል፤ ሲያፈናቅል፤ስልጣን ሲያዋርድና ሲሾም ነበር ፡፡ በዚህ መሰረትም  የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በግልፅም /በውስጠ ታወቂነትም  በኤርትራ፤ በትግራይ፤ ወሎ፤ ጎንድር፤ሶማሌ ክልል (ኦጋዴን) የምዕራብ ኢ/ያና ሌሎች ኮሽታ የተሰማባቸው ቦታዎች ሁሉ በልዩ ወታደራዊ ዕዝ ስር ነበሩ፡፡ የስልጣን ማራዘምያ/ማቆያ መንገድ መብት ለጠየቁ ህዘቦች የጎሶኞች፤ጎጠኞችና የዘረኞች ፖለቲካ  የሚል ታርጋ ለጥፎ በጦር ሰራዊት ይጨፍጨፍ ነበር፡፡ ሌ/ኮ አብይም እንደ ሌ/ኮ መንግሰቱ ትምክህትን እያደነቀ ብዙህነትን በቤተ መንግሰት ሳይቀር የዘር ፖለቲካ እያለ በግጥም መልክ ያጣጥለዋል፡፡ ስለሆነም  ልብ ብሎ ለተመለከተ ወገናዊነቱ ወደ ስልጣን የወጣበት አስተሳሰብ ሳይሆን የዚህ ቀጥታ ተፃራሪ የሆነው አሃዳዊ ነው፡፡

Full Website