የችግኝ ፖለቲካ

ወላጅ አልባ ችግኝ (orphan) ተክሎ የአለም ሪኮርድ ተሰበረ ማለት ይቻላል ወይ ?

ዘመድኩን ዘሪሁን 8-3-19

በግንቦት ወር ሁለት ሰዎች ተመሳሰሉብኝ በሚል ርዕስ የሌ/ኮ አብይ ከሌ/ኮሎኔል  መንግሰቱ  በህርያት አቅርቤ ነበር አሁን ይህቺ አጭር ፅሁፍ  ጀባ ብያሎህ ፡፡ በሌላ  ፅሁፍ ደግሞ አሁንም እነዚህ  ሁለት ሰዎች በጣም እየተመሳሰሉብኝ ስለሆነ  ቁ 2  አቅርባላሁ፡፡

ኢትዮጵያ የአረንጋዴ ኢኮኖሚ ለመገንባትና በአየር ንብረት ለወጥ ሰፊ ጥረት ማደረግ ከጀመረች በርካታ አመታት አድርጋለች ሚድያወቹ ግን ችግኝ መትከል ሀምሌ 22/2011 በሌ/ኮሎኔል አብይ የተጀመረ አስመስለውታል ፡፡ አገሪትዋ ከዚህ በፊትም  እንደዚህ የተሸባረቀ ባይሆነም  በዘመቻ ችግኝ ለመትከል ቦዝና አታውቅም፡፡ ኢ/ያ በታሪክዋ በዘመቻ መልክ በየወቅቱ ያልታቀደና ዘላቂነት የሌለው ስራ ሳይሆን ስራ የሚመስል ነገር እየፈጠሩ በአዋጅ በማሰነገር ህዝቡ የውዴታ ግዴታ አይነት ለፖሊታካ ፍጆታ ማዋል የአገራቸን መሪዎች ተግባር ነው፡፡ በተለይ ሌ/ኮ  አብይ ዋነኛ መለያ ባህሪ መሆኑ ልይነት ያለው ኢትዮጵያዊ አለ ብየ አላሰብም ፡፡ በሌ/ኮ አብይን አካሄድ  ራዒና ፍኖተ ካርታ የሚባል  የለም ፡፡ የሌ/ኮ አብይ ፍኖተ ካርታ(road map) ለአንድ ሳምንት ወይም አንድ ቀን ወይም ለአንድ ሰአት የሚያቆየው ፕሮፓጋንዳ ካገኝ  በቂ ነው ፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ሌላ አጀንዳ በመፍጠር ህዘቡን  ለጊዜው ማወናበድ ያውም አሁን የሚደናገር ካለ ነው ፡፡ የሚገርመው ግን ከሌ/ኮ መንግሰቱ  ለማማር አለመቻሉ ነው፡፡

ችግኝ መትከል ተቃወሞ ያለው ዜጋ የለም ሊኖርም አይችልም ትልቁ ችግር ግን ህ/ሰቡን በአጀንዳ ለመጥመድ  ያዘጋጀው የችግኝ ተከላ መሆኑ ነው ፡፡ በኢ/ያ ታሪክ በዘመቻ መልክ ተሰርቶ የተሳካ ስራ የለም ፡፡ የአሁኑ ለየት የሚለው በስፋት የፕሮፓጋንዳ መሳርያ መሆኑና የሌ/ኮ አብይ ዝና ከፍ ለማድረግ መሰራቱ ነው፡፡ ለምሳሌ የተደመሩ ሚድያዎች ቤተ መንግስት እግር የጣለው ሁሉ  ከጠ/ሚ  አብይ  አብሮ ችግኝ ተከሉ እያሉ መዘገብ ብቻ ነው ስራቸው ፡፡ ይባስ  ብሎም ከተወሰነ ሳምንታት በፊት ፋና  ጠ/ሚ አብይ 100ኛ  ችግኛቸው  ተከሉ  ብሎ እንደ ቀዳሚ ዜና መዘገብ ፤የሰው አጀንዳ  ለማስቀየስና አዛኝ መስሎ ለመቅረብ      “በመፈንቅለ መንግሰት” ለሞቱት አመራሮች ስም ጠ/ሚኒሰተሩ ችግኝ ተከሎ ብሎ የሰበር ዜና መስራት ነበር ሆኖም ህዝቡና የማች ቤተሰቦች በነሱ ስም ችግኝ ትከልልን ሳይሆን እያሉ ያሉት ማጣራቱ በገለልተኛ አካል ይሁን አንደ አንጂነር ስመኘው ማጣራት ተጭበርብሮ/ተድበስብሶ እየቀረ ነው እያሉ ያሉት፡፡ ከሁለት ሳምንት ጀምሮ ደግሞ የተደመሩ ሚድያዎች ችግኝ ተከላው በየቀኑ 10 ቀን ቀረ ፤ 9 ቀን ቀረ ና 1 ቀረ  እያሉ  ህዘቡ የአለም ዋንጫ  የሚጣባበቅ አስመሰሉት፡፡ በዕለቱ (ሀምሌ 22) የነበረ ዜና ደግሞ የዶ/ር አብይ 4 ቢልዮን ችግኝ የመትከል ራኢ ለማሳካት ህዘቡ በነቂስ ወጥታል፤ በዕለቱ  ደግሞ ኢትዮጵያ በህንድ ተይዞ የነበረው የአለም ክበረወሰን መሰበሩን ጠ/ሚ አብይ ለኢ/ያ ህዘብ አበሰሩ አሉ ተደማሪ ሚድያዎቹ፡፡

እነዚህ ዜናዎች ተደምረው  የሚሰጠት እንደምታ በችግኝ ፖለቲካ ራስን ማጉላትና ህዘቡ በየጊዘው አጀንዳ እየፈጠሩ መጥመድና ሌ/ኮ አብይ ትአምር እንደሰራ አድርጎ ለመሳል የተዘጋጀ   እንጂ ችግኝ ዋነኛ ጉዳይ አለመሆኑ ለማንም ግልፅ ነው ሆኖም አካሄዱ የተበላ ዕቁብ ከሆነ ቆይተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያሉ ቦታዎች በተደጋጋሚ ችግኝ ያልተተከለበት  ቦታ አለ ብሎ መውሰድ አስቸጋሪ ነው፡፡ ከደርግ ጊዜ ጀምረን አረንጋዴ ዘመቻ እያልን በዘመቻ መልክ ተክለናል አሁንም እየተከልን ነው፡፡ አንድ የመንግሰተ ሰራተኛ ጋደኛየ እንዳጫወተኝ በአዲስ አበባ ዙርያ የሚገኝ ስፍራ በተመሳሳይ ቦታ ሀምሌ 22/2011 ለ4ኛ ጊዜ ችግኝ ተክያሎህ ብሎኛል ከዚህ በፊት የተከልኩት ችግኝ በቦታው የለም ፡፡ አንድ ነገር እረግጠኛ መሆን ያለብን ልጅ ወልዶ ተንከባክቦ ማሰደግና ችግኝ ተክሎ ተንከባክቦ ማሰደግ ሁለቱም እኩል ክብደት አለቻው ፡፡ በሌላ አገላለፅ  ደግሞ ልጅ ዝምብሎ መውለድና ችግኝ ዝምብሎ መትከል ሁለቱም ቀላል ናቸው ስለሆነም ሌ/ኮ አብይ  የአለም ሪኮረድ  ሰብረናል እንኳን ደስ አላቹህ ብሎ በሚድያ መናገር የልጆች የእቃ እቃ ጨዋታ ነው፡፡ አሱ አልነገረንም  እንጂ ዜጎች በማፈናቀልም የአለም ሪኮርድ ሰብረናል ፡፡ ሌ/ኮ አብይ  አሁን እያለ ያለው  እንደ ሀይለ፤ ደራርቱ፤ቀነኒሳ ፤የዲባባ ልጆች ወዘተ ሪከርድ  ሰብሬ አሎህ ስለሆነም ለእነሱ በሰልፍ ያደረጋቹሁት ድጋፍ አይነት ለኔም አድረጉ ነው ፡፡

አሁን ላለፉት 50 አመታት ችግኝ በዘመቻ መትከል እንጂ ችግኝ መንከባከብ አልቻልንም ምክንያቱም የዘመቻ ነገር እንደተለመደው በሌ/ኮ አብይ መሪነት 4ቢልዮን ችግኝ ተክለን የአለም ሪከርድ ሰብረን ለማለት ነው፡፡ ብዙ ችግኝ በመትከል በቻ አይደለም ብዙ ልጅ በመወለድም ሪከርድ ሰብረናል ፡፡

ሌ/ኮ አብይ የህንድ ህዘብ  ብዛት 1.2 ቢልዮን ሆኖ  በአንድ ጅንበር 63 ሚልዮን  ብቻ ተከሉ እኛ 100 ሚልዮን ህዘብ ይዘን ከ ሚልዮን በላይ ችግኝ ተከልን ሪኮረድ ሰብረናል እንከን ደስ አለን ሲል ገልፀዋል፡፡ ሌ/ኮ አብይ ያልገበው ነገር ወይም ሊያድበሰብሰው የፈለገው ነገር ህንዶች በአንድ ቀን የተከሉት 63 ሚልዮን ችግኝ ለብዙ አመታት ሰፊ ጥናትና ዘግጅት አድርገው፤ የአፈርና ችግኝ አይነት ለይተው፤ ችግኙ እስኪያድግ ለእንክብካቤ በጀትና ሞያተኞች መድበውና 100 % እንደሚፀድቅ እርግጠኛ በመሆን ነው ችግኝ የተከሉት እንጂ  በአባት ወኔ  እንደ ሌ/ኮ አብይ ብድግ ብለው 4 ቢለዮን የማይፀድቅ ችግኝ የተከሉት ፡፡ የኢትዮጵያ ችግኝ ወላጅ አልባ ችግኝ (orphan) ነው ከተተከለ በሃላ ባለቤት የለውም :: የህንድ ችግኝ  ሃለፊነት የሚሰማው ወላጅና አሳደጊ  አለው፡፡ ታደያ ወላጅና አሳደጊ ያለው 63 ሚልዮን በቀን መትከል ይሻላል  ወይስ  ወላጅ አልባ ችግኝ (orphan )   350 ሚልዮን በቀን መትከል ? ፡፡ ህንዶች እንደ ሌ/ኮሎኔሉ  ቁጥር ላይ መጫወት ቢፈልጉ በህዝብ ብዛት ስሌት 48 ቢልዮን ችግኝ መትከል ይችላሉ፡፡ ስለሆነም ሌ/ኮ አብይ 350 ራሱ ከህንድ ከማወዳደሩ ይልቅ ከሌ/ኮ መንግሰቱ ቢያወዳድር በጣም ትክክል ይሆን ነበር ምክንያቱም  አካሄዱ ከሌ/ኮ  መንግሰቱ አረንጋዴ ዘመቻ ጋር አንድና አንድ ናቸው ፡፡

የህንድ ጠ/ሚ ቢሮ  ቁጭ ብሎ ለረጅም ጌዜ የሚሆን እቀድ አውጥቶ ነው የሚሰራው እንጂ ጊዜውን ስራ ሳይሆን ስራ የሚመስል ነገር በመስራት አያባክንም ፡፡ ህንድ በጣም የዳበረ ዴሞክራሲ ስርአት ከገነቡ አገራት አንድዋ ናት ፡፡ የአገሪቱ መሪ ብደግ ብሎ እንደ ሌ/ኮ አብይ በቢልዮን የሚቆጠር ዘፍ እንዲተከል  በስሜት ማዘዝ አይችልም ምክንያቱም ተጠያቂነት አለ፡፡  በሙያተኞች ግምት አንድ ችግኝ ለማፍላት ከ1ብር እሰከ ሁለት ብር  ውጪ ያወጣል ተብሏል ስለሆነም በአማካይ ለአሁኑ ዘመቻ 6 ቢልዮን ብር ወጪ ሆኖዋል ማለት ነው ፡፡ ለዚህ ድሀ አገር ታድያ ወላጅ አልባ(orphan) ችግኝ ለመትከል ይህ ሁሉ ብር ማፍሰስ ግፍ አይደለም ? ወይስ እንደ ተለመድው የውሸት ዶክመንተሪ ሰርቶ 4 ቢልዮን ችግኝ በሙሉ ፀድቃል ብሎ በሚድያ መግለፅ ነው ቀጥሎ ደግሞ ሌ/ኮሎኔሎ በሚድያ ቀርቦ እንኳን ደስ አለን ለማለት ነው፡፡

ህንድ ላይ  በዘመቻ ችግኝ መትከል አይቻልም ስለማይፀደቅ እንደ ኢ/ያ በቁጥር ሪኮርድ ለመስበር ከሆነ ግን 4 ቢልዮን ሳይሆን ከሌ/ኮ አብይ ቁጠር በላይ በብዙ እጥፍ  ችግኝ መትከል ይችላሉ ሆኖም የመንግሰት ገንዘብ፤ የህዘብ ጉልበትና ጊዜ  በዘመቻ መልክ ለማባከን   አይቸልም ምክንያቱም ተጠያቂነት አለ የውሸት ሪፖርትም የለም ፡፡ ለምን ቢባል ህንድ ያለው የህግ የበላይነት( rule of law)ኢ/ያ ውሰጥ ያለው የሰዎች የበላይነት(rule of men) ነው ምክንያቱም የትም አለም ሁሉም ስራዎች የስርአቱ ነፀብራቅ ናቸው ፡፡

በአጠቃላይ በአገራቸን ሁሉም ነገር በዘመቻ መፈፀም ትልቁ በሽታችን ነው፡፡ ከመሬት ተነስተህ አዕመሮህ ላይ የመጣልህ ሃሰብ  በአንድ ጀንበር እንዲፈፅም ትእዛዝ መሰጠት በሌ/ኮ አህመድ በእጅጉ የሚታይ ባህሪ ነው፡፡ ለቀጣይ አመትም 10 ቢልዮን ችግኝ እንተክላለን ተብለዋል ምን ችግር አለው ደግሞ  ወላጅ አልባ (orphan) ዛፍ ለመትከል፡፡

Full Website