ኢትዮጵያውያን ሆይ ዝም ዝም መፍትሔ አይደለም!

ኡስማን ሙሉዓለም

ከሓራ ገበያ

6-10-19

አሁን ስልጣን ላይ የተቆናጠጠው ቡዱን የህዝብን ጥያቄ ለስልጣን ጥማቱ ቀይሮ ነው የወጣ፡፡ ወደ ስልጣን ካርቻ ለመወጣት ለእርካብነት የሚጠቅሙትን  ጥያቄዎች ለወጣቱ አስጨብጦና የትግሉን ስልት ነውጥና ሁለገብ ብሎ ነው ያወጀው፡፡ለዚህም ደግሞ ከለየላቸው ሽብርተኞችና ፀረ-ሰላም ሓይሎች በድብቅ ሕብረት ፈጥሮ ተንቀሳቅሳል፡፡ የለማ ቡድናዊ ሃይል (ቲም) መንበረ ስልጣን ለመቆጣጠር መጀመርያ በኦህዴድ ማእከላይ ኮሚቴ ውስጥ ኩዴታ አድርጎ ቁንጮ ቦታ ላይ ወጣ፡፡ በኃላም በኢህወዴግ ተመሳሳይ ኩዴታ አደረገ። ለዚህም እንዲረዳው በውጭ ኦሮማራ ብሎ አደራጀ፡፡  በኢህአዴግ ውስጥ ደግሞ በስድስት ኪሎ የኦህዴድ ፅ/ቤት መጀመርያ በኦህዴድና በብአዴን አመራር ተከታታይ ስብሰባ ተደረገ።በጥቂት አመራር መካከል የተደረገ ምስጥራዊ ስብሰባ መሆኑ ነው።በኃላደግሞ በጴጥሮሱ ሃ/ማርያም አማካኝነት ደህዴንም በብሄር በመከፋፈልና ሌላም የጥቅም ድለላ ስልቶች በመጠቀም የስድስት ኪሎው ድብቅ ማህበር አባል እንዲሆን ተደረገ።በዚህ ተዘጋጅተው ያለቀለት ጉዳይ በኢህአድግ የምርጫ ትያትር ተደርጎ ቲም ለማ ስልጣን ተቆጣጠረ።

እነሆ ከዛቺ ሰአት ጀምሮ ኢህአዴግ በሁለት መተርተሩን ገሃድ ሆነ።በሁለት የመተርተሩ መገለጫዎች ብዙ ናቸው። በምርጫው ምሽት መተርተሩን ሦስት ለአንድ በሆነ ሁኔታ ለመጀመርያ ግዜ በግልፅ ፍንትው ብሎ ወጣ።ወያኔና ጥቂት ከሌሎች ፓርቲ አመራር አባለት የተሰባሰቡበት አንድ ሲሆን ሦስቱ ደግሞ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደህዴን ተብሎ መግለፅ ይቻላል።በነገራችን ላይ በረከት ስምኦንን ለእስር የዳረገው በዚህ ምሽት ያደረገው ታሪካዊ ንግግር /ትንቢት/ መሆኑ ይታወቃል፡፡  ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ‘የተደመረና ያልተደመረ’በሚል ኢህአዴግ መተርተሩን በግልፅ የሚገልፅ መግለጫ በመሰጠቱ ነበር።ቀጥሎም በሀዋሳው ጉባኤ የኢህአዴግ ፕሮግራምና ህገመንግስቱና ፌደራል ስርአቱ ደጋፊና መለወጥ አለበት በሚሉ ሁለት አይዶሎጂና መስመሮችኢህአዴግ ውስጥ መተርተር እንደተፈጠረ በግልፅ ወጣ።ነገር ግን ወቅቱ አይደለም በሚል የለማ ቲም  ነገሩን አድበስብሶና ሸፋፍኖ አለፈው፡፡ ባያልፈው ኖሮያኔ ሁኔታው ፈርጦ መልክ በያዘ ነበር። መተርተሩ ቀጠለና ኦህዴድ ህዝባዊነቱን አሽቀኝጥሮ ጥሎ ኦዴፓ ነኝ አለ።ብአዴንም አዴፓ ብሎ ስም ቀየረ። እንደኔ አተያይ ደግ አደረጉ ነው የሚለው።ህዝባዊነት ከጣሉትኮ ቆይተዋል።ህዝበኞች እንጂ መቼ ህዝባዊያን ቆዩና።ድሮ የተውት! እንኳን ህዝቡን አባላቸውንም ከጠሉትኮ ቆይተዋል።አብዮታዊ ዲሞክራሲ እያለ የሙጥኝ የሚል ካድሪያቸውን የምር ጠልተውት ነበር። ሁለቱም ስማቸውን የቀየሩ ኢህአዴግ ግንባር ውስጥ ያሉ ኢህአዴግን የሚጠሉ ድርጅቶች ነባር አባላቸውን የለውጥ ዕንቅፋት አድርገው ቆጥረው በሱ ትሩፋት ፀዳያለ ልብስ የለበሰ ሞላጫና አሰመሳይ፣በንግግሩ እንግሊዝኛን ጣል የሚያደርግ፣ ከስራና ትግል ይልቅ ንግግር የሚያሳምር፣ከህግ ውጭ የሚሰራና በተለይ ደግሞ ወያኔን የሚያጥላላ ዲስኩር የሚያሰሙ አሻቅባጮች እንደምርጥ የለውጥ ሃዋርያ ማየት ጀመሩ፡፡በመጨረሻ ደግሞ አምና መጋቢት የፈረሰውን ኢህአዴግን ዘንድሮ መጋቢት አፍርሰን አንድ ወጥ ፓርቲ እንመስርት በሚሉና መጀመርያ በአይዶሎጂና በፕሮግራም አንድ እንሁን ወደ አንድ ፓርቲ ከመጠቃለላችን በፊት በሚሉ ሁለት ሐሳቦች ላይ ሳይስማሙ ተተረተረ።

አገሪቱ በዚህ ሂደት ከጊዜ ጊዜ እየፈራረሰች በለችበት ወቅት ሁሉም ዝም ዝም ሆነ። ዋናው ችግሩ ዝም ያልኩት የተፈጠረ ነገር የለም ብሎ ለውጥ አመጣሁ የሚለው ሐይል በመካዱ ነው። ሌላው ሃይል ደግሞ መጀመርያ ላይ ለተፈጠረው ሁሉ ተጠያቂ ይደረግ ስለነበረ ምንም ማድረግ እንኳን የማይችል የነበረ ቢሆንም የኃላ ኃላ ግን እስቲ አንደጀመሩት ይወጡት እያለ ዝም ዝም ያለ ይመስላል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ምን ትመስላለች?

አገራችን ያለችበት ሁኔታ በወራት፣ በሳምንታትና በቀናት ቀርቶ በሰዓታትትና በደቂቃዎች የሚቀያየሩበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ህዝባችን የለመደው ሰላም ደፍርሰቦታል፡፡ ወጥቶ ስለመመለሱ እርግጠኛ አየደለም፡፡ ወንጀል፣ ዝርፍያ፣የፆታ ትንኮሳና ግድያ በሁሉም የአገሪቱ ክፍል መገለጫ ሆኗል።መንግስት በመንግስትነት መስፈርት ወድቋል።የጎበዝ አለቃ የሚያስተዳድራት አገር ሆናለች። የመንግስት መዋቅር በቀበሌ፣በወረዳ፣በክልልናበፌድራል ፈራርሷል።ያልፈረሰውም ሽባ ሆኗል።አይወስንም።አዲስ አበባም ሳይቀርወንጀል ተፈፀመብኝ ብለህ ብትጮህ ፖሊስ አይደርስልህም።ስርዓቱ ቀድሞ ለወንጀሎቹ ይቆማል፡፡ ስለዚህ ራሳቹህ ተደራጅታቹህ ተወጡት እያለ ፖሊስ መልስ የሚሰጥበትአገር ሁናለች።ከአራት ኪሎ ቤተመንግስት በስተቀር ሰላም የለም።መንግስትም የለም። ሰለዚህ በተጨባጭ አገራችን መንግስት አልባ አገር ሆናለች።

በኢኮኖሚ ጉዳይም ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ ከቀን ወደ ቀን እያሻቀበ በመሄድ ላይ ያለው የዋጋ ንረት ከህብረተሰቡ ገቢ ጋር መመጣጠን አቅቶትኑሮ ውድነት ህዝቡን ክፉኛ እያጠቃው ነው።የሚበላና የሚጠጣ አጥቶ ረሃብ የጀመረው ህብረተሰብ ክፍል በከተሞችም ሳይቀር እየተበረከተ ነው።ይህም ተመልሶ ለወንጀልና ዝርፍያ መንስኤ እየሆነ ይገኛል።ስራ ላይ መቀዛቀዝ በመፈጠሩም ቀደም ባሉ ጊዚያት በበጎ ዘመን የቆጠበውን ገንዘብና ንብረት እየሸጠም አስካሁን ኑሮውን የሚገፋ ህዝብ በሚልዮኖች ይቆጠራል።ተሎ መፍትሄ ካልተገኘ ወይም ካልመጣ ዝም ዝም ከተባለ ይህም የቆጠበውን ተጠቅሞ ሲጨርስ ፈጥኖ ወደ መራብ የጀመሩት ህብረተሰብ ክፍሎች የሚቀላቀልበት ጊዜ አጭር ነው።ከሃይል አቅርቦት ጀምሮ እስከ ውጭ ምንዛሬ በወረፋና በፈረቃ የሆነበት አገር በከፍተኛ ካፒታል የተሰሩ ፋብሪካዎች ምርት የማምረት ሂደት እየተስተጋጎለ ችግር ላይ ወድቀዋል።መካከለኛ፣ አነስተኛና ጥቃቅን ስራ ላይ የተሰማሩትም ስራ የሚፈቱበት ጊዜ ከሚሰሩበት እየበለጠ ተከራይተው ለሚሰሩበት ቦታና ቤት መክፈል እየተቸገሩ ናቸው።በኮንስትራክሽን እንዱስትሪውም አብዛኛዎቹ በዘርፉ የተሰማሩት ድርጅቶች ከዚህ በፊት ለመንግስት ፕሮጄክቶች ለሰሩት በመቶ ቢሊዮኖች ያልተከፈላቸው ብር በመኖሩ መንቀሳቀስ የማይችሉበት ሁኔታ እየተፈጠረ ነው። በአጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ ልማት የለም።ድህነት እያጣ የመጣውን ቦታ በፍጥነት እየመለሰ ነው። ድህነትም አሰመላሽ ኮሚቴ አቋቁሞ ይዞታውን በፍጥነት እያስመለሰ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡

ብሄር ተኮር ጥቃት በዚህ አገር በስፋት እየታየ ያለው ሌላው ምስላችን ነው።የፈረሰው ኢህአዴግ መሪዎች የሚመሩት የብሄር ተኮር ጥቃት በመሆኑ ደግሞ እጅግ አሰከፊ አድርጎታል፡፡ የብዙ ንፁኋን ህይወት እየቀጠፈና ለአራት ሚልዮን የሚሆኑ ህዝቦች ደግሞ መፈናቀል ምክንያት ሆኖ እያለ ዝም ዝም የሚባልበትና በውጭ ሚድያ ሲጋለጥ ደግሞ ነበር ግን ተቆጣጥረንዋልተብሎ መልስ የሚሰጥበት ነው፡፡ ራሳቸው ጥቃት ፈፃሚዎቹ መሪዎቹእንዲገናኙ ተደርጎ ታረቁ፣ ችግሩ ተፈታ ተብሎ ዳንኬራ ይመታል። በተጨማሪ ደግሞ ችግሩ ለማድበስበስ ሌላ ሰበር ዜና በመፍጠር እንዲረሳ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው።የሶማሊው፣ የኦሮሚያና የቅማንት ጭፍጨፋ አስረስተው እንደ አዲስ ወለጋ ላይ በኮማንድ ፖስት ተብዬ ጆኖሳይድ ይፈፅማሉ።ይህ ዝም ሲባል አማራንና ቤንሻንጉልን ህዝቦች አጣልተው ቤንሻጉል ህዝብን በጅምላ ይጨፈጭፋሉ። በቅማንት ህዝብ ጆኖሳይድ በፈፀሙት በደም በጨቀየው እጃቸው ቤንሻንጉል ላይ ይደግሙታል።ጠያቂ የለም።ዝም ብለው ህዝቦችን ዝም ለማሰኘት ሲፈፅሙት ተግባሩያልዘገነናቸው ጆኖሳይድና ጅምላ ጭፍጨፋ ቃላቶች እንዳይባሉ አታጋግሉት ተጨማሪ መጨፋጨፍ ይፈጠራል ብለው ይመክራሉ።ራሳቸው እንተርሀሞዬዎቹ።ቤንሻንጉል ጭፍጨፋ ሲፈፀም ሳይሄዱ በሳውዲአረብያና በኢሜሬትስ እንዲሁም በግብፅ የሚደገፈው የሱዳን ጊዚያዊ ወታደራዊ መንግስት ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ገደለ ተብሎ ለማስታረቅ የኛው መሪ ተብዬ ኮ/ል አብዬ ዘለው ሄዱ ተባሉ።የሱዳኑ ዝም ዝም እንዳይሉ ያንገበገባቸው ምን ይሆን? ሀገራችን በብሄር ተኮር ጥቃት እየታመሰች ቆይታ በግልፅም በአደባባይ ዘረኛ የሆኑ ሚድያዎች ተው የሚላቸው ሳይሆን ቀጥሉበት የሚል መሪ የታደለች ሀገር ሁኔታው ከመቀነስ ይልቅ እየተባባሰ እየሄደ ነው።ቄሶች በመድረክበህዝቦች መካከል ስላም ስለሰበኩ ወላዋዮች አትሁኑ የሚል መሪ ያላት ሀገር ዝም ቢል ምን ነውር አለው?አሁን ደግሞ ትምህርት ቤቶች በተለይም ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እየተስፋፋ ነው።ሰላም ስለሌ ምርጫ ማካሄድ አይቻልም የሚል ምክንያት ለማጠናከር በሚመስልየፌደራል ስልጣን የተቆጣጠረው ራሱን ቲም ለማ ብሎ የሰየመ ቡዱን ሃላፊነቱ መወጣት አቅቶት ዝም ዝም ብሏል።

በማጠቃለል ሀገራችን ኢትዮጵያ ቀጣይ ዕጣ ፋንታ ግልፅ ያልሆነ ሁኔታ ላይ ትገኛለች።የሰላም ዕጦት ቀውስ፣የኢኮኒሚ ቀውስ፣ሰብኣዊ ቀውስ እና መጨረሻው የሀገር ህልውና አደጋ ላይ መውደቅ ቀውስ ላይ ገብተናል።ብርሃኑንና ያለፈውን ሃያሰባት ዓመት ጨለማ ያሉት ሰዎች ወደ ጨለማ እየወሰዱን ነው።በፍጥነት። ወደ ጥፋት የምናደርገው የጉዞ ፍጥነት ሁኔታ መሪ የሌላት አውቶብስ የገደል ቁልቁለት ላይ ስትጣደፍ ወንበርህ ላይ ቁጭ ብለህ የሚሆነውን ለማየት ባለመፈለግ አይንን ጨፍኖ ዝም እንደማለት ይቆጠራል።ዝም ማለት በአሁኑ ወቅት ጥፋት እንጂ ትዕግስት አይደለም።ዝም ማለት ከደሙ ንፁህ ነኝ ለማለትም አይበጅም።ራስንም ማዳን አይቻልም።ለብቻም መፍትሄ አይሆንም።

ሰለዚህ አገራችን ከተጋረጠችበት አደጋ ለመታደግ በጋራ እምቢ እንበል! ገደል እያየንማ ዝም ዝም ብለን አንገባም እንበል፣አገራችን ፍርስርስ ስትል አናይም እንበል፣ አገራችንም የህዝቦቻችን ሉዓላዊነት መገለጫ የሆነውን ህገመንግስቱንና ፌደራል ስርዓቱን አናስነካም እንበልና፣ስንሞትም ስንኖርም ኢትዮጲያውያን ነን ከሚሉ አስመሳዮችን ተላላኪዎች ታግለን እናስጥላት።ኦሮሞ ስለሆን ነው እየተቃወሙን ያሉት የሚለውን የሸፈጥ ሽፋን በፉፁም አይደለም! ብለን እናጋልጣቸው። አጭበርባሪዎች እንበላቸው። የኦሮሞ ወጣትና ህዝብ ጥያቄ መች መለሳቹህ እንበላቸው።ወለጋ ላይ ኦነግ እያላቹህ ለምን ትጨፈጭፉናላቹህ እንበላቸው።ፌደራሊዝምን ለምን ከሚኒሊክ ተከታዮች ጋር ሆናቹህ ልታፈርሱ ትተጋላቹህ እንበላቸው።እናንተን ብቻ ነው ወይ ኦሮሚያ የወለደችው እንበላቸው። እውነታው ማንም ኢትዮጵያዊ ኦሮሞ ጠቅላይ ሚኒስተር አይሆንም አላለም። በኢትዮጵ

እንደዜጋ የብሄር መብታችንን እየተጠቅምን የግለሰብ መብታችን ማስከበር እንችላለን።ሁለቱ መብቶች በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አይለያዩም።ኦሮሞ ሁኜ የራሴን አስተዳዳሪ የመምረጥም የማውረድም መብቴ እስከተከበረና እስካስከበርኩኝ እንደዜጋም እንደግለሰብም መብቴን አረጋገጥኩኝ ማለት ነው።ያልተሰበረን ዕቃ አይሰራም ብሎ እንደመጣል ነው።ሲሰራና ለውጥ እያስመዘገበ የነበረውን ህገመንግስታዊና ፌደራላዊ ስርዓትንና ኢኮኖሚ ፖሊሶዎቻችን መሪዎቹ ስለተበላሹ መሪዎቹ ይቀየራሉ እንጂ በምን ሂሳብ ያልተሰበረውና ያልተጣመመውን ለማቃናት ይሞከራል።የሚስራውን ጥላቹህ ተበድራቹህ ባመጣቹሁት የጌቶቻቹህ ህግና ስርዓት ስታመጡማ ነው ስላም ያጣንው፣ወንጀል የተባዛው፣ኢኮኖሚ ደቅቆ አይቶ ያጣ ያደረጋችሁን፣ህዝብ ለህዝብ እያበላለጣቹህ በእኩልነት በፍቅር በአንድነት የነበሩትን ህዝቦች አጣልታቹህ ብሄር ተኮር ጥቃት ሰለባ አድርጋቹህን በተፈናቃይ ሀገራችንን ከዓለም ቀዳሚዋ ሀገር አደረጋችኋት፡፡ እንደ የግመል ሽንት ወደ ኃሊት አስኬዳቹሁን ብለን ይበቃል እንበላቸው።
Full Website