መደመር እና ተንኮሉ

ከስዮም ሓጐስ መቐለ ነሓሰ1, 2010

አንዳንድ ወገኖች መደመር፤ ፍቅር ለምን ትጠላላችሁ ይሉናል፡፡ በዚህ አለም መደመር፤ ፍቅር የሚጠላ ሰይጣን ብቻ ነው ግን እኛ ይንን ኣባባል ተንኮል ያለበት ስለሆነ ነው፤ የማንቀበለው ምክንያቱም

መረጃ አንድ፤ 27 ዓመታት በጨለማ ነበርን፤ ኣእምሮ ያለው ሰው ይንን እንዴት ይቀበላል? የተሰራውን ስራ ሁሉ ከንቱ የሚዳርግ እና የተሰራው ጥሩውን ነገር ላለማንሳት ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ቤቱ ብፈታሽ ባለፉት ዓመታት ዕድግት አለው፡ እንካንስ በአገር ደረጃ የተሰሩት እና በኢትዮጵያ ህዝብ በአለም አቀፍ ተቃማት የተመሰከረላቸው

መረጃ ሁለት፤ የትግራይ ህዝብ ማንቃሸሽ፤ በጅምላ መሳዳብ (የቀን ጅቦች ፀገሩ ልውጥ) የለማኞች ምሳሌ ማድረግ፡፡ በላፉት 27 ዓመታት በሁሉም ክልል ኮራፕሽን እና የመልካም አስዳድር ችግር ነበር፤ ግን ለአንድ ወገን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ ትክክል አይደልም

መረጃ ሶስት፤ አሁን በስልጣን ያሉ ለ27 ዓመታትም በስልጣን ነበሩ ያውም በከፍተኛ ቦታ፤ ስለዚህ እንዴት ራሳቸው ንፁህ ሌላውም ባለዕዳ ያደርጋሉ፤ ህልና ላላው ሰው ይንን እያየ እንዴት ይደመራል

መረጃ አራት፤ ትናንት ወያነ ሁሉም የስልጣን እርከን ይዛል ብሎ ስውቅስ የነበረ ዛሬ ይንን ራሱ እንዴት ይደግማል (ጠቅላየ ሚነስቴር፡ ውጭ ጉዳይ፤ ምክትል አታማጆር ሹም እና ኦፕሬሽን ሃላፉ፤ አየር ሃይል አዛዝ፤ ምክትል ደህንነት ሓላፊ፡ ዓቃቤ ሕግ፤ ጉምርክ፤ አድስ ኣባባ ከንቲባ እና ፖሊስ አዛዥ ወዘተ)

መረጃ አምስት፤ ትናንት ህገ መንግስቱ ተግበራዊ አልሆነም እያለ ህዝብን ስያነሳሳ የነበረ ሰው፤ ዛሬ በራሱ ጉልበት ሽብርተኛ የተባሉ እስረኛች መፍታት፤ የክልል መስደዳድሮች ያለ በቂ ምክንያት ማንሳት ወይ እንድነሱ በተዘዋዋሪ መስራት፤ ሁሉም ማስ ሚድያ ለራሱ አገልግሎት ማዋል

Videos From Around The World

Full Website