Back to Front Page

እንዲህ ያለ ነገር በዘራችሁ አይድረስ! ማለት አሁን ነው

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

10-15-21

ትርጓሜ፥ ልሃጫም ምንሊካዊ አስተሳሰብና እምነት ማለት ለዚህ ትውልድ የማይመጠን፣ የድህነትና የድንቁርና የጦርነትና የእልቂት የሞትና የደም መፋሰስ የኋላቀርነትና የተመፅዋችነት የሁከትና የግርግር መዝገብ የሆነ፥ ዘመኑ ያለፈበት፣ የበከተ፣ መናኛ፣ አብሮነትና እኩልነት መከባበርና መጠባበቅን የሚፀየፍ፣ በህዝቦች በተሳትፎ የማያምን፥ ፀረ-እኩልነት፣ ፀረ-ፍትህ፣ ፀረ-ዲሞክራሲያዊ አመለካከትና አስተሳሰብ የሆነ ጨፍላቂ የአፈናና የግፍ አሰራር/አገዛዝ ለማለት ነው።

ወያነ ትግራይ፥ እንዴት እዚህ ውስጥ ልንገባ ቻልን? መውጫው ምንድ ነው? አንድም፥ እንደዚህ ያለ ነገር ላይደገም ምን መደረግ አለበት? ቀጣይ ጉዞአችንስ ምን ይሁን? ተብለው ለሚነሱ ጥያቄዎች በጥሞና አስቦበት ዘመን ተሻጋሪ የመፍትሔ ሃሳብ ወይም ምላሽ መስጠት ከቻለ ዳርጋ ዘይሞትና!

ሐተታ፥ ስለ ጦርነት አስከፊነትና አውዳሚነት አንስተን/እያነሳን፥ መጡብን እንጅ አልሆንባቸውም፣ ተኮሱብን እንጅ አልቶኮስንባቸውም፣ ጦርነቱን የጀመሩት እነሱ እንጅ እኛ አልጀመርነውም ወዘተ እያልን ንጽህናችን ለማሳየት፣ ለማሳወቅና ለመግለጥ ብዙና ጥቂት የምንልበት ሰዓት አልፏል። ጦርነት የሰው ህይወትና ንብረት እንደሚበላ፣ ጦርነቱ እኛ እንዳልጀመርነውና ወራሪ ኃይሎች አማራጭ አሳጥተውን ህልውናችንና ድህንነታችን ለመጠበቅና ለመከላከል ተገደን የገባንበት ለመሆኑ እኛም እናውቃለን - ከዚህም ከዚያም ተሰባስበው መጥተው በዓላማና በዕቅድ ወረራ የፈጸሙብን ህዝቦችና አገራትም ጠንቅቀው ያውቃሉ። የጦርነት አውዳሚነት በተመለከተም አመል ያልበት ካልሆነ በቀር ለትግራይ ህዝብ ስለ ጦርነት አስከፊነት አፉን ሞልቶ መናገር የሚደፍር ቢኖር በእውነቱ ነገር ጦርነትን የማያወቅ ዜጋ ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው። ቢሞክርም ለኳየሩ መስበክ በመሆኑ እዚህ ላይ የምናጠፋው ጊዜ አይኖርምና በቀጥታ ወደ ፍሬ ነገራችን እንግባ።

1. እንዴት እዚህ ውስጥ ልንገባ ቻልን?

እአአ 1991 ዓ/ም የተመታ አመለካከት እንዴት አንሰራራ? የሚለው ጥያቄ ለጊዜው ወደ ጎን ትተን ተንሰራርቶ የፈጀን አስተሳሰብና አመለካከት ላቶክር። ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ አፈ-ህጻን ዐቢይ አህመድ ዓሊና ልሃጫሞቹ የአማራ ልሒቃን፥ ትግራይን ከካርታ የትግራይን ህዝብ ስመ ታሪኩ መታሰቢያ ላይኖረው ለመደምሰስና ለመፋቅና፥ ከሱዳን መንግሥት ጋር መክረውና ዘክረው፥ ከምዕራቡም ከምስራቁም ርዕሰ ኃያላን አገራትና መንግሥታት ይሁንታና ፈቃድ አግኝተው፣ የሶማሊያና የኢምሬትስ ድሮንና የሰው ኃይል (ሠራዊት) አስከትለው ትግራይን በአራት አቅጣጭ በመክበብና በመነጠል የፈጸሙት በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም፣ የጦርና የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ማናችንም ልናስበው በማንችለው ሁኔታ እውን ሆኖ አይተናል። ጥያቄው፥ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ኢትዮጵያ በዚህ ዘመን ሊደረግ ቀርቶ ፈጽሞ የማይታሰብ ግፍና በደል ትፈጽምብን ዘንድ ጉልበት የሰጣት ነገር ምንድ ነው? የፈጸመችብን አረማዊና ሰይጣናዊ ግፍና በደል በጠራራ ጸሐይ እንድትፈጽምብን እንዴት አቅም ልታገኝ ቻለች? የሰምንት ዓመት ህጻን ልጅ የሚደፍር፣ የሰማኒያ ዓመት የዕድሜ ባለ ጸጋ የሚያስነወር፣ ዘመናቸው በሙሉ እግዚአብሔርና የእግዚአብሔር ቤት ከማገልገል ውጭ ሌላ ዓለም የማያውቁ መነኮሳት የሚጋሰስ፣ አንዴት ሴት ለአስራ አምስትና ለሃያ እየተፈራረቁ የሚማግጡ፣ አባት ከሴት ልጁ ጋር እንዲተኛ ብረት የሚደቅኑ፣ ሰውን እንደ ጠቦት በገመድ አስረው የሚያርዱ፣ ሰው ገድለው በእሳት የሚያነዱ፣ ወደ ገደልና ወደ ወንዝ የሚወረውሩ ወታደሮች እንዴት ልትፈጥር ቻለች? ይህን ሁሉ ግፍና በደል እያየ በደስታ የሚዘልና ዊስኪ የሚራጭ ህዝብስ እንዴት ልታፈራ ተቻላት? የሚል ነው።

እአአ ግንቦት 2020 ዓ/ም በአሜሪካን አገር ለህተመት የበቃ “አዲዮስ ኢትዮጵያ” የተሰኘ መጽሐፌ ላይ እንዳሰፈርኩት፥ በትግራይ ላይ የተፈጸመ የዘር ጭፍጨፋ፣ ያየነው እልቂትና ውድመት ሁሉ ከሰማይ የወረደ ቁጣ እንዳልሆነና የአንዲት ሌሊት ፀብና ኩርፊያ ውጤት እንዳይደለምም አትቼ ነበር። ይልቁንም፥ እነዚህ የጥፋትና የትምክህት ሃይሎች የትግራይ ህዝብ በዚህ ደረጃ ሲጨፈጭፉ፣ ህጻናትና ሽማግሌዎቻችን ወጣቶችና ጎልማሶቻችን ሲረሽኑ፣ ዲያቆናትና ካህናቶቻችን ሲያርዱ፣ አብያተ ክርስቲያናት በታንክ ሲያፈራርሱ፣ ሴቶች እህቶቻችንና እናቶቻችን እንደ ሰዶምና ጎመራ ሲያራክሱና ሲያስነውሩ፣ ፋብሪካዎቻችን ሲያጋዩ፣ ሹካና ማንኪያ ድስትና መጥረጊያ ሲዘርፉ፣ የህዝብና የመንግስት ንብረት ሲያወድሙ፣ ከተሞቻንን በእሳት ሲያነዱ፣ ከጥይት ያመለጠ ህዝባችን በምግብና በመድኃኒት እጦት እንደ ቅጠል ሲያረግፉ እንዲሁ ከመሬት ተነስተው ሳይሆን፥ ትምክህተኛና ልሃጫም ምንሊካዊ አስተሳሰብ የጸነሰው ቅናትና ምቀኝነት ያዋለደው ትግራይ ጠል የጥላቻ ፖለቲካ ነው። ቀለል ባለ አማርኛ፥ የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ለደረሰበት የዘር ጭፍጨፋና እልቂት ዋና ተጠያቂና ምንጭ በዋናነት የትግራይ ህዝብ ህልውና እንደ ኮሶ መድኃኒት የሚመረራቸው፣ ኢትዮጵያን የመግዛት መለኮታዊ ስልጣን ተሰጥቶኛል፣ ስዩማነ እግዚአብሔር ነን፣ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋላና ሻንቅላ እያልኩ እንዳልገዛቸው እንቅፋት ሆኖብኛል፣ ትግራይና ትግራዋይ የሚባል ህዝብ ሳናጠፋ የትግራይ ሀብት ሀብታችንና ገንዘባችን ማድረግ ሆነ የአባታችን የምንሊክ ህልም ልናሳካ አንችልም ብለው የሚያምኑ
Full Website