9-12-19

ባሳለፍነው ዓመት በጽሁፎቼ ትኩረት ካደረግኩባቸው ጉዳዮች አንዱ የትምህርት ጉዳይ ነበር፡፡ እንደፈራሁትም አልቀረ አሮጌውን ዓመት የሸኘነው በትምህርት ሚኒስቴር አዲስ የትምህርት ፖሊሲ ፍኖተ ካርታ ውዝግብ እና በአስራ ሁለተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የስርቆት ዜና ነው፡፡ የዚህን ጽሁፌን ርዕስ “ትምህርት ሚኒስቴር ተጭበርብሮ አጭበረበረን” ያልኩት ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ወደ ምክንያቶቼ ከመሄዴ በፊት አንዳንድ ጉዳዮችን ላንሳና በምክንያቱ ላይ እመለስበታለሁ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ባለፉት 25 ዓመታት የነበረውን የትምህርት ሂደት ከገመገመ በኋላ “ከሦስተኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል፣ ግማሽ ያህሉ (50%) አንዲት አጭር ዓረፍተ ነገር አንብበው ለመገንዘብ የሚያስችል እውቀት የላቸውም። ሩብ (25%) ያህሉ ደግሞ አንዲትም ቃል ማንበብና መጻፍ፣ መደመርና ማባዛት… አይችሉም” የሚል ዜና አምና በዚህ ወቅት በጥናት አረጋግጦ ነግሮን ነበር፡፡ ባለፉት 25 ዓመታት ትምህርት ለሁሉም የሀገሪቱ ህፃናት ተደራሽ ባለመሆኑና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ባለመቻሉ አራት ክፍሎች ያሉት “የትምህርትና የስልጠና ችግሮችንና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን…” የያዘ ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀቱንም የነገረን ያኔ ነው፡፡

ዓይነት የመከኑ፣ እውቀት አልባ፣ ስማቸውን እንኳ በትክክለኛ ፊደ አስተካክለው መጻፍ የተሳናቸው መሆናቸውን ያስተዋሉ ሰዎች ገና ከጅምሩ “ፖሊሲው ትውልድ ገዳይ ነው” በማለት ሲናገሩ ጆሮውን በጥጥ ደፍኖ አስተያየቱን እንደ “ሟርት”፣ ትችቱን እንደ “የጠላት ወሬ” ሲቆጥር የነበረው ትምህርት ሚኒስቴር እንደ አዲስ ግኝት የፖሊሲውን የድክመት መርዶ መናገሩ ሲገርመን፤ ይህንን ለመቀየር በአዲሱ ፍኖተ ካርታ አማካይነት “እውቀትን ማስጨበጥ ሳይሆን ሙያን ማስተማር አስፈላጊ ነው” የሚል አስቂኝ የትምህርት ዓላማ ይዞ ብቅ ማለቱን ስንሰማ “ኧረ እየተስተዋለ
Full Website