mahbereseytan@gmail.com

ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ ዐቢይ አህመድ ዓሊና ምዋርተኞቹ የአማራ ልሒቃን

ገቢ የሚያደርግ ኃይል ሌላ ምንም ሳይሆን ወያኔ ትግራይ ነው

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል 04-30-21

እ.አ.አ ከ1991ዓ/ም ማለትም ከሶቬት ህብረት መደርመስና መበታተን ጀምሮ የዓለማችን አሰላልፍ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ ከተለወጠ በኋላም ቢሆን ርእሰ ኃያላኑ ላለፉት ሣላሳ ዓመታት በምስራቅ አፍሪካ በተለይ ኢትዮጵያን እንደ መሳሪያ (proxy) በመጠቀም በቀጠናው የሚኖራቸው ጥቅም በማስጠብቅ ረገድ ከሞላ ጎደል ስኬታማ ነበር ቢባልም፥ ርእሰ ኃያላኑ ኢትዮጵያ በአጋርነት ለማሰለፍ የተቻላቸው ያህል ግን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮች ገብተው እንዳሻቸው የሚፈተፍቱበት፣ ኢትዮጵያ ራስዋን የሚመዘብሩበት አቅም ግን ፈጽሞ አልነበራቸውም። ርእሰ ኃያላኑ ቀጠናው በሚፈልጉት መልክና ቀርጽ ለማስያዝና ለማበጃጀት ያስችላቸው ዘንድ ኢትዮጵያን እንደ ሉዓላዊት አገር በመቀበልና በማክበር በአጋርነት ማጨትና ማሰለፍ ማለትና አገሪቱ ራስዋ የርእሰ ኃያላኑ ህቡእ አጀንዳ ሰለባ መሆንና ማድረግን ሁለት ጽንፍ ናቸው።

ኢትዮጵያን እንደ ሉዓላዊት አገር በመቀበልና በማክበር በአጋርነት ማጨት፣ ማሰለፍና በቀጠናው ለጋራ ጥቅም (የተጠቃሚነት መጠን ቢለያይም) አብሮ መስራት ማለት በሁለቱም አገራት መካከል የሚኖሮው መልካም ግኝኑነት መሰረት ያደረገ ሰጥቶ መቀበልን የሚያሳይ ሲሆን፤ ሁለተኛውና ሌላኛው ግንኙነት ግን፥ የአንዲት አገር ውድቀትንና ኪሳራን ተከትሎ የሚፈጠር ወዶ ገብነትና የተመጽዋጭነት ዕጣ ፈንታ የሚያሳይ ነው። ይህ ሁለተኛ መደብ ቀለል ባለ አማርኛና በምሳሌ የተመለከትነው እንደሆነ፥ ባልበሰለ ሰው በዐቢይ አህመድ ዓሊ እየበሰለች የምትገኘው፣ ህልውናዋ ግድግዳ ላይ በሚንጠለጠል የወረቀት ካርታ ያለፈ እንደ አገር ህልውና የሌላትና ያበቃላት፣ በሁሉም አገራዊ መስኮች መቀመቅ ውስጥ የገባችው፣ በነጋ በጠባ ቁጥር የዜጎችዋን ሞትና እልቂት በሰበር ዜና ማብሰር የተለመደ የስራ ጸባይ የሆነባት የደም መሬት ጋለሞታይቱ ኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ በገሃድ የሚተርክ ነው። ከሊፋ ቢን ዛይድ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብሎ በአራት ኪሎ ቤተ መንግስት ሲመላለስ ካላየሁ የሚል በእንቅልፍ ልቡ የሚመላለስ ሰው ካልሆነ በቀር፣ አንድም፥ ‘ማፈሪያ’ ማለትም ‘መመኪያ’ ማለት አይደለምና ኢትዮጵያ ሲባል “የጥቁሮች መመኪያ” የሚለው የአዝማሪዎች ትርክርት እንደ እናትህ ጡት እርሳው። አድዮስ ኢትዮጵያ!

ከምዕራቡ ዓለም እጅ ይልቅ የወያነ ትግራይ እጅ ትከብዳለች

በትግራይ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀልና ስለ ሰብአዊ መብት በጠበቅና መከበር ግድ ይለናል በማለት በተገኘ አጋጣሚ ሁሉ ስለ ፍትህ፣ ስለ ዲሞክራሲና ስለ ነጻነት ተናግረውና አውርተው የማይጠግቡ የሚታወቁ በኢኮኖሚያዊ ቁጠባቸው የበለጸጉና በወታደራዊ አቅማቸው ፈርጣማ የሆኑ መንግስታትና አገር አዝጋሚ አሰራርና የኤሊ አካሄድ ዓላማ በሚገባ ልንረዳውና ሊገባን ይገባል። ዐቢይ አህመድ ዓሊ የውስጥም የውጭም አገራትና መንግስታት አሰልፎ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጸመው ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ወንጀልና የኃያላኑ መንግስታትና አገራት የግብር ይውጣ አሰራር፤ አንድም፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊና ምዋርተኞቹ የአማራ ልሂቃን በዓለም ማኅበረሰብ ዘንድ ርጉም ከመ ሰይጣን ውጉዝ ከመ አርዮስ! ተብሎ ፈጽሞ የተለየና የተወገዘ የሰው መጨረሻ ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር ግንባር በመፍጠር በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈጸሙት ያለ የዘር ማጥፋት ወንጀልና የኃያላኑ መንግስታትና አገራት ይህን የመሰለ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም የወንጀሎች ሁሉ አውራ የሆነ ወንጀል በአስቸኳይ መጨረሻ እንዲኖረውና የዐቢይ አህመድ ዓሊና የኢሳይያስ አፈወርቂን አሳዳጊ የበደላቸው እጆች በብረት ሰንሰለት ጠፍረው ፍርድንና ፍትህን ለማድረግ የሚያስችላቸው የመረጃና የማስረጃ እጥረት ስለገጠማቸውና ስላላቸው ሳይሆን አገራቱ ላለፉት ሠላሳ ዓመታት የተዘጋባቸው በር ማለትም በኢትዮጵያ ጥቅማቸውን ለማስከበር አገሪቱ አሁን የምትገኝበት የተመሰቃቀለና የለየለት ቀውስ የተሻለ ሁኔታ/አጋጣሚ ሊፈጠር አይችልምና በትግራይ መሬት ላይ እየተፈጸመ ያለ ወንጀል የዘር ማጽዳት ወንጀል መሆኑን በይፋ የታመነበት የትግራይ ህዝብ ሞትና እልቂት እንደ መሳሪያ በመጠቀም ለራሳቸው ጥቅም መጠበቅ መጠቀሚያ እያደረጉትና እየተደራደሩበት ስለሆነ ነው። ይህ ማለት ግን ሳይማር መጠሪያው ያሳመረና ሳይቀባ የተሾመ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ሆነ ምዋርተኞቹ የአማራ ልሒቃን ከፍትህ ያመልጣሉ ማለት አይደለም።

v መስዋዕትነት መጎናጸፊያው ያደረገ፣

v ጽናትና ቁርጠኝነት ምልክቱ የሆነው፣

v ሲታገል ለመጣል የሚታገል፣

v በቁጥር ጥቂት ሆኖ ሳለ በፈረሰኛ ብዛት የሚመኩትን በማጥመልመልና በማሽመድመድ የታወቀ፣

v ክፉ ቀን እንደ መቀነት የሚታጠቅ፣

v ትጥቁና ስንቁን ከጠላት የሚቀበል፣

) በማለት ያለ ግብዣ በራሱ ጊዜ ተጠራርቶ የትግራይ መሬት የገባ ወራሪ ኃይል ሁሉ የትግራይ መሬት መቀበሪያቸው ሲያደርገው ሰውዬው (ዐቢይ አህመድ ዓሊን) የወደቀና የተጣለ ሆኖ ሳለ ደጋግፈው ያቆሙትን፣ በትግራይ ህዝብ ሞትና እልቂት የራሳቸው ጥቅም ለማስከበር ጊዜው አሁን ነው! በማለት እየተረባረቡ የሚገኙ ርዕሰ ኃያላኑ ወደው ሳይሆን ተገደው ገቢ ያደርጉታል። የወያነ ትግራይ እጅ በጠላቶቹ ላይ ስትከብድ፣ የትግራይ ህዝብ በልጆቹ የህይወት መስዋዕነት በድል ማማ ላይ ሲቀመጥ እንደ ኤሊ እየተራመዱ ያሉትን ኃያላን አገራትና መንግስታት ሁሉ እንደ ጥንቸል ይፈጥናሉ።
Full Website