“It’s a familiar story to what we’ve seen in other countries undergoing a rapid and messy democratization, and it will require a massive effort to ensure that high-quality journalism and civic dialogue prevails without compromising freedom of expression,” said Nicholas Benequista of the Washington-based Center for International Media Assistance. በግርድፉ ሲተረጎም፤ ይህ በሌሎች ፈጣን እና ውጥንቅጡ በሆነ ሂደት የዲሞክራሲ ለውጥ ባካሄዱ ሌሎች ሃገራት ያየነው ተመሳሳይ ትርከት ነወ፤ ሃሳብን የመግለጽ ነፃነት አደጋ ላይ ሳይወድቅ፤ ከፍተኛ ጥራት ያለው ጋዜጠኝነት እና የዜጎች ውይይት ኧሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ ከፍተኛ ጥረት መደረግ አለበት። ይህን የተናገሩት ኒኮላስ ቤኔኩዊስታ የተባሉት የአለማቀፍ የሚድያ እርዳታ ማእከል  ባለስልጣን ናቸው። ኒኮላስ ይህንን ሃሳባቸውን የሰጡት፤ ለዋሽንግተን ፖስት ጋዜጠኛ እና  የብሔር ውጥረት እሳትን እያራገበ ይገኛል። ጋዜጣው  በጽሁፉ ለምሳሌነት ያነሳው ጋዜጣም፤ የእስክንድር ነጋን ሳምንታዊ ጋዜጣ ነው። ይህ ጽሁፍ፤ በአዲስ አበባ ከተማ “ባለ አደራ ምክር ቤት” ተብሎ መቋቋሙ ተገቢ አለመሆኑን ለማሳየት፤ የፃፍኩት የመጨረሻው ክፍል ጽሁፍ ቀድም ብሎ የተፃፈ ቢሆንም፤ ለሕትመት ከመብቃቱ በፊት፤ አዲሱን “ነፃነት” ያገኘው የኢትዮጵያ ሚዲያ፤ ለሃገሪቱ የሚበጅ ሚዛናዊ እና ትክክለኛ የሆኑ ነገሮችን ከመስራት ይልቅ፤ አብዛኛው የዜና አውታር፤ “በአድማ ፖለቲካ” ተካፋይ በመሆን፤ ከሃገር እና ከሕዝብ ጥቅም ይልቅ፤ የግል ጥቅሙን ለማስጠበቅ፤ ሲል፤ የብሔር ግጭቶችን የሚያራግብ “ተቋም” መሆኑ በዋሽንግተን ፖስት ተዘግቧል። በዚህ የመጨረሻ ክፍል ጽሁፌም ለማቅረብ የፈለግኩት፤ እምብዛም ከዚህ የተለየ ባይሆንም፤ ትኩረቴ ግን፤ የአዲስ አበባ “ባለ አደራ ምክር ቤት” መቋቋምን ተከትሎ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ፤ እስክንድር ላይ “ጦርነት አወጁ ዓይነት” ፕሮፖጋንዳ “በጋዜጠኞች” በመነሳቱ እና፤ በዛም ምክንያት፤ በዶ ጋዜጠኞች እና የዜና አውታሮቻችን፤ በሃገራችን ላይ ሊሰሩ የሚገባው ተገቢ ሥራን በተመለከተ፤ በሚቀጥለው በሰፊው እጽፍበታለሁ። ዛሬ ግን፤ “እስክንድር ነጋ ተነካ” በሚል ስሜት፤ “ከ ር ዓብይ መራሹ አስተዳደር፤ ስሕተት እና ጥፋት ሲስራ ሊወቀስ፤ ሊወገዝ፤ እና አስፈላጊ ትችት ሊሰነዘርበት ይገባል። በበጎም ይሁን በመጥፎ የሚነሱ ማናቸውም የአስተዳደሩ ሥራዎች ሚዛናዊ እና ተገቢ መሆን አለባቸው ብዬ አምናለሁ። የሃገራችን ሁኔታ ያለፈቀደ በመሆኑ፤ ሃገራችን፤ ብዙ በጋዜጠኝነት ሙያ ትምህርት የቀሰሙ “ሚዛናዊ ጋዜጠኞች” የሏትም። አብዛኞቹ የሃገራችን ጋዜጠኞች የተካኑት የፕሮፖጋንዳ ሥራ ነው። ትላንት “በልማታዊ ጋዜጠኝነት” ሙያ ሰልጥነው፤ የገዥው ፓርቲ አቀንቃኝ የነበሩ የዜና አውታሮች እና ጋዜጠኞች የነበሩትን ያክል፤ በተቃውሚው ጎራም፤ በታሪክ አጋጣም ማይክሮፎን እና በዕር የጨበጡ፤ ጋዜጠኞች እና እራሳቸውን ጋዜጠኛ አድርገው የሾሙ፤ ፕሮፓጋንዲስቶች እንደ አሸን ሊፈሉ ችለዋል።
Full Website