Back to Front Page
ከመረጣችሁት ከንጉሣችሁ የተነሣ ትጮኻላችሁ፤ በዚያም ቀን እግዚአብሔር አይሰማችሁም

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

10-21-21

የጽሑፍ ዓላማ፥

1. በአፋቸው “ኢትዮጵያ የክርስትያን ደሴት ናት፣ ኢትዮጵያ የድንግል ማሪያም የአስራት አገር ናት፣ ኢትዮጵያዊነት ፈሪሃ እግዚአብሔር ነው” እያሉ በእግዚአብሔር ስም መሸቃቀጥ የለመዱ፣ መንፈሳዊ ካባ ለብሰው ሰውን ማደናገርና ማወናበድ ስራችን ብለው የተያያዙት፣ ሰውና እግዚአብሔር የማይፈሩ፣ ሰውን እንደ ጠቦት በገመድ አስረው የሚያርዱ፣ የሚገድሉና ገድለው ወደ ወንዝና ወደ ገደል የሚወረውሩ የሰይጣን ባለሟሎች የአማራ ልሒቃን ከተጸናወታቸው ክፉ አስመሳይና አጭበርባሪ መንፈስ ይፈወሱ እንደሆነ፤

2. ትግራይ ከካርታ ለመፋቅና የትግራይ ህዝብ ስመ ዝክሩ መታሰቢያ ላይኖረው ከፖለቲከኞች እኩል የዘመተችብን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ያን እንዲሁም ወንጌላውያን አብያተ ክርስትያናት እንደ ዱላ ቅብብል በሃይማኖት ሽፋን የሚሰሩት የሴራ ፖለቲካ በተጠና መልኩ ማወቅና መረዳት ለእኛ ለተራሩ ባህላችንና ማንነታችን ጠብቀን ቀጣይ ህልውናችንና ደህንነታችን ለማረጋገጥ የላቀ ሚናና አስተዋጽዖ ስላለው አንባቢ በእውነተኛ እውቀት ለማስታጠቅ ታስቦ የተዘጋጀ ጽሑፍ ነው።

መንደርደሪያ፥ “የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ ተሰብስበው ወደ ሳሙኤል ወደ አርማቴም መጡና እነሆ፥ አንተ ሸምግለሃል፥ ልጆችህም በመንገድህ አይሄዱም፤ አሁንም እንደ አሕዛብ ሁሉ የሚፈርድልን ንጉሥ አድርግልን አሉት… እግዚአብሔርም ሳሙኤልን አለው በእነርሱ ላይ እንዳልነግሥ እኔን እንጂ አንተን አልናቁምና በሚሉህ ነገር ሁሉ የሕዝቡን ቃል ስማ ” አሉት ይላል (1ኛሳሙ 8፥ 4-8)። እስራኤላውያን፥ የሳሙኤል በዕድሜ መግፋትና የልጆቹም የአባታቸው አሰር የሚከተሉ ሆነው መገኘት አስከፍቷቸው እንደ አህዛብ የሚፈርድላቸው ንጉሥ መምረጣቸው ትክክለኛ ምርጫ እንዳይደለና ጣጣ ይዞባቸው እንደሚመጣም በሚገባ እንዳላሰቡበት በቀላሉ ለመረዳት ይቻላል። እዚህ ላይ በጥሞና ልናስተለው የሚገባ አንኳር ነጥብ ቢኖር፥ እስራኤላውያን እንደ አሕዛብ ሁሉ የሚፈርድልን ንጉሥ አድርግልን በማለት ጥያቄያቸው ሲያቀርቡና ለሳሙኤል ምርጫቸው ሲያሳውቁት ከግብጽ ምደር ቀን በደመና ሌሊት በአምደ እሳት እየመራ ያወጣቸው፣ መና ከሰማያት የምንጭ ውሃ ከአለት እያፈለቀና እያወረደ የመገባቸውና ያጠጣቸው፣ ጠላቶቻቸው ድባቅ እየመታ ለአባቶቻቸው ወደ ማለላቸው ርስት ያበቃቸው የአባታቸው አምላክ እግዚአብሔር በመጣል ነው። ወረድ ብለን በቁ. 18 ላይ ያነበብን እንደሆነ ታድያ የእስራኤል ምርጫ መዘዝ እናነባለን፥ “በዚያም ቀን ለእናንተ ከመረጣችሁት ከንጉሣችሁ የተነሣ ትጮኻላችሁ፤ በዚያም ቀን እግዚአብሔር አይሰማችሁም” ይላል። በነገራችን ላይ፥ ይህ ማለት መጽሐፍ ቅዱስ ምርጫ (Election) ይቃወማል ማለት እንዳይደለ መረዳት አስፈላጊ ነው። እያወራን ያለነው የሰው ፍላጎት/ምኞች መሰረት ያደረገ የዕለት ዕለት የህይወት ውሳኔዎች/ምርጫና (Choice) የሚያስከትለው ውጤት (Consequence) ነው። ቀጥሎ የሚቀርበው ሐታታም መንፈሳዊ ስብከትና ሃይማኖታዊ ትምህርት ሳይሆን አማኞች ሆን - አልሆን እንደ ዜጎች የዕለት ዕለት ኑሯችን ያነበብነው መጽሐፍ መነሻ ያደረገ ምርመራ ማድረግና ማካሄድ ነው።

ሐተታ፥ ይነስም ይብዛ ኃላፊነትና ተጠያቂነት የማያስከትል የህይወት ውሳኔ ወይም ምርጫ የለም። ቀለል ባለ አማርኛ፥ ህይወት ምርጫ ናት ምርጫ ደግሞ ዘር ነው። ሰው የዘራውን ነው የሚያጭድው። ይህ ማለት፥ አንድ ገበሬ ስንዴ ከዘራ የሚያጭደው ስንዴ ነው፥ ጤፍ ከዘራ ደግሞ ሊያጭደው የሚችል ጠፍ ነው። ይህ ያለና የነበረ መሰረታዊ የተፈጥሮ ህግ ነው። አንድ ገበሬ፥ ስንዴ ዘርቶ ሲያበቃ ጤፍ፤ ጤፍ ዘርቶ ሲያበቃ ስንዴ አያጭድም፤ የሚያጭደው የዘራው ዘር ነው። በአገር ደረጃ ሆነ በግለሰብ ደረጃ የሰው ህይወትና ገጽታ በተመሳሳይ የዕለት ዕለት ምርጫ ውጤት ነው። ሰላምና ዕረፍት ገንዘብህ ማድረግ ሆነ መበጣበጥና መታወክ ድንገታዊ ክስተቶች ሳይሆኑ በማወቅም ባለማወቅም በስህተትም በድፍረትም የምንወስዳቸውና የምናደርጋቸው የህይወት ምርጫዎች ውጤቶች ናቸው። በሌላ አባባል፥ የነገ ህይወታችን ዛሬ ለሚገጥመን ክስተት በማወቅም ባለ ማወቅም የምንሰጠው ምላሽ ውጤት ነው።

እዚህ ላይ፥ “ሰይጣን አሳስቶኝ ነው” የሚባል አባባል ቦታ የለውም። ይህ ዓይነቱ ምክንያት እንደ እኔ እምነት ኃላፊነት ላለመውሰድና ከተጠያቂነት ለማምለጥ የሚነገር ግብዝነት የሞላበት ኢትዮጵያዊ ባህል ነው። እኔ እሰከማውቀው ድረስ፥ ፈረንጅ “ሰይጣን አሳስቶኝ ነው” ሲል ሰምቸው አላውቅም። በስራም ሆነ በማህበራዊ ህይወት ለሚፈጠር ስህተት የእኔ ጥፋት ነው በማለት ኃላፊነት የሚወስድ ሰው እንጅ ለለፈው አስር ዓመት ሙሉ በትምህርትም በስራ ዓለምም በነጮች መካከል ስኖር አንድም ቀን አንድም አሜሪካዊ ሰይጣን አሳስቶኝ ነው! ሲል ሰምቼው አላውቅም። ሰይጣን አሳስቶኝ ነው የሚል አባባል ራሱ በፈረንጆች መዝገበ ቃላት ውስጥ የለም። እውነት ነው፥ ሰይጣን የሚለው የዕብራይስጥ ትርጉም ተቃዋሚ፣ ከሳሽ ወይም አሳች ማለት ቢሆንም ይህ ማለት ግን ሰይጣን በኳሌታትህ ይዞ አመጽ እንድትፈጽም ያደርግሃል ማለት አይደለም። ከነተረቱ፥ ሊበሏት የፈለጉ ምን ይሏታል እንደሚባለው፤ ሰው የገዛ ራሱ ፍላጎትና ምኞት እንጅ ሰይጣን እጅህን ጠምዝዞ የሚያሰራህ ኃጢአት የለም። ሰይጣን በሰው ላይ የሚሰለጥነው ፍቃድህ ስትሰጠው ብቻ ነው። ይህም፥ ሰይጣን ና እፈልግሃለሁ ብለህ በመጥራት ሳይሆን ሰይጣንን እንደ ማግኔት የሚጠራ ውስጣዊ ፍላጎታችንና ምኞታችን ነው። በመሆኑም፥ እጅ የመቆረጥ ያህል እያመመንም ቢሆን ሩቅ አይተን (ነገን እያየን) የምንወስነውና የምናደርገው የህይወት ምርጫ ዕረፍትና ሰላም፤ በይድረስ ይድረስ፣ በግድ የለሽነትና በሌሎች ምክንያቶች የምናደርገው ምርጫ በአንጻሩ መልሶ ሊያስለቅሰን እንደሚችል ማናችንም አንስተውም።

እንደ አገር በኢትዮጵያ ውስጥ የሆነ ሐቅ እንግዲህ ይህ ነው። የህወሓት መሪዎች ጨምሮ ድምጽ ሰጥተው ወደ ስልጣን ያመጡት ሰው (ዐቢይ አህመድ ዓሊ) ኢትዮጵያን ገደል እንዲከታት፣ አገሪቱ ጽልመት የማይገልጸው ቅርቃር ውስጥ ከቶ ህዝቦችዋ እንዲያጎሳቅል፣ ጦርነትና ደም መፋሰስ በምድሪቱ ላይ እንዲያንግስ ሳይሆን የህዝብ ፍላጎት ለሟሟላትና ለዲሞክራሲያዊ አሰራር ማበብ ሲባል የተደረገ እንደሆነ በሁሉም ዘንድ የታወቀ ነው። በዚህ መልኩ የተከፈተ አዲስ ምዕራፍና ጉዞ በአግባቡ መጠቀምና አለመጠቀም የአገሪቱ ህዝቦች ምርጫ በመሆኑ ግን ደግሞ ወደ ስልጣን የመጣ ቡድን ሆነ ህዝቡ የተገኘ ዕድል በአግባቡ ለመጠቀም ባለመታደሉ፤ የተገኘ ዕድል ለበለጠ ልማትና ለውጥ ከመጠቀም ይልቅ ወደኋላ በመመለስ አንድን ህዝብ እንደ ህዝብ በጠላትነት በመፈረጅ፣ ህልውናው ለማክሰምና ለማጽዳት ምርጫው በማድረጉ ይሄው ዛሬ በየቦታው የሚታይ ያለ ደም ማፋሰስና ዕልቂት ለማየት በቃን።

ትናንት ፈጽሞ ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ የተፈረደረበት ህዝብ የትግራይ ህዝብ ብቻ ነበርና ኢትዮጵያ በንጹሐን ደም ሰክራ በተናቸው! አጠፋናቸው! ቺርስ እየተባለ ሽር-ብትን ሲባል ይሄው ወያነ ትግራይ አፈሩን አራግፎ ዳግም ሲነሳ ደግሞ በኢትዮጵያ በኩል “የህልውና ጦርነት” የሚል አዲስ ስያሜ ተሰጥቶት አገሪቱ በጦርነት ብቻ ሳይሆን እስከ ዛሬ ዕለት ጦርነቱ ያልደረሰባቸው አከባቢዎች ሳይቀሩ ጦርነቱ ያስከተለው የኢኮኖሚ ውድቀት ሰላባ ሆነው በዳቦ እጦት እየታሹ ይገኛሉ። የአዲስ አበባ ከተማ ነዎሪዎች ጨምሮ ሚልዮኖች ኢትዮጵያውያን የሚላስ የሚቀመስ አጥተው በርሃብና በችጋር እየተፈገመገሙ በሚገኙበት ሰዓትም የሰው ክብር የሌለውና ያልፈጠረበት ህጋዊ ሽፍታ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ሚልዮን ዶላሮችን ወጪ አድርጎ ሽፍትነቱ ህጋዊ ለማድረግ ቢሞክርም ከዚህ ቀደም “እናት” በማለት የጠራው IMF የተባለ የገንዘብ ተቋም ኢትዮጵያን እንደ አገር ፈልጎ ስላጣት ስለ ኢትዮጵያ ለመናገር አቸገራለሁ፤ አትታየኝም ባሏል። በእውነቱ ነገር “ኢትዮጵያ አገሬ” ለሚል ሰው ከዚህ በላይ አሳፋሪ፣ ውርደትና ቅሌት የለም። ይህ የIMF መግለጫ ኢትዮጵያ፥ ከጨርቅና ከወረቀት የሚሰራ ግድግዳ ላይ የሚንጠለጠው የዓለም ካርታ ውስጥ የምትገኝ ስዕል ከመሆኗ አልፎ እንደ አገር ህልውና እንደሌላት ይህ በቂ ማሳያ ነው።

አምላኬ ሰው በልኬ እያለክ! እያልክ ስትዘፍን ያላፈርክ አሁን ምን ያስለቅስሃል ?

የአማራ ልሒቃን፥ ትንሽ ነካ ሲያደርጉት አገር ምድሩን በጩኸት እንደሚቀውጠው ቀጣፊ የሰፈር ልጅ እንዲሁ አይደለም ምክንያት አግኝተው በባዶ ሜዳም ሰማይ ይያዝልን እያሉ ምላሳቸው ከትናጋቸው እስኪጣበቅ ድረስ መጮህና ማለቃቀስ የባህሪያቸው ነው። ሰዎቹ የድራማ ህይወት የሚኖሩ ሰዎች ከመሆናቸው የተነሳም እንደ ባልታት ሲገለባበጡ ማየት የተለመደ ነው። ሰዎቹ ሌላ አበረኛ ባህሪይም አላቸውም፤ ይኸውም፥ የይሁዳ መንፈስ የተጋባባቸው ኃፍረት የማያውቁ ሰዎችም ናቸው። የሚፈልጉት ካገኙና ሆዳቸው ከሞሉም የእናታቸው ልጅ (ወንድማቸው) የሚሸጡ ክህደት ያሰመጣቸው ሰዎች ናቸው። ትናንት የነጻነት ተጋይ እያሉ ሲያቆላጳጵስዋቸው የኖሩ ወንድሞቻቸው ዛሬ ውህኒ ቤት አስወርውረው ስመ ዝክራቸው አያነስዋቸውም። እነዚህ ሰዎች ናቸው እንግዲህ ትናንት “አማራ ታሪክ ሰራ” እያሉ መለከት ሲነፉ ሰዎች ዛሬ ደግሞ የአዞ እምባ እያነቡ በጦር ሜዳ ሲሸነፉ ወደ በፖለቲካ ዲስኩ እዚህ ላይ ሲመቱ ወደ ኃይማኖት እየተገለባበጡ “ይግባኝ ለክርስቶስ! ይግባኝ ለተክልዬ!” እያሉ ልባችን እያወለቁ ያሉ ነፈዞች። ደግነቱ፥ ክእንግዲህ ወዲህ በሃይማኖት ሽፋን በእግዚአብሔር ስም የሚሰራ ድራማና ሴራ ተታሎ በአማራ ልሒቃን ወጥመድ የሚገባ ህዝብ የለም። አብያተ ክርስትያናቱ በተለይ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያንና ወንጌላውያን አብያተ ክርስትያናት በሃይማኖት ሽፋን እያካሄዱት ያለ የወንጀል ድርጊትና ዘመቻ መመልከት ግን አስፈላጊ ነው።

ኢትዮጵያዊ ዓይነቱ ሰው ፈጣሪ የማይሰማው የጸሎት ዓይነት እንዳለ መስማት ሆነ ማወቅ አይፈልግም። የሚፈልገው፥ እንደ ሜዳ አህያ የፈለገውን እየሆነና ያሻውን እያደረገ አንድ ነገር ሲደርስበት ደግሞ እኔ ሰው አልገደልኩ፥ እንዲህ ያለ ነገር በእኔ ላይ እንዴት ይሆናል? እያለ ጽድቁን በመቁጠር፣ ሻማና ጥዋፍ በመወርወር አንድም በልዩ ልሳን ስለ ጸለየ ብቻ የፈለገው ነገር ማግኘት እንደሚችል ነው ያምናል። ይህ ግን ፍጹም ስህትት ከመሆኑ በላይ እንዲህ ያለ እምነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንዳይደለ ስገልጽሎት በአክብሮት ነው። አንድን ህዝብ እንደ ህዝብ ጠላቴ ነው ብለህ ባገኘኸው አጋጣሚ ሁሉ የሰው ሀብትና ንብረት እየዘረፍክ፣ ሰው ገድለህ ወደ ገደልና ወደ ወንዝ እየወረወርክ፣ ሬሳ እየጎተትክ ደስታህ የምትገልጽ ሆነህ ስታበቃ ካንተ የበረታ ደግሞ በተራው አንተን ሲያሳድድ፥ “ይግባኝ ለክርስቶስ - ይግባኝ ለእመበቴ፣ ይግባኝ ለአቡየ - ይግባኝ ለተክልየ” እያልክ ማላዘን፣ ማለቃቀስና ተጎንብሰህ መጮህም ቢሆን አንዳች የሚፈይደው የለውም ብዬ ስጽፍሎት በፍቅር ነው። ምን ነው? ቢሉ፥ እንዲህ ያለ የግብር ይውጣ በደምና በነውር የታነቀ ጸሎትና ጩኸት የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር ፈጽሞ አይሰማውምና። ሌላው፥ ፆምና ፀሎት ማለት በአጭሩ ከክፋትና ከአመጻ መራቅ ማለት እንጅ ጩኸትና ዋይታ ማለትም እንዳይደለ ሊገባን ይገባል። በክፋትና በተንኮል፣ በጥላቻና በጸብ፣ አመጽና በደም ተጨማልቀህ ስታበቃ የሚደረገው ጾም ሆነ ጸሎት ከንቱ ልፋት ድካምም ነው። በዚህ አጋጣሚ፥ ፈጥሪ ለምን አይሰማንም? የምትል ሰው ካለህ በእውነቱ ነገር፥ ፈጣሪ ሳይሆን የማይሰማው እንተ ነህ የተሳሳተ አድራሻ ይዘህ ሄደህ የተሳሳተ ፌርማታ ላይ ወርደህ እየተንቀዋለልክ ያለኸው። ተመለስና ትክክለኛ አድራሻ ይዘህ ትክክለኛ ስፍራ ላይ ቆመህ አቤት በል (ከአመጽ፣ ከክፋትና ከጥላቻ ራስህን ቀድስ) ያን ጊዜ እግዚአብሔር ውሸታም ይሁን። ኣብያተ ክርስቲያናቱ ታድያ ይህን ሐቅ ሳያውቁ ቀርተው ሳይሆን የሚዘውራቸው የክፉ መንፈስ እውነቱን አስጥሎ ጽድቃቸው ስላሳጣቸው ብቻ ነው።

Full Website