ባንዲራ የአንድ አገር ሕዝብ ማንነት መገለጫ ነው። የሰው ልጆች በታሪካቸው ውስጥ የየራሳቸውን ቡድን ወይም ወገን ከሌሎች ለመለየት ጨርቅን በተለያዩ ቀለሞች በመቀባት፣ እንጨት ላይ ሰክተው በእጃቸው ይዘው በመዞር፣ አንገታቸው ላይ በማሰር ወይም ጎልቶ እንዲታይ ከማሰብ አንጻር ረዘም ባሉ እንጨቶች ላይ እየሰቀሉ ከማንነት መገለጫም ባሻገር ይዞታን ወይም ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ይጠቀሙበት እንደነበር የሕብረተሰብ ታሪኮች መዝግበዋል። ባገራችን ባንዲራ እንደ ኢትዮጵያ መገለጫ ሆኖ መቼ እንደቀረበ በትክክል ባይታወቅም፣ ባንዲራን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ለመጀመርያ ጊዜ ያስተዋወቁት አጼ ምኒልክ መሆናቸው በሰፊው ይነገራል። ያኔ ትክክለኛ ስሙ “ሰንደቅ ዓላማ” በመባል ቢታወቅም፣ ጣሊያኖች ኢትዮጵያን ከወረሩ በኋላ ግን “ባንዲራ” በሚለው የጣሊያንኛ ቃል ተተክቶ ዛሬ በስፋት እየተጠቀምንበት ነው። (በዚህ ጹፌም ይህንን ሳንወድ በግድ ተጭኖብን ዛሬ የአማርኛ ቋንቋችን አካል የሆነውን “ባንዲራ” የሚለውን አባባል በተደጋጋሚ እጠቀማለሁ)። ይህ ጽሁፌ የሚያተኩረው፣ ከአገርና ከማንነት ጋር ስለ ተያያዘው ባንዲራ ላይ ብቻ ነው። አገራት ባንዲራዎቻቸውን እንደሚያመቻቸው የማንነታቸው መገለጫ አድርገው ይጠቀሙበታል። ዲሞክራሲ እንደ አንድ የአገዛዝ ሥርዓት ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት በነበሩት ያገዛዝ ሥርዓቶች፣ የገዢው ክፍል (ለምሳሌ ንጉሦች) ያላንዳች የሕዝብ ተሳትፎ ራሳቸው ያሰኛቸውን ቅርጽና ቀለም ያለውን ባንዲራ አሰርተው ያገራቸውና የሕዝባቸው መለያ አድርገው ይጠቀሙበት ነበር። ለምሳሌ በተለምዶ የኢትዮጵያ የምንለው ባለሶስት ቀለማት ባንዲራ ያገራችን ሕዝቦች መለያ እንዲሆን የተወሰነው በሕዝቦች ተሳትፎ ሳይሆንበአጼ ምኒልክ ውሳኔ ነበር። ያኔ በነበረው ያገዛዝ ሥርዓት፣ ንጉሥ “ስዩመ እግዚአብሔር” ስለሆነ ሕዝቡከንጉሡ“የተሰጠውን”እንዳለተቀብሎ ሥራ ላይ ማዋል እንጂ የሚፈልገውን የመምረጥ መብት ስላልነበረው፣የራሱ ባንዲራ አድርጎ ሲጥቀምበት ኖሯል። በሌሎች አገራት ግንዲሞክራሲያዊ የአገዛዝ ሥርዓቶች እየተስፋፉና እየተለመዱ ሲመጡ፣ የባንዲራ ምርጫም ልክ እንደ ሌሎች አገራዊ ጉዳዮች ለሕዝብ ቀርቦና ሕዝብም ተወያይቶበት የሚበጀውን ባብላጫው ድምጽ እንዲወስን ይደረግ ነበር። ዛሬም ብዙ አገራት የሚከተሉት ይህንን ልምድ ነው። ባንዲራና አገርን በተመለከተ ገዢው የዲሞክራሲ መርህ፣ አገር ቋሚ ናት፣ ባንዲራ ግን እንዳስፈላጊነቱ ሊቀየር ይችላል የሚል ነው። አዎ! የባንዲራ ቀለምና አርማ፣ እንደ አገር ቋሚ ነገር አይደለም። አስፈላጊ ከሆነ መሪዎች በተቀያየሩ ቁጥር ባንዲራም ሊቀየር ይችላል። አገራችን ኢትዮጵያን እንደ ምሳሌ ብንወስድ፣ ሶስት ቀለማት የነበረውን ልሙጡን የአጼ ምኒልክን ባንዲራ፣ አጼ ኃይለ ሥላሴ ሲነግሱ፣ ቀለማቱን እንዳለ ወስደው በላዩ ላይ ግን የሞዓ አንበሳን ምልክት ለጥፈውበት የኢትዮጵያ ባንዲራ እንዲሆን ወሰኑ። ምንም እንኳ የሕዝባችን ተሳትፎ ባይኖርበትም፣ ያ ባንዲራ የዘውዱ አገዛዝ በደርግ እስኪተካ ድረስ ያገራችንና የሕዝባችን የማንነት መታወቂያ ሆኖ ከማገልገሉም በላይ፣ ላብዛኛው ሕዝባችን ከወንጀለኛ መቅጫ ወይም ከፍትሃብሔር ሕጎች ይልቅ በዜጎች ሕይወት ውስጥ ትልቅ ሚና ነበረው። በአከራካሪ ጉዳዮች መካከል አንደኛው ወገን “በባንዲራ አምላክ” “ወድቆ በተነሳው ባንዲራ” ካለ፣ ሌላው ወገን በምንም ተዓምር በሚከራከሩበት ጉዳይ ላይ ሊቀጥል አይችልም። የደርግ መንግሥት ሥልጣን ሲረከብ፣ የአጼውን ባንዲራ ቀለሞቹንና የቀለሞቹን አቀማመጥ ሳይቀይር፣ መጀመርያ ላይ፣ ከሞዓ አንበሳው ዘውዱን አንስቶ ያንኑ አንበሳ ያለዘውድ አስቀመጠ። እየቆየ ሥልጣን ወንበሩ ላይ ተረጋግቶ ኢሠፓን ከመሰረተ በኋላ፣ ይህን ዘውድ የለሹን ያንበሳ አርማ የአርሶ አደሩና የወዛደሩን ሕብረት በሚያሳይ “ሶሺያሊስታዊ” አርማ ተካው። ኢሕአዴግ ደርግን ገልብጦ ሥልጣን ሲወስድ፣ ሶስቱን ቀለማት አቀማመጥ ሳይነካ የ “ሶሺያሊስቱን” አርማ አንስቶ “የብሄር ብሄረ ሰቦችን” ይወክላል ባለው የኮከብ አርማ ተካው። በዚህ ጊዜ አንድ እስከዛሬ ባባንዲራችን ታሪክ ውስጥ ያልታየ አዲስ ክስተት ቢኖር፣ በኢሕአዴግ ዘመን ከአርማው መቀየር ባሻገር ከለምደናቸው ሶስት ቀለማት ሌላ ሰማያዊ ቀለም መጨመሩንም ነው። ከዚህ ሂደት የምንረዳው ሁለት ዋና ነገር፣ ሀ) ተከታታይ ገዢዎቻችን የባንዲራዎቻችን ቅርጽና ይዘት ያላንዳች የሕዝብ ተሳትፎ እንዳሰኛቸው ይቀያይሩ እንደነበርና፣ ለ) ከአጼ ምኒልክ ወዲህ ሥልጣን ከያዙት ተከታታይ ገዢዎቻችን መካከል፣ አንዳቸውም የፊተኛውን ባንዲራ ቅርጽና ይዘት እንዳለ ጠብቆ ያኖረ እስከዛሬም አለመኖሩን ነው። ባንዲራ በርግጥም ያንድን አገር ልዕልና ማስከበርያና በዚያ አገር ለሚኖሩት ዜጎች መለያና ማንነት ማረጋገጫ የሆነ ከጨርቅነት በላይ ልዩ ስሜትን የሚረጭ አገራዊ ሃብት ነው። አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ጨርቆች ጣቃ ተራ ለሽያጭ ተዘርግተው ሲታዩ የሌላቸውን ዋጋ፣ ሶስቱ ቀለማት አንድ ላይ ተሰፍተው ከአርማው ጋር ሰንደቅ ላይ ሆነው ሲውለበለቡ ማየት የሆነ ልዩ ስሜትን በሰውነታችን ውስጥ ይረጫል። ለዚህ ነው አባቶቻችን ጠላትን ለመውጋት ሲሄዱ ባንዲራውን ከፊት አድርገው በድፍረት የሚዘምቱት! ለዚህም ነው ጠላት እንኳ ሲያጠቃቸውና ሲያፈገፍጉ፣ ድንገት ተማርከው ጠላት ባንዲራውን መዘባበቻ እንዳያደርግ ከማሰብ “እኔስ ልሙት ባንዲራው ግን መሞት የለበትም ብለው፣ ከጦርነቱ በኋላ ተከታዩ ትውልድ ፈልጎ ያገኘዋል ብሎ ከማሰብ ባንዲራውን ጠቅልለው የሚቀብሩት!  አዎ! ባንዲራ ልዩ ኃይል ያለው የማንነት መገለጫ ምልክት ነው። ይህ የባንዲራ ልዩ ኃይልና የኔ ነው ብለው በተቀበሉት ዜጎች ላይ የሚያሳድረው ልዩ የሆነ የማንነት ስሜት ነው እንግዲህ ባንዲራው የማንነቴ መገለጫ ነው ብለው የሚያስቡትን ሰዎች በሌላ ይህንን ማንነታቸውን ይቀናቀናል ብለው በሚገምቷቸው ግለሰቦች ወይም ቡድኖች ላይ ከቃላት ግጭት አልፎ ውድ ሕይወትን ለመሰዋት ዝግጁ የሚያስደርግ። ለዚህም ነው መንግሥታትም በሰላሙ ጊዜ ያገራቸው ምልክትና የራሳቸው መገለጫ በመሆኑ ውዱን ሕይወታቸውንም ቢሆን ክፍለው እንዲንከባከቡት ሕዝብን የሚያስተማሩትና በጦርነት ጊዜ ደግሞ ለባንዲራው ክብር መሞት የሚጠበቅባቸው መስዋዕትነት መሆኑን አጥብቀው የሚያስረዱት። ይም ሆኖ ግን፣ አገርና ሕዝብን ከውጭ ወራሪ ኃይል ለመከላከል ሕዝቡንለማስተባበር ይረዳ እንደሁ እንጂ፣ ባንዲራ በየትም አገር አንድ መንግሥት ከዜጎች ጋር ያለውን ግንኙነት ማለትም የዜጎችን ዲሞክራሲያዊና መሠረታዊ የሰው ልጆችን ሰብዓዊ መብት ለማስከበር እምብዛም ጠቃሚ ሲሆን አልተስተዋለም። ዛሬ ባንዲራን አስመልክቶ ባገራችን በዝቅተኛ ደረጃ የሚታይ በተለያዩ ቡድኖች መካከል የሚከሰቱ ግጭቶች ከዚሁ ከባንዲራ ምንነትና በባንዲራው ከሚያምኑቡድኖች ውስጣዊ ስሜት የመነጨ ይመስለኛል። ግጭቶቹ ግን ከቃላት ወደ አካላዊ  ተሸጋግረው የዜጎችን ነፍስ እስከማጥፋት ደርሰዋል። ዛሬ በዝቅተኛ ደራጅ የሚታይ ግጭት ይምሰል እንጂ አስቸኳይ መፍትሄ ካልተፈለገለት ወደ ከፍተኛ ደረጃ ግጭት እንደሚሻገር ሁኔታዎች ያመላክታሉ። ግን እንዴት ሆኖ ነው እዚህ የደረስነው? ከወትሮ የተለየ ምን ነገር ቢፈጠር ነው ዛሬ የተለያዩ ቡድኖች የኔ ባንዲራ ካንተ ባንዲራ የተሻለ ስለሆነ ያንተን ትተህ የኔን ተቀበል፣ ካልተቀበልክ ደግሞ እንድትቀበል አስገድድሃለሁ የሚል ደረጃ ላይ የደረስነው? መንግሥትም ላለፉት ኸያ ሰባት ዓመታት፣ ምንም እንኳ ያው እንደተለመደው ያለ ሕዝቦቻችን ፈቃድ፣ በተለመደው ሶስት ቀለማት መደብ ላይ ባለ አምስት ጫፍ ኮከብና ሰማያዊ መደብ ጨምሮ የፌዴራሉ ባንዲራ ነው ብሎ በተባበሩት መንግሥታትና በሌሎች ዓለም አቀፍ እንዲሁም በቀጠናዊ ድርጅቶች ዋና መሥርያ ቤቶች ካውለበለበና፣ ዘጠኙ የፌዴራሉ አባል ክልሎችም የየራሳቸውን ባንዲራ ማውለብለብ ከጀመሩ ያን ያህል ጊዜ ቢያልፍም፣ ለምንድነው ዛሬ ልሙጡ የምኒልክ ባንዲራ እንደ ትክክለኛው የኢትዮጵያ ባንዲራ ሆኖ የቀረበው? አጼ ኃይለ ሥላሴ ይህንን አርማ አልባው የምኒልክን ባንዲራ ቀይረው ራሳቸው የፈለጉትን ሞዓ አንበሳ ሲጨምሩበት፣ ደርግ ደግሞ ሞዓ አንበሳውን አስነስቶ በሶሺያሊስት አርማሲተካው ምንም ተቃውሞ ሳያስነሳ፣ ለምንድነው ዛሬ ልሙጡ የምኒልክ ባንዲራ ላይ ኮከብ መጨመሩእስከ ግጭት የሚያደርሰን? የሚገርመው እኮ አርማዎች ተቀያየሩ እንጂ ባንዲራው ከምኒልክ ጊዜ ጀምሮ ቀለሞቹም፣ የቀለሞቹም አቀማመጥ እንዲሁም የጨርቁ ርዝመትና ስፋት አልተቀየረም። በኔ ግምት፣ ችግሩ ያለው በአርማው ላይ አይደለም የምልበት ሁለት ምክንያቶች አሉኝ። አንደኛው፣ አገሪቱ በፌዴራሊዝም የአስተዳደር ሥርዓት መሠረት፣ ዘጠኝ “ራሳቸውን የሚያስተዳድሩ” እና የየራሳቸውን ባንዲራ የሚያውለበልቡ ክልሎች በመፈጠራቸው፣ የለመድነው አንድ አሓዳዊ መንግሥትና አንድ ባንዲራ ስለቀረብን ይመስለኛል። ሶስቱን ቀለማትና አቀማመጣቸውን ሳይቀይሩ ተከታታይ መንግሥቶቻችን እንደተመቻቸው ያሰኟቸውን አርማዎች በባንዲራው ላይ ሲለጥፉ ያላመመን፣ ዛሬ እንደዚህ ሊያሳምመን የቻለው ኢሕአዴግ በለጠፈው አርማ ሳይሆን፣ ባወጀው የፌዴራል ሥርዓትና አስተዳደርና ክልላዊ መዋቅር ይመስለኛል። ችግሩ እንግዲህ ከፌዴራሊዝም ሥርዓትና የሥርዓቱ ውጤት በሆነው የክልሎች አወቃቀር ዘንድከሆነ ደግሞ ባንዲራውን እንደ ሰበብ ከመጠቀም ዋናው የችግሩ ምክንያት የሆነውን ፌዴራሊዝም ላገራችን ይበጃል ወይስ አይበጅም ብሎ መወያየቱ የሚበጅ መሰለኝ። ሁለተኛው ደግሞ የኦቦ ለማ የለውጥ ቡድን የተቃዋሚ ድርጅቶችን አጄንዳ በሙሉ ስለነጠቃቸው፣ እነዚህ ድርጅቶች ዉሃ የቋጠረና ሕዝቦቻችንን የሚያቀራርብ ሕዝባዊ የፖሊቲካ አጄንዳ ማቅረብ ሲያቅታቸው፣ በዚህ በቀላሉ ሊለያየን በሚችል ጎጂ አጄንዳ ላይ ማተኮርን ስለመረጡ ይመስለኛል። ስለፌዴራሊዝም አዋጪነት ወይም ኪሳራ፣ መድረኩ ተበጅቶ እሰጥ አገባ እስክንጀምር ድረስ፣ ለጊዜው በየቦታው የተለያዩ ባንዲራዎችንና አርማዎችን በማውለብለብ “ከተቃራኒ ወገን” ጋር ግብ ግብ ለመግጠም ለሚዘጋጁ ወገኖቻችን፣ ባንዲራና ዲሞክራሲያዊ መብትን አመላክቼ የሚከተለውን ለማለት እሻለሁ። ባንዲራ ያንድን አገር ልዕልና ለማስከበር ሕዝቦቿን ከማስተባበር ባሻገር በአገሪቷ ውስጥ የሕዝቦችንና የዜጎችን ዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶችን ከማስከበር አንጻር የሚጫወተው ሚና በጣም ውስን ነው ብያለሁ። የግለሰብና የቡድን መብቶችን በማስከበር ረገድ ላንዳንድ ሕዝቦች ባንዲራ እንዲያውም የመጨቆኛ መሳርያ እንጂ የእኩልነት ተምሳሊት ሆና አይታይም። የምኒልክን ባንዲራ በተመለከተ ለምሳሌ፣ ጀግኖች የጦር መሪዎቻችን በዚህ ባንዲራ ሥር ሕዝቡን አሰልፈውና ራሳቸውም ባንዲራውን እያውለበለቡ ጣሊያንን ሲዋጉ ተገደለውም በዚሁ ባንዲራ ተገንዘው ወደዚያኛው ዓለም ሲሸኙ፣ ጦርነቱ አልቆ በሕይወት የተመለሱት የጦር አበጋዞችና ሌሎችም ተዋጊዊች ደግሞ “አርበኛ” ተብለው ይህንኑ ባንዲራ እያውለበለቡ ወደ ደቡብ ተልከው የዜጎችን መሬት ያላንዳች ካሳ በመንጠቅና፣ የቀድሞ ባለመሬቶችን “ገባር” አድርገው፣ የ 1967 ዓ

እስካሁን በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የታዩት አራት መንግሥታት ሲሆኑ (ንግሥት ዘውዲቱና ልጅ ኢያሱን ሳይጨምር)፣ በአራቱም የአገዛዝ ዘመን በኢትዮጵያ ባንዲራዎቹ ሥር የዜጎችና የሕዝቦች መብት የተከበረበት ጊዜ አልነበረም። በምኒልክ ዘመን የዜጎች አካላት ተቆርጠዋል፣ በኢሕአዴግም እግሮችና ጣቶች ሲቆረጡ አይተናል። በኃይለ ሥላሴ ዘመን የዘውዱን አገዛዝ ሥርዓት ለመመፈንቀል አሲራችኋል ተብለው ዜጎች በጥይት ተረሽነዋል፣ ተሰቅለዋል። በደርግ ዘመንም በተለይም በቀይና በነጭ ሽብር ጊዜ ብዙ ወገኖቻችን ተገድለዋል፣ ለስቃይ ተዳርገዋል። ያም ሆኖ ግን፣ በምኒልክ ዘመን  ወደ ዓድዋ፣ በኃይለ ሥላሴ ዘመን ወደ ማይጨው፣ በደርግ ዘመን ደግሞ ወደ ኦጋዴን፣ በኢሕአዴግ ዘመን ደግሞ ወደ ባድሜ የዘመተውና የተዋደቀው ሕዝባችን በወቅቱ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ተብሎ ከላይ “የተሰጣቸውን” የኢትዮጵያዊነት ማንነታቸውን ማረጋገጫ የሆነውን ይዘው እንደነበር ታሪክም እኛም ምስክሮች ነን።የሚገርመው ደግሞ፣ ሕዝባችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለማስከበር ወደ ባድሜ የዘመተው ከሁሉም ባንዲራዎች ዝቅተኛ ቅቡልነት ያገኘውን የኢሕአዴግን ባንዲራ እያውለበለበ ነበር። ስለዚህ ነው ባንዲራ ያንድ አገርና ሕዝብ የማንነት መገለጫ በተለይም ዳር ድንበርን ለማስከበር ሕዝብን ለማስተባበር ይረዳል እንጂ በሰላሙ ጊዜ ለዜጎች የፍትህ ምንጭ ወይም መለኪያ አይደለም የሚባለው። 7 ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ መንግሥት ባቀረበላቸው ጥሪ መሠረት መመለስ ከጀመሩ በኋላ የድርጅቶቹን ባንዲራ አስታኮ በአዲስ አበባና አካባቢው የተከሰተውና በመከሰት ላይ ያለው ግጭት አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል። የግንቦት ደግሞ ለአንድነት ዘብ የቆመ አድርጎ ማቅረብ ትክክል አለመሆኑ እየታወቀና፣ በተለይም ደግሞ ሁለቱም አርማዎች ወይም ባንዲራዎች የድርጅቶቹ እንጂ እንወክለዋለን የሚሏቸው ሕዝቦች ማንነት መገለጫና አርማ አለመሆኑ እየታወቀ፣ በግድ የኔ ብቻ ትክክለኛ ነው ብሎ መሞገት፣ አንድም የዲሞክራሲን ምንነት ካለመረዳት የሚመጣ፣ አለያም ማን አለብኝነት  ይመስለኛል።

ሁለት ዓቢይ ጉዳዮችን አንስቼ ላጠቃልል፣

እስካሁን ስናውለበልባቸው የነበሩ ባንዲራዎቻችን በሙሉ ከላይ ገዢዎቻችን “ይህ ነው የሚበጃችሁ” ብለው የወሰኑልን እንጂ እኛ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በፈቃዳችን ያመጣነው አይደለም። ወደፊት በሚደረጉት ዲሞክራሲያዊ ምርጫዎች የምንፈልጋቸውን ተወካዮቻችንን መርጠንና እነሱ እንዳስፈላጊነቱ የሚያጸድቋቸውን ሕግጋት መሠረት ባደረገ ሕዝበ ውሳኔ የሚጸድቅው አዲስ የባንዲራ ዓዋጅ እስኪደነገግልን ድረስ፣ አሁን ባለው ሕገ መንግሥት በሥራ ላይ ያለው ሕጋዊውን ባንዲራ እንደያዝን የመቆየት ሕጋዊ ግዴታ አለብን። በአንጻሩ ግን፣ የፖሊቲካ ድርጅቶችና ቡድኖች እንዲሁም አክቲቪስቶች የየራሳቸውን ባንዲራና አርማ ይዘው ለመንቀሳቀስና ደጋፊዎችን ለማፍራት እኩል መብት እንዳላቸው ጠንቅቀው በማወቅ፣ ሌላውን ወገን መኮነን ብሎም ለጥል ከመዘጋጀት ግን መቆጠብ አለባቸው። ያሰኘውን ባንዲራ ይዞ መንቀሳቀስ የማንኛውም ዜጋ መብት ስለሆነ፣ የተለየ ባንዲራ ወይም የድርጅቶች አርማ ይዞ በተገኘ ግለሰብ ላይ ጉዳት ለማድረስ መሞከር በሕግ የሚያስቀጣ ወንጀል መሆኑን ድርጅቶቹ ጠንቅቀው ማወቅ ይኖርባቸዋል። ዛሬ አገራችን ያለችበት የፖሊቲካ ሁኔታ አስተማማኝ የሆነ ጅማሬ ያለው ቢሆንም ከኸያ ሰባት ዓመታት በኋላ ስንት መስዋዕት ተከፍሎበት ያገኘነውን ጊዜያዊ ነጻነት፣ በጋራ ሆነን ልዩነቶች እንዳሉን አውቀን፣ ከተቻለ ለመስማማት፣ ካልተቻለ ደግሞ ልዩነታችንን አቻችለን አብረን ያገራችን ሕዝቦች ያላንዳች ተጽዕኖና ነጻ በሆነ መንገድ የሚበጃቸውን አስተዳደራዊ ሥርዓትና ብሎም መገለጫቸው የሆነውን ባንዲራ በሕዝበ ውሳኔ እንዲያረጋግጡ ከመታገል፣ ዛሬ በፖሊቲካ ሂደቱም ሆነ በውጤቱም ላይ አንዳችም ዓይነት አዎንታዊ ጎን ሊኖረው የማይችለውን የባንዲራና አርማ ጉዳይ አንስቶ ደጋፊዎችን ማጋጨት ኃላፊነት የጎደለው ድርጊት ይመስለኛል። ከላይ እንዳልኩት ባገሪቷ ሕገ መንግሥት መሠረት ያለን ባንዲራ አንድ ብቻ ነው። ሌላው ሁሉ ድርጅቶች በራሳቸው ውሳኔ ለፖሊቲካ ዓላማቸው ስኬት ብለው የወሰዱትና ሕዝብን የሚቀሰቅሱበት መሳርያ ስለሆነ የኔ ብቻ ትክክል ነውና ያንተን ተው ማለት የዲሞክራሲን መብት ምንነት ካለማወቅ የሚመነጭ ይመስለኛል። ከዚህ በፊትም ደጋግሜ እንዳልኩት፣ ኢትዮጵያዊነትን በተመለከተ ማንም ከማንም በላይ ኢትዮጵያዊ ሊሆን አይችልም። የሁላችንም አባቶች በጊዜያቸው የነበረውን ባንዲራ እያውለበለቡ እንደየችሎታቸው ላገራችን ኅልውና ሞተውላታል። እኛም እንደየችሎታችን ላገራችን ኅልውናና ለሕዝቦቿ አንድነት እኩል እየተቆረቆርንላት ነው። ዛሬ ያገራችንን ኅልውና እያሰጋ ያለው ደግሞ የውጪ ወራሪ ኃይል ሳይሆን፣ ረሃብ፣ እርዛት፣ ሥራ አጥነትና ተማርን የሚሉት ቡድኖች የሚያካሄዱት ኢ በኔ ግምት፣ የዛሬው አንገብጋቢ ጥያቄ መሆን ያለበት፣ ይህንን ውድ ዋጋ ከፍለንበት ያገኘነውን ጊዜያዊ ድል እንዴት አድርገን አጠናክረን ወደ ቋሚነት ለማሻገር እንደምንችል፣ የሚቀጥለው ምርጫ ሰላምና መረጋጋት በሰፈነበት ሁኔታ ተካሂዶ ሕዝቡ የፈለገውን እንዲመርጥ የምናግዝበት፣ ከምርጫው በኋላ ደግሞ መደረግ ወይም መለወጥ ስላለባቸው ሕጎች የምንወያይበትን መድረክ መክፈት፣ እስከዚያው ድረስ ደግሞ እኛ ውጭ አገር ያለነው ዜጎች፣ ዶ/ር ዓቢይ ባቀረቡልን የድረሱልን ጥሪ መሠረትወዳገራችን ተመልሰን ፖሊቲካዊ ባልሆኑ ዘርፎች እንደየሙያችን ተሰልፈን ማሕበረሰባዊ ግዴታችንን መወጣት እንጂ፣ ዛሬ በሰላሙ ጊዜ እንኳን አውለብልበነው ይቅርናተጠቅልለንበትም ብንተኛ አንዲት ግራም ዳቦ እንኳ ሊገዛ የማይችለውን የባንዲራና የአርማን ጉዳይ እንደ አንድ ወቅታዊና አገራዊ አጄንዳ አቅርቦ ዜጎችን ማጋጨት የዜግነት ኃላፊነትን ምንነት አለማወቅ ብቻ ሳይሆን ታሪካዊ ወንጀልም እየፈጸምን መሆኑን ማወቅ ያለብን መሰለኝ።
Full Website