የኢትዮጵያ
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
በ2012
ዓ.ም የሚካሄደውን
አጠቃላይ ምርጫ
ለማስፈፀም የቅድመ
ምርጫ ዝግጅት ስራዎች
ሲያከናውን ከቆየ
በኋላ የምርጫ የጊዜ
ሰሌዳውን ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህ የምርጫ ጊዜ
ሰሌዳ መሰረት ምርጫው
ነሐሴ 23 ቀን 2012
እንዲካሄድ ተወስኖ
ቦርዱ በጊዜ ሰሌዳው
የተገለጹ ተግባራትን
በተያዘላቸው ጊዜ እያከናወነ
ለህዝብ እያሳወቀ
እንደቆየ
ይታወሳል፡፡፡
በዚህም መሰረት
በያዝነው መጋቢት ወር
እና በሚያዚያ 2012 ዓ.ም
፡መጠናቀቅ ያለባቸው
በርካታ ስራዎች አሉ፡፡
መከናወን ካለባቸው
ስራዎች ዋና ዋናዎቹ
የመራጮች ምዝገባ፤
የምርጫ አስፈፃሚዎች
ምልመላ፤ ስልጠናና
ስምሪት፤ የመራጮች
ትምህርት፤ ለመራጮች
ምዝገባ የሚያስፈልጉ
ቁሳቁስ ስርጭት
የመሳሰሉት ናቸው፡፡
• በኢትዮጵያ አየር መንገድ መጋዘን የሚገኙ የምርጫ ቁሳቁሶችን የማሸግ ስራ በሁለት ሳምንት ዘግይቷል፤
• የቀሪ ህትመት ውጤቶች ግዥ በቫይረሱ ምክንያት በተፈጠረ የአቅርቦት ሰንሰለት መደናቀፍ ምክንያት ተጓቷል፤
• ለምርጫ አስፈፃሚዎች ስልጠና ቁጥራቸው 1000 /አንድ ሺ/ በላይ የሚሆን አሰልጣኞችን ክክልሎች ወደ አዲስ አበባ በማምጣት የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት አልተቻለም፤• ለ 150,000 የምርጫ አስፈፃሚዎች በየክልሎቹ መሰጠት ያለበትን ስልጠና መጀመር አልተቻለም፤
• ቦርዱ የሚሰጠው የመራጮች ትምህርት ኮቪድ 19 ቫይረስን አስመልክቶ በሚወጡ የማህበረሰብ ጤና መልእክቶች ሊዋጡ የሚችሉበት እድል ከፍተኛ ሆኖ ተገኝቷዋል፡፡ የቫይረሱ ስጋት በቀጣዩ ሃገራዊ ምርጫ በአጠቃላይ በተለይም በአፋጣኝ መፈጸም ባለባቸው የመራጮች ምዝገባ፤ የምርጫ አስፈፃሚዎች ስልጠና፤ የመራጮች ትምህርት ተግባራት አፈፃፀም ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተፅእኖ አስመልክቶ ቦርዱ ከህግ አውጪው አካል፤ በጉዳዩ ላይ ከሚሰሩ የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የማህበረሰብ ጤና ባለሞያዎች፣ ከአለምአቀፍ አጋሮች እና ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ጋር ተመካክሯል፡፡ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር በተደረገው ውይይት አብዛኞቹ ፓርቲዎች የችግሩን ግዝፈት እና በምርጫ ላይ የሚኖረውን ተጽእኖ ተገንዝበው ቦርዱ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ተመካክሮ አማራጭ የአፈጻጸም አቅድ ሊኖረው እነደሚገባ መክረዋል፡፡ይሁን እና በዚህ አግባብ የሚወሰደው እርምጃ ችግሩ ከሚጠይቀው በላይ የሆነ መዘናጋት እንዳያመጣ ቦርዱ በወረርሽኙ አፈጻጸማቸው የማይስተጓጎል ስራዎችን እንዲያጠናቅቅ አሳስበዋል፡፡ ቦርዱ ለውሳኔው መሰረት የሚሆነው የዳሰሳ ጥናት በአማካሪ ባለሙያዎቹ ተሰርቶ እንዲቀርብለትም አድርጓል ፡፡ የተፈጠረው አጠቃላይ ሁኔታ ከታቀደው የምርጫ ምዝገባና ቀጣይ እርምጃዎች ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ተፅዕኖ ባግባቡ ለመዳሰስ ያስችለው ዘንድ በዳሰሳ ጥናቱ ላይ ተመስርቶ ቦርዱ ሁለት የቢሆን ሁኔታ ግምቶች (scenarios) ተመልክቷል፡፡ የመጀመሪያው የቢሆን ሁኔታ ግምት መሰረት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመግታት በኢትዮጵያ መንግስት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ለአራት ሳምንት ብቻ ማለትም እስከ ሚያዚያ 7 ሊቆይ ይችላል በሚል ግምት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ክልከላው የአራት ሳምንት ብቻ የሚቆይ ከሆነ አሁን ባለው የጊዜ ሰሌዳ ዋና የሆነውን የመራጮች ምዝገባ ቢያንስ በአራት ሳምንት የሚገፋው ሲሆን ምዝገባው ቢከናወን የማህበረሰቡ ተሳትፎ፣ የምርጫው ተአማኒነት ማግኘትን እና የኦፕሬሽን ድጋፍ የሚያደርጉ ተቋማት ድጋፍን ሙሉ ለሙሉ ማግኘትን በጣም አስቸጋሪ መሆኑን ያሳያል፡፡ ቫይረሱ በቁጥጥር ስር ካልዋለም የመራጮች ምዝገባን ማካሄድ የማህበረሰብ ደህንነትን