ወደ ብልፅግና ፓርቲ የተቀላቀለ ወይስ ራሱን ያገለለ ተጠቀመ?

ህዳሴ ኢትዮጵያ ሕዳር 23፣ 2012 ዓ.ም.

ብልፅግና ፓርቲ የመሰረቱት 3ቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች እና 5ቱ አጋር ድርጅቶች ህልውናቸው ስለሚያበቃ በያንዳንዱ ክልል የሚኖረው ገዢ ፓርቲ ኢህአዴግ ወይም አጋር ድርጅት ሳይሆን የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ነው፡፡

ይህም የኢትዮጵያ ብልፅግና ፓርቲ በነዚህ ክልሎች የኢህአዴግ እህት እና አጋር ድርጅቶች ሃላፊነት በመረከብ ክልሎችን ይመራል ማለት ነው፡፡ የዚህ ፓርቲ ድምፅ አሰጣጥ ኦሮሚያ 34% ኣማራ 28%፣ ደቡብ 12%፣ ሱማሌ 6.6%፣ አፋር 5%፣ ቤንሻንጉል ጉምዝ 3%፣ ጋምቤላ 3%፣ ሐረሪ 3% አላቸው፡፡ ስለዚህ የአገር ጉዳይ ይሁን የክልል ጉዳይ ተነስቶ መግባባት ካልተደረሰ በዚህ ድምፅ አሰጣጥ መሰረት በአብላጫ ድምፅ ይወሰነል፡፡

በእርግጥ ባለፉት 27 ዓመታት በኢህአዴግ የስልጣን ዘመን ጠቅላይ ሚኒስተር የመሆን ዕድሉ ለአራቱ የኢህአዴግ እህት ድርጅቶች ብቻ እያንዳንዳቸ 25% ዕድል የተሰጠ ሲሆን አጋር ድርጅቶች ግን ጠ/ሚኒስተር የመሆን ዕድላቸው 0% ነበር ማለት ይቻላል፡፡ የኢህአዴግ እህት ድርጅቶችም የኢህአዴግ አጋር ድርጅቶችም በሙሉ የራሳቸው ጉዳይ በራሳቸው የመወሰን፣ ክልላቸው የመምራት ዕድለሉ ግን ሙሉ በሙሉ ወይም 100% የየራሳቸው ነበር፡፡

ከዚህ ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት 5ቱ የኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች፣ ባለፉት 27 ዓመታት ከኛ ጠ/ሚ የመሆን ዕድሉ ዜሮ ነበር ስለዚህ በጣም ተበድለናል፣ እንደ ዜጎች

አልተቆጠርንም፣ አሁን በብልፅግና ፓርቲ ጠ/ሚ የመሆን ዕድል ከ3% እስከ 6.6% በመሆኑ ወደ ብልፅግና ፓርቲ እንዋሀዳለን በማለት ተቀላቀሉ፡፡

ታድያ አሁን ተጠቀሙ ወይስ ተጎዱ?

መልሱ በሬሆይ ሳሩን እንጂ ገደሉን ሳታይ እንደሚባለው እስከ 6.6% የጠ/ሚነት ዕድል ለማግኘት ከ93.4% በላይ ራሳቸው በራሳቸው የመወሰን ዕድል አጡ እንጂ ምንም ጥቅም አላገኙም፡፡ የያንዳንዱ ክልል ጥቅም እና ጉዳት ሲታይ፡- ሶማሌ ክልል በኢህአዴግ ጊዜ ጠ/ሚ የመሆን ዕድሉ 0% ሲሆን ራስን በራስ የመወሰን ዕድል ግን 100% ነበረው፡፡ ወደ ብልፅግና ፓርቲ ከተቀላቀለ ግን ጠ/ሚ የመሆንም ክልሉ ራሱን በራሱ የመምራትም ዕድል ያለው 6.6% ብቻ ነው፡፡  ከዚህ መረዳት የሚቻለው የሶማሌ ክልል በሶዴፓ መሪነት 6.6% የጠ/ሚ ነት ዕድል ለማግኘት ብሎ 93.4% ክልሉን የመምራት ዕድል አጣ፡፡  አፋር ክልል በኢህአዴግ ጊዜ ጠ/ሚ የመሆን ዕድሉ 0% ሲሆን ራስን በራስ የመወሰን ዕድል ግን 100% የነበረው፡፡ ወደ ብልፅግና ፓርቲ ከተቀላቀለ ግን ጠ/ሚ የመሆንም ክልሉ ራሱን በራሱ የመምራትም ዕድል ያለው 5% ብቻ ነው፡፡  ከዚህ መረዳት የሚቻለው የአፋር ክልል በአብዴፓ መሪነት 5% የጠ/ሚ ነት ዕድል ለማግኘት ብሎ 95% ክልሉን የመምራት ዕድል አጣ፡፡

ቤንሻንጉል ጉምዝ፣ ጋምቤላ፣ እና ሐረሪ ክልሎች በኢህአዴግ ጊዜ ጠ/ሚ የመሆን ዕድላቸው 0% ሲሆን ራስን በራስ የመወሰን ዕድል ግን 100% ነበራቸው፡፡ ወደ ብልፅግና ፓርቲ ከተቀላቀሉ ግን ጠ/ሚ የመሆንም ክልሉ ራስን በራስ የመምራትም ዕድል እያንዳንዳቸው 3% ብቻ አላቸው፡፡  ከዚህ መረዳት የሚቻለው የክልሉ አመራር 3% የጠ/ሚ ነት ዕድል ለማግኘት ብሎ 97% ክልሉን የመምራት ዕድል አጣ፡፡  ደቡብ ክልል በኢህአዴግ ጊዜ ጠ/ሚ የመሆን ዕድሉ 25% ሲሆን ራስን በራስ የመወሰን ዕድል ግን 100% ነበረው፡፡ ወደ ብልፅግና ፓርቲ ከተቀላቀለ ግን ጠ / ሚ የመሆንም ክልሉ ራሱን በራሱ የመምራትም ዕድል ያለው 12 % ብቻ ነው፡፡ ከዚህ መረዳት የሚቻለው የክልሉ አመራር በዚህ አሳፋሪ ውሳኔው 13% የጠ/ሚ ነት ዕድል ሲያጣ በተጨማሪ 88% ክልሉን የመምራት ዕድል አጣ፡፡ ደቡብ ከብልፅግና ፓርቲ ያገኘው ምንም ጥቅም የለም ሙሉ በbሙሉ ጉዳት ብቻ ነው፡፡ ይህ ለፅድቅ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡

አማራ ክልል በኢህአዴግ ጊዜ ጠ/ሚ የመሆን ዕድሉ 25% ሲሆን ራስን በራስ የመወሰን ዕድል ግን 100% ነበረው፡፡ ወደ ብልፅግና ፓርቲ ከተቀላቀለ ግን ጠ/ሚ የመሆንም ክልሉ ራሱን በራሱ የመምራትም ዕድል ያለው 28% ብቻ ነው፡፡  ከዚህ መረዳት የሚቻለው የክልሉ አመራር 28% የጠ/ሚ ነት ዕድል ለማግኘት /የነበረውን ዕድል በ3% ለማሳደግ/ ብሎ 72% ክልሉን የመምራት ዕድል አጣ፡፡

ኦሮሚያ ክልል በኢህአዴግ ጊዜ ጠ/ሚ የመሆን ዕድሉ 25% ሲሆን ራስን በራስ የመወሰን ዕድል ግን 100% ነበረው፡፡ ወደ ብልፅግና ፓርቲ ከተቀላቀለ ግን ጠ/ሚ የመሆንም ክልሉ ራሱን በራሱ የመምራትም ዕድል ያለው 34% ብቻ ነው፡፡  ከዚህ መረዳት የሚቻለው የክልሉ አመራር 34% የጠ/ሚ ነት ዕድል ለማግኘት /የነበረውን ዕድል በ9% ለማሳደግ/ ብሎ 66% ክልሉን የመምራት ዕድል አጣ፡፡  ትግራይ ክልል በኢህአዴግ ጊዜ ጠ/ሚ የመሆን ዕድሉ 25% ሲሆን ራስን በራስ የመወሰን ዕድል ግን 100% ነበረው፡፡ ከብልፅግና ፓርቲ ራሱን በማግለሉ ግን ጠ/ሚ የመሆንም ዕድሉ 0% ሲሆን ክልሉ ራሱን በራሱ የመምራትም ዕድል ያለው ግን 100% ይሆናል፡፡  ከዚህ መረዳት የሚቻለው የክልሉ አመራር 25% የጠ/ሚ ነት ዕድል በማጣት /መስዋእት በመክፈል/ የነበረውን የራሱን ክልል በራሱ የማስተዳደር ዕድል 100% እንዲሆን አድርጓል፡፡

ብልፅግና ፓርቲ የተቀላቀሉ ወይስ ራሳቸውን ያገለሉ ተጠቀሙ?

ወደ ብልፅግና ፓርቲ ከተቀላቀሉትስ፣ የተጠቀመ የቱ ክልል ነው? የተጎዳስ የቱ ክልል ነው? ለነገሩ ይህን ስሌት ማስላት የማይችል ተስፈኛ የአጋር ድርጅት አመራር የጠ / ሚነት ዕድል ቢሰጣቸውም በምንም ተኣምር ጠ / ሚ ሊሆኑ አይችሉም ምክንያቱ በብልፅግና ፓርቲ የተሰባሰቡ ግለሰቦች ሁሉም ስልጣን ስለአሰባሰባቸው ፣ የኢትዮጵያ ጠ / ሚ የሚሁኑት በርካታ ድምፅ /34% እና 28% ያላቸው / ኦሮሚያና አማራ በመስማማት እየተፈራረቁ ለዘልአለሙ ይይዙታል ፡፡

ስለዚህ አጋር ድርጅቶች ምንም እንኳ ከ 3% እስከ 6.6% ዕድል ቢሰጣውም ይህ ዕድል አሸናፊ የሚሆንበት ዕድል 0% ነው፡፡ ስለዚህ በኢህአዴግ ጊዜ የነበራቸው የጠ / ሚ የመሆን ዕድል እና በብልፅግና ፓርቲ ያላቸው ጠ / ሚ የመሆን ዕድል በተጨባጭ አንድ እና ያው ነው፡፡ ነገር ግን በኢህአዴግ ጊዜ የነበራቸው ራስን በራስ የማስተዳደር፣ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ስልጣናቸው ግን አሳልፈው ስለሚሰጡ አጋር ድ ርጅቶች በብልፅግና ፓርቲ አባል መሆናቸው ትልቅ ጉዳት እንጂ ቅንጣት ጥቅም የላቸውም፡፡

የደኢህዴን ጉዳይ ከሁሉም የባሰ ጉዳት ነው፡፡ ምክንያቱ ጠቅላይ ሚኒስተርነት የመሆን ዕድሉ በ13% ሲያጣ ክልሉን ራሱ በራሱ የማስተዳደር ዕድሉም ቢሆን በ88% ቀንሰዋል፡፡ ስለዚ ሌሎች ክልሎች አንዱን ዕድል ለማግኘት ለላውን ዕድል ሲያጡ ደቡቦች ግን በሁሉም ዕድሎች ተጎጂዎች ሆኖዋል፡፡

Full Website