መግቢያ

ከገራገር ዘበርጋ /14/09/2011 ዓ.ም/

አንባቢያን ይህንን ፅሑፍ ለማዘጋጀት የተገደድኩበት ዋናው ምክንያት ባሁኑ ወቅት ባገራችን የፖለቲካና የፍትሕ ሂደት ውስጥ የማይገናኘውን ክስተት ምንም ከማይቀራረበው እውነታ በማዛመድ፡ መጠየቅ ያለበትን ወደ ጎን በመተው ወይም በመሸለምና በመሾም ሌላውን ወገን ግን ተጠያቂ ለማድረግ ብዙ ሽርጉድና ሸፍጥ የሚሰራበት ፖለቲካና የፍትሕ ሂደት ተብየው ድራማ እየተፈጸመ ‹‹እኔን አይመለከተኝም!›› በማለት በዝምታ ማለፉ ሕሊናን የሚቆረቁር በመሆኑ በመሬት ላይ ያለውን እውነታ ከሕግና ከፍሬነገሩ ጋር በማዛመድ ትክክለኛውን ስእል ሕዝቡ እንዲያውቀው ለማድረግ ነው፡፡

የፀረ ሽብር ጉዳይ

በመስከረም 2001 ዓ.ም በኒውዮርክ ከተማ በነበሩት ሁለት መንትየ ሕንጻዎች ላይ አሸባሪዎች አውሮፕላኖችን ጠልፈው ከሕንጻዎቹ ጋር በማላተም በውስጡ የነበሩት ሰዎች እንዲያልቁና ሕንጻዎቹም አንዲፈራርሱ ካደረጉ በኃላ ኃያሏ አሜሪካ ተደፈርኩ ብላ ጡንቻዋን ለማሳየት ሰብብ ፈጥራ ኢራቅን ወርራ የሳዳም ሑሴን መንግስትን ያፈራረሰች ሲሆን ከዚያ በመቀጠልም አሸባሪዎች በአፍጋኒስታን፡ በኢራቅ፡ በሰሜን ሳሄል አገሮች፡ በናይጀሪያ፡ በሶማሊያ ወዘተ… አገራት የሽብር ጥቃታቸውን እያስፋፉ እንደመጡ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ የዓለም አገራት አሻባሪዎችን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የሚያስችላቸውን ሕግ በየጊዜው ሲያውጁና ተግባራዊ ሲያደርጉ ተስተውሏል፡፡ ኢትዮጵያም ብትሆን የሽብር ሰለባ ከመሆን የተረፈችበት ጊዜ ስላልነበረ ጉዳዩ ስታስጠናና የሌሎች አገሮች ልምድንም ስትቀምር ከቆየች በኃላ በ2001 ዓ.ም ነሐሴ ወር ላይ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አውጥታ አሸባሪ ብላ የፈረጀቻቸውን አካላትና ግለሰቦችን ስትከታተልና ለፍርድ ስታቀርብ ከርማለች፡፡ ይህ አዋጅ እስካሁን ድረስ በስራ ላይ ያለ ሲሆን በቅርብ ቀናት ሌላ ማሻሻያ የተደረገበት አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ለመጽደቅ በሂደት ላይ እንዳለ ይነገራል፡፡ በዚህ አዋጅ መግቢያ ላይ እንደተገለጸው ‹‹… የአገሪቱ ሕዝቦች ደህንነትና ያገሪቱ ጥቅም ከማንኛውንም የሽብር አደጋ መጠበቅና መከላከል በማስፈለጉ፡ አገሪቱ አሸባሪ ብላ የሰየመቻቸው አካላትን ተጠርጣሪ ግለሰቦች በማስረጃና በመረጃ አስደግፎ ለሕግ ማቅረብ እንደሚያስፈልግና ለዚሁም ጠንካራ የሕግ ማእቀፍ ማውጣትና ማደራጀት አስላጊ ሆኖ በመገኘቱ፡ አገሪቱ የአህጉራዊና የዓለም አቀፍ ግዴታዎቿን ለመወጣት ሽብርተኝነትን መከላከልና ግዴታዋን መወጣት እንዳለባት ግንዛቤ ተወስዶ ሕጉ እንደወጣ …›› ይደነግጋል፡፡

ከዚያም በመቀጠል በዝርዝር አዋጁ ላይ ሽብርተኝነት ማለት ምን እንደሆነ፡ በሽብርተኝነት የሚጠረጠር አካል ወይም ቡድን ወይም ግለሰብ ምን ዓይነት ድርጊት የፈጸመ ወይም ሊፈጽም ያሴረ እንደሆነ ወዘተ… የሚያብራሩ በርካታ አንቀጾች ያሉት ሲሆኑ፡ ይህንን ጉዳይ የሚያስፈጽሙና የሚከታተሉት አካላትና ሰራተኞችም እነማን እንደሆኑ በአንቀጽ 28፡ 29 እና 30 ላይ በግልጽ ሰፍሯል፡፡ ግርታን ላለመፍጠርና ሌላ ትርጉምም ላለመስጠት አንቀጾቹን እንዳሉ ኮፒ ፔስት አድርገን አቅርበነዋል፡፡ ከዚያም አንባቢ በማያሻማ ሁኔታ በፀረ ሽብርተኝነት የሚሳተፉት አካላትና አባላት እነማን እንደሆኑ ለመለየትና ኃላፊነትን ከባለስልጣንና ከግለሰብ ጋር አጣብቆ ፍርድ ለመስጠት ይመቸዋል፡፡
አንቀጽ 28 በግልጽ እንዳሰፈረው በፀረ ሽብርተኝነት ጉዳዮች ላይ የሚሳተፍ ፖሊስም ይሁን ዓቃቤ ሕግ በክፍሉ ኃላፊዎች ዘንድ ስለታታሪነቱና ብቃቱ የተመሰከረለትና በቂ የስራ ልምድ ያለውና በስራው ስልጠና የወሰደ መሆን እንዳለበት የተጠቀሰ ሲሆን ሁለቱም አካላት ማለትም ፍትሕ ሚኒስቴርና ፌዴራል ፖሊስ የሽብርተኝነትን ጉዳዮች የሚከታተሉ የስራ ክፍሎችን እንደሚያደራጁ:

‹‹28. የሽብርተኝነት ድርጊትን ስለሚከታተል ዐቃቤ ሕግና ፖሊስ

1/ በሕግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት

የሽብርተኝነት የወንጀል ጉዳይን የሚከታተል ዐቃቤ ሕግ ወይም ፖሊስ፡-

Full Website