Back to Front Page

የዝቅጠት ጉዞና  የቀውሱ ውጤት በብልሃት የማለፍ  አማራጭ መንገዶች

ሓጎስ ኣረጋይ (8/10/2011)

በኢትዮጵያ አሁን ለደረሰው ቀውስ  መሰረት የሚያደርገው  አንድ አገር፣ አንድ ህዝብ፣ አንድ ሃይማኖት ሲባል  የነበረና አሁኑም ያለ የገዢዎች አስተሳሰብ ነው።  መገለጫዎቹም

1. ዘመናዊ አስተሳሰብ አራምዳሎህ የሚለው  ሃይል ሳይቀር  ፣ እኛ የተረከብናት አገር ለተተኪው  ትውልድ እናስረክባለን ይላሉ። በዚህ አስተሳሰብ የምንመለከተው  ኢትዮጵያ ለዘር  የምትተላለፍ  የማይነካ እቃ  መሆንዋን ነው። በመሆኑ እነዚህ ሰዎች የወረስዋት አገር  ከነምናምንዋ ለተተኪው ሊያወርሱ  መዘጋጀታቸው   በግልፅ ያሳያል።

· ነገር ግን መሆን የነበረበት እና አሁንም ያለበት ኢትዮጵያ ለነዋሪዎችዋ  ምቹ  አገር እናደርጋለን ቢሉ   ሁሉንም የሚያስማማ ይመስለኛል። በመርህ ደረጃም ትክክል ነው።

2. በአገሪቱ  ውስጥ የአገሬው  ሰው የሚያራመድ  አስተሳሰብ   አፍራሽ/ገንጣይ  ነው ብሎ መፈረጅ ነው።  በመሆኑም በዚህ የአስተሳሰብ መጋረጃ ተወሽቀው  ወደ ውስጥ መመልከት  ያቅታችኋል። ይልቁንስ የኢትዮጵያን ዋነኛ የቀውስ ምክንያት  ብለው የሚፈርጁት በብሄር  መደራጀትን  ነው። ከዚህ በመነሳት   የጥላቻ ትርክታቸውን  ማላዘን  ያጎርፋሉ ። እንዲሁም  ከሆነላቸው በብሄር የተደራጁ ፓርቲዎችና  ቡድኖች ለማገድና ለማጥፋት ያሴራሉ ።ለምሳሌ  በብሄር የመደራጀት ጉዳይ  በህግ መታገድ አለበት በማለት  ያላዝናሉ። ለጦርነት  መዘጋጀት እና   የጦርነት ቅስቀሳን ያደርጋሉ ፣

· ነገር ግን  አሁን ኢትዮጵያ የምንላት አገር  በፈጣሪ  የተሰጠችና ነገም ሆነ ዛሪ  አይነኬ ዓይነት  አይደለችም።  አገሪቱ በሰዎች  የተሰራች መሆንዋ መገንዘብ ያሻል። በመሆኑም  ሲመቸን  አብረን የምንኖርባት ካልሆነ ግን  ትውልዱ  የሚመቸው አገር መመስረት  እንደ ሚችል ግንዛቤ  መውሰድ ያስፈልጋል። በአለም እየታዬ ያለው ሂደት ይህንን የሚያሳይ ነው።

3. በታሪካዊ ትርክት  የተተብትበ  አስተሳሰብ ይዞ ማህበረሰቡን መጤና  ነባር ባለ ይዞታ ብሎ  መክፋፈል ነው። በዚህ አስተሳሰብ  ተገፋፍቶ  ሁሉም የኔ  ነው በሚል ስሜት ያጉራራል።  በአጠቃላይ  ሲታይና ሲመዘን   በአንድ ወይም በሌላ መልኩ በጠቅላይነት አባዜ  የተወሸቀ አስተሳሰብ መሆኑን ያሳል።

· ነገር ግን በሁኑ ሰዓት ሰዎች ለሚኖሩበት አከባቢ  ባለቤቶች ናቸው ። ከማንም  ውል ገብተው የተረከቡት መሬት/ አካባቢ  የላቸውም። ጥርት ያሉ ባለቤቶች ናቸው ብለን ማመን ግድ ይላል።  በእርግጥ የይገባኛል  መርህ የምንከተል ከሆነ  እጠቅሳሎህ “ እዚያም  አለ ቁስል የኛ የሚመስል”  የሚለውንና  በግንቦት 20/2011 በጠቅላይ ሚኒስተር አቢይ መልእክት  መገንዘብ ያሻል ። ምክንያቱ አንዱ ብቻ ሳይሆን ሌላም ጠያቂ   እንዳለ ነው መረዳት ያለብን  ። ለምን ቢባል  ታሪክን ከወሰድን  እያንዳንዱ የየራሱ የሆነ ምክንያት ይኖረዋል ።

በአጠቃላይ  እየታዬ ያለው ነውጥ

· የጥላቻና የውሸት ፖለቲካ

· የታሪክ ተቃርኖ

· ለብሄር ብሄረ ሰቦች  እስከመገንጠል  ያለው መብት አለመስጠት እና  እውቅና  አለመቸር። እንዲያውም የብሄር ብሄረ ሰቦች ጥያቄ የመደፍጠጥ  አዝማምያ ይታያል።

· ገዢ ፓርቲዎች  በየክልላቸው  ራሳቸውን ወደ ገዢ መደብ  የመቀየር  አዝማምያ እና የመሳሰሉት  ትልቅ አስተዋኦ አድርገዋል

ከላይ በተጠቀሱት የመርህ መዛነፍ  ያስከተላቸው  ልዩነቶች  ዜጎች  ተሰቃይተዋል፣   በግፍ ተፈናቅለዋል፣ ታርዘዋል፣ ህይወታቸው በግፍ አጥተዋል፣  የኢትዮጵያዊነት ስሜት ተሸርሽረዋል። በአሁኑ ሰአት በነዚህና በሌሎች ችግሮች  ምክንያት  በፓርቲዎች መካከል  ብቻ ሳይሆን   በብሄር ደረጃ  አንደኛው  ለሌላኛው  በጥርጣሪ  የመመልከት  አባዜ  አንግሰዋል ማለት ይቻላል ።

መፍትሄ፥

ሁሉም  ወገኖች  ጠንካራና ደካማ ጎኖች ሊኖርዋቸው ይችላሉ ። ነገር ግን የልጅ ጨዋታ ባለመሆኑ ጥንቃቄ በተሞላበት መፍትሄ ማስቀመጥ ያሻል።  ለምን ቢባል የፖለቲካ  ቃል ይታጠፋል። ምክንያቱም  በፖለቲካ  አለም  ቋሚ ወዳጅም ሆነ ጠላት የለም። ስለዚህ  በፖለቲካ የተተበተበ ችግር ፖለቲካዊ መፍትሄ ያሸዋል።  በመሆኑም  ወደድንም ጠላንም  ሁለት ነገር ግን ዘላቂ መፍትሄ ከፊታችን ተደቅነዋል፣ እነሱም፣

1) ኢትዮጵያን በልል ኮንፌዴሬሽን ማዋቀር ። ከዚያ በኢኮኖሚ ፣ በማህበራዊ  እና በፖለቲካ መስተጋብር በብሄሮች ያለው ያለመተማመን  የሚሽርበት መንገድ መሻት።    በሂደቱም  ማህበረ ሰቡ  የውሸት ትርክት  እየተረዱ  ይሄዳሉ። በዚህ ሂደት ከተጓዝን  የተቀደሰ ጋብቻ ልንለው እንችላለን

ወይም

2) በሰላም  እንደ  ሶብዬት ህብረት መለያዬት  ያስፈልጋል።  ከዚያ በኋላ ስለ መልካም ጉርብትና  ማሰብና በጤናማ ጉርብትና  ደግሞ  የማህበረሰቦቻችን  ግንኙነት ማጠናከር።

እዚህ ላይ  ኤርትራ  ምን አገኘች  ፣ እንዲሁም በአለም መድረክ ላይ  ተሰሚነትም አይኖረንም  የሚሉ ሰዎች  አሉ። ይህ አስተሳሰብ በጣም የተሳሰተ ነው። ምክንያቱ ሌላ አማራጭ እንዳልለ ማዬት ያስፈልጋል ። ጠንክረን ከሰራንና ሰላም ካገኘን  ቁጥራችን ትንሽ ቢሆንም በስራችን ትልቅ እንሆናለን።  በአለም  ውስጥ እየሆነ ያለው ይሄው ነው  ። ለምሳሌ ኖርወይ፣ ቤልጄም ፣ ቦትስዋና ወዘተ  እንውሰድ። አግሮቹ  እርዳታ ይሰጣሉ እንጂ እርዳታ ተቀባይ አገራት አይደሉም። እኛ ግን የነዚህን አገራት (ከአምስት ሚልዮን የማይበልጥ ህዝባቸው)  ስንዴ ተመፅዋች ነን ።ስለዚህ    የየራሳችን ነፃ መንግስት አቋቁመን  የተመቸ አገር መመስረት እንችላለን ማለት ነው።

Full Website