ይህ ፅሁፍ በነፃ ጉተማ ፌስቡክ እየተፃፈ የሚገኝ ነው፡፡ አላለቀም፡፡ ነገር ግን አገራችን የሚትገኝብትና ተጨባጭ አደጋና ለወደፊት የተደገሰላት የጥፋት ድግስ የሚሳይ በመሆኑ በሐሳብ ልእልነት በሚያመነው በአይጋ ድረ ገፅ ቢወጣ ቡዙ ኢትጵያዊ ተገንዝበው አገራቸውን ለመታደግ ይተጋሉ ብየ አስባለሁ፡፡ የአርትኦት ስራ ብቻ ነው የተጨመረው እንጂ ፅሁፍ የነፃ ጉተማ ነው፡፡

መኮነን ነብይ፣ ከአዲስ አበባ 10-2-19

ላይ ነው። ትርጉሙም ከፍርድ ቀን በፊት የሚደረገው የመጨረሻው ጦርነት ስፍራ ነው። ሀይማኖትን ልሰብካችሁ አይደለም። ነገር ግን የቁጣ

ነገሮች ውስጥ አንዱ የስድብ _ አንደበት ምናልባት እኔ እንደሚገባኝ የስድብ _ ሚድያ ነው ይለናል ባለ ራእዩ። እናም አውሬው መልካም ነገር ለመናገር፣ እውነትን ለማውራትም ሆነ ቀናን ነገር ለማድረግ ስብእናው አይፈቅድምና ይሳደባል፣ ይወርፋል፣ ያበሻቅጣል።

በምድራችን የተከሰቱ የህዝብ ፍጅትንና በርካታ የአርማጌዶን _ መንትዮች ብንመለከት ህዝብ ሳንጃ መዝዞ በባሩድ ከመታጠኑ በፊት የፕሮፖጋንዳ ማሽኖቹ ሚድያዎች በዙ ነገር ብለው ነበር። ለምሳሌ የናዚ ፍጅት፣ የናፖሊዮን ፍጅት፣ የአርመኖች ፍጅት፣ የስታሊን ፍጅት፣ የኤዲ አሚን ፍጅት፣ የደርግ ፍጅት፣ የሩዋንዳ ፍጅት፣ የሶሪያ ፍጅት ወዘተ ከመፈጸማቸው በፊት ሚዲያዎች እልቂቱን በጣም በሚያማልሉና ልብ በሚያቀልጡ ንግግሮች ሲያሽሞኖሙኗቸው ነበር። እነዚያ ሚዲያዎች በወቅቱ ያደረጉትን ባያደርጉ ፍጅቱ ተረት እልቂቱም ነበር በሆነ ነበር። ግን አለማችን አልታደለችም። ስልጣንን በአቋራጭ ለሚሰቀሉባት፣ መንበርን በቆረጣ ለሚጋልቡባት ህሊና ቢስ የሀይል ሚዛን አምላኪዎች ስትል ብቻ ይህች አለማችን ሚሊዮኖችን ዶግ አመድ አድርጋ ለሌላ እልቂት ትዘጋጃለች።

እኛ ጋርም ልክ እንዲሁ ነው። ዳቦ ተነጥቆ ቆሎ የተሰጥው፣ ጠጅ ተቀምቶ ድፍርስ ውሀ የተሰጠው ግፍና በደሉ በመቶ እጥፍ ተሰብኮለት በፍጅት ዳክሯል። በዚያው ልክ ደግሞ አሻሮ ተነጥቆ ዳቦ የታደለው፣ ድፍርስ ውሀ ተቀምቶ ወተት የተሰጠውም መጥፎውን ቀምተው ጥሩውን የሰጡህ ለአሻጥር ነው፣ ሸውደውህ ነው፣ ዘርፈውህ ነው ወዘተ ተብሎ፣ ታሪክ ተገልብጦ በፍጅት ውስጥ ተንከባሏል። በአሁኑ ሰአት በገዛ አይናችን ፊት የምናየው ይህንን ነው።

ሚዲያዎቻችን ምን ምን እንዳደረጉ፣ ያስተላለፏቸው ስርጭቶች አገራችንን እንዴት እንዳመሳቀለው፣ ለማይቀረው አርማጌዶን በምን ልክ እያዘጋጁን እንደሆነ በሚገባ እንመለከታለን።
Full Website