ተኗል በኗል፣ ትንኝ አክሏል በረሮ ሆኗል በሚሉ ፓለቲካዊና ወታደራዊ ሳይንስ ባልነካቸው ተራ የመንገደኛ ቃላት ትልልቅ ነን የሚሉ ግን በቅጥፈታቸው ግርምት በሚያጭሩ ሰዎች ሲብጠለጠል የከረመው የህወሓት አመራርና የትግራይ መከላከያ ሰራዊት ሰዎቹ የሚናገሩት ሁሉ ከእውነት የራቀ መሆኑን በተግባር ማሳየት ሲጀምር ጉድ የሚያሰኙና ይሉኝታቸውን ቁርጥም አድርገው የበሉ ነገሮች መከሰት ጀምረዋል። ትግራይና መሪዎቿ ከምድረገፅ የተደመሰሱ መስሏቸው መለኪያ ሲያጋጩ፣ ዊስኪ ሲራጩ፣ ስለሚቀጥለው ኢላማቸው እቅድ ሲነድፉ፣ ከደስታቸው ብዛት የተነሳ ልሳናቸው ተዘግቶ ዝም ያሉ፣ መስቀልን እንደ ሽጉጥ እያወዛወዙ ቀረርቶን በቅዳሴ ሲያሰሙ የነበሩት አሁን አይናቸውን በጨው ሙልጭ አድርገው አጥበው "ወንድማቸው" ለሆነው ለትግራይ ህዝብ እንደሚሳሱለት በነዛ በትግራይ ላይ ምፅአት ሲያውጁ በነበሩት ሚድያዎች ለሰሚው እስኪታክት ድረስ እየተረኩ ነው። በትግራይ ውስጥ የአማራንና የኤሪትርያ ትግራይን የማጥፋት ህልም በሚፈፅሙና በሚያስፈፅሙ የአራዊት መንጋ ስድስት ወራትና አሁንም ቀጣይ የሆነው አረመኔያዊ ድርጊት ለመዘርዘር አንድ አምድ ይቅርና በመቶ ወፍራም ቅፃች ተተርኮ የሚያበቃም አይደለም። ትግራይ ውስጥም ሆነ ከትግራይ ውጪ የትም የአለም ክፍል የሚኖረው ትግራዋይ የሚብሰለሰለው በደረሰበት ዳር ድንበር የሌለው ሰቆቃ ብቻ አይደለም። ከአካላዊ ጥቃቱ በላይ በእጅጉ የሚያመውና የአእምሮ ቁስል የሆነበት ከእንደዚህ አይነት የዲያብሎስ ዘሮች ጋር ለነዚህ ሁሉ ምእት አመታት እንዴት አብሮ ሊኖር እንደቻለ ነው። የትግራይ ህዝብ ዝምታው የመነጨው እንደ በሬ ከአራጁ ጋር በሃይማኖት ተቃቅፎ ሙሉ እምነት አሳድሮ የኖረባቸው ዘመናት የራሱ አስከፊ ዝንጋታዎች መሆናቸውን አምኖ ስለተቀበለ ነው። በትግራይ ላይ የተተገበረው ሰይጣናዊ አላማ ሲቀለበስና፣ አማራው የእጁ ሆኖ በቤኒሻንጉል፣ በቅማንት፣ በኦሮሞ በያለበት መገደልና መዋከብ ሲበዛበት ትግራይ ውስጥ ስድስት ወር ሙሉ እስካሁንም ድረስ ሲሰራ የከረመው እንደ ሆሊውድ ተከታታይ ፊልም ቆጥሮ የትግራይን ህዝብ በኦሮሞ ላይ ሊያነሳሳ የሚድያ ዘመቻውን ተያይዞታል። አይኑን ጨፍኖ ትግራይን ሲያጠፋ የነበረ ይመስል አይኑ "ሲበራለት" የተፈፀመው ግፍ ወለል ብሎ ታየውና የውሸት ሙሾ ያወርዳል። አማራ አይኑ "የበራው" በማናለብኝነት ራሱ ትግራይ ላይ በፈፀመው ድርጊት ለብቻው መቅረቱ ስላየ ነው። የትግራይ ህዝብ ከኦሮሞዎች ጋር ያሉት አንዳንድ ብዙም መሰረታዊ ያልሆኑ ልዩነቶች እንደተጠበቁ ሆነው አንድ የሚያደርገው አንድ ግዙፍ ነገር አለ። ይህም የራስን እድል በራስ መወሰን የሚለው መርሆ ነው። ከአስተሳሰብ አንድነት የበለጠ ምን ቁም ነገር አለ? የትግራይ ህዝብ ከአማራ ጋር አለ የሚባለው የሃይማኖት፣ የታሪክና የባህል ጋርዮሽ የአስተሳሰብ አንድነትን አላመጣም። ከትግራይ ጋር ከሚያመሳስለው ይልቅ የሚያለያየው ነገር የሚበዛው የኦሮሞ ህዝብ ይህ ልዩነት የአስተሳሰብ አንድነት እንዳይኖረው አላደረገም። አማራ አሃዳዊነትን፣ ትግራይ ፌደራላዊነትን ሲያራምዱ ደም የተቃቡ አስተሳሰቦች መሆናቸው ስውር አይደለም። በዚህ ሁኔታ ላይ የአማራና የትግራይ "ወንድማማችነት" ጉንጭ አልፋ ክርክር ነው። የህወሓትና የትግራይ ብልፅግናን አባላት ተጋሩ ስለሆኑ ወንድማማች ናቸው እያሉ መፈላሰፍ እንደማይቻለው ሁሉ አሃዳዊያን አማሮች በራስ እድል በራስ መወሰን መርህ መሰረት ምርጫ ያካሄደችውን ትግራይን ለመደምሰስ የፈፀሙት ድርጊት ወንድማማችነት የሚሆንበት ምክንያት የለም። የትግራዩ ወረራ ከተጀመረ ጀምሮ ምንም ልዩነት የሚባል ነገር የሌላቸው የአማራ ልሂቃን የሚያቀርቡትን ግፋዊ የሆነ ትንተና ቆሽታችን እያረረ ስናዳምጥ ቆይተናል። ከመብዛቱና ጭንቅላትንን ከማሳመሙ የተነሳም ተጋሩ መከታተል ያቆሙባቸው ሚድያዎች በርካታ ናቸው። እነሱን ከማዳመጥ ማእከላዊ ምርመራ ውስጥ ገብቶ ወፌላላ መቀጥቀጥ በምን ጣእሙ። በተቃራኒው በርካታ የኦሮሞ ልሂቃን በቴሌቪዥን መስኮት እየቀረቡ ተቃውሞ የገልፁበት ሁኔታና ለተጨነቅነው ተጋሩ ያደረጉት የመንፈስ ድጋፍ ከቶ ሊረሳ አይችልም። በትግራይ ውስጥ የአማራና የኤሪትርያን እንጂ ኦሮሞዎች ፈፀሙ የተባሉበት የግፍ ዜና አልሰማንም። የተማረከው ኦሮሞ ኮሎኔል በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ስላለው ግፍ እንባ እየተናነቀው የተናገረውም የኦሮሞዎችን አስተሳሰብ የሚወክል ነው። ጃዋር በብልፅግና እስር እየተሰቃየም ያገኘውን አጋጣሚ ተጠቅሞ ወረራውን አውግዟል። የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ወረራውን በማውገዝ ተደጋጋሚ መግለጫዎች ማውጣቱ ትልቅ አለኝታነት ነው። ይህ ለትግራይ ወሳኝ ጊዜ ነው፣ ወዳጆቿንና ጠላቶቿን የለየችበት! የመከራ ጊዜ ጓደኛ ነው እውነተኛ ጓደኛ። ተጋሩ ኦሮሞዎች በአሃዳዊነት ላይ ያነሱትን ዱላ የሚቃወሙበት ምንም ምክንያት የላቸውም፣ ይልቁንም ደግፎ ትግሉን ማጋጋል እንጂ። አማራ ይሁን ሌላ አሃዳዊነትን አንግቦ መንገድ ላይ የሚገተር ከሆነ ለሚደርስበት ችግር ዋናው ተጠያቂ ራሱ ብቻ ነው። የብልጠት ጩኸት የትም አያደርስም። አማራ ጨፍልቆ ሲገዛው ኖሮ አሁንም የአማራ አገዛዝ ሱስ አለበት ብሎ የሚያስበው ከትግራይ ውጪ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ "ትግራይ እንኳን አጠፋህልን እንጂ ሌላ ሺህ አመት ብትገዛን ደስታችን ነው" ብለው ለዙፋን ያበቁኛል የሚል የአማራ ምሁር እስከ መሃይም ድረስ የሚጋራው የቁም ቅዠት አለ። የዚህ ቅዠት ክንብንቡ ኢትዮጵያዊነት ነው። አሁን በዚህ ከማይታለለው የትግራይ ህዝብ ውጪ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የአማራ እንቅስቃሴ የራሱን አገዛዝ ለመመለስ ሳይሆን ኢትዮጵያን ለማዳን እንደሆነ ያስባል። እውነታው ግን በአማራ ከተሞች በተካሄዱት ሰልፎች ላይ ገሃድ ወጥቷል። "ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል" እንደሚባለው የአማራ ሰልፈኞች "አማራ ኢትዮጵያ ነው፣ ኢትዮጵያ አማራ ነው፣ እዎ አማራ ነፍጠኛ ነው" እያሉ ሲጮሁ ውለዋል ሰንብተዋል። ልብ በሉ አማራ ነፍጠኛ አልነበረም አሁንም አይደለም ብሎ ማስተባበል ያለ ነገር ነው። ነፍጠኝነት ቀጥታ ትርጉሙ ጠመንጃ ያዥነት ቢሆንም በህዝብ ላይ ከፍተኛ በደል ላደረሰ ጨቋኝና በዝባዥ ስርአት የተሰጠ ስያሜ ነው። የተሰየመውም አሁን ሳይሆን ድሮ ድሮ ነው! አዎ አማራ ድሮ ነፍጠኛ ነበር አሁን ግን አይደለም ማለትም የተሻለ ነው። አማራ አሁንም ነፍጠኛ ነው እየተባለ የኢትዮጵያን ህዝብ ፍቅር አገኛለሁ ብሎ ማሰብ ምን አይነት አባዜ ነው? አማራና ኢትዮጵያ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች መሆናቸውን ባደባባይ እየተናገሩ 79 ብሄር ብሄረሰቦች ህልውናቸው ሁለተኛ ደረጃ እንደሆነ የሚያስመስል ቋንቋ መናገርስ እንዴት ሆኖ ነው የአማራን ግድያ የሚያስቆመው? አማራው ትግራይ ላይ በማረሻ እየወጋ ራሱ በመርፌ ሲነካ ከትግራይ በላይ የሚጮህበት ምን አይነት የማደናገር ስራ ነው? ይህንን የሚያይና የሚያስተውል ሰውስ አማራን እንደ ጅራፍ ቆጥሮ አዘኔታ ይኖረዋልን? ከሩቅ የሚሰማው ጀርባው እየተለተለ ያለው አራሽ በሬ ሳይሆን የተልታዩ የጅራፍ ጩኽት ነው። አማራ ሆይ ሌላ ምንም ነገር ቢጠፋ ይሉኝታ የሚባል ነገር እኮ አለ! ሽመልስ አብዲሳ የብልፅግና ካድሬ ሆኖ በትግራይ ላይ የዘመቻው አላማ አስፈፃሚ በመሆኑ ይቅር የሚባል አይደለም። የኦሮሞ ህዝብ ትክክለኛ ስሜትም ወክሏል ብየ አላምንም። የኦሮሞ ህዝብ ኢትዮጵያ ብቻየን ልግዛ ብሎ የኦሮሞ ነፍጠኛነትን ለማስፈን ይታገላል ብየ አላስብም። ነፍጠኝነትን እየታገለ ራሱ ነፍጠኛ ይሆናል ብየ ለማሰብ ዝግጁ አይደለሁም። እኔ የማስበው የኦሮሞ ህዝብ የራስን እድል በራስ የመወሰን መርህ አንግቦ፣ የራሱን ድርሻ አስከብሮ የሌሎችን ድርሻ አክብሮ ይኖራል ብየ ነው። ከዚህ ውጪ ያለው ውሃ መውቀጥ ነው። ይህን ሁሉ ትንተና የዘረጋሁት አማራ አጀንዳ ለማስቀየስና አለመረጋጋት ፈጥሮ በትግራይ ላይ የሚፈፅመውን የዘር ማፅዳትና የግዛት ማጠናከር ዘመቻ ስር ሳይሰድ እንዳይከሽፍበት በመፍራት ኦሮሞ አማራን ሊያጠፋ ነው የሚለው ሽብር በመፍጠር የአማራን ህዝብ ሙሉ በሙሉ በማነሳሳት የአገዛዝ ህልሙን ለማስፈፀም ነው። ሽመልስ አብዲሳ አብዮት አደባባይ ላይ የተናገረው ነፍጠኛን ሰበርነው እንጂ አማራን ሰበርነው አይደለም። "ነፍጠኞታ" ስላለ አማራ ተብሎ ሊተረጎም አይገባም። ስለ ህዝብ መናገርና ስለ ስርአት መናገር የተለያዩ ናቸው። ናዚ ማለት ጀርመን ማለት አይደለም። ናዚን ሰበርነው ሲባል ጀርመኖች ሁሉ እንደ ስድብ ከቆጠሩት ህዝቡ ሁሉ ወንጀለኛ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ናዚ ሁሉ መሰበር አለበት። የናዚና የነፍጠኛነት ግፎች ዘመናት ስላለፉ ብቻ የሚረሱ አይደለም። በአማራ ክልል በተደረገው ሰልፍ አማራ ነፍጠኛ ነው ከተባለ ህዝቡ የስርአቱ አካል ሆኖ ግፍ ፈፅሟል ብሎ እንደማመን ይቆጠራል። ይህ ደግሞ የሚያኮራ ድርጊት አይደለም የሚያሸማቅቅና ይቅርታ የሚያስጠይቅ እንጂ። ወደ ዋናው ጉዳይ ልመለስና ቁጥር ስፍር ያልነበራቸው የትግራይ ተወላጆች ሲያስቡ የኖሩት ከአማራ ጋር ያለው የሃይማኖት፣ የባህልና፣ የስርወ ቋንቋ ትስስር በራሱ ዘላቂ የወንድማማችነትና የእህትማማችነት ስሜት ያመጣል የሚል ነው። ይህንን እምነት መሰረት በማድረግም ከኦሮሞ፣ ከሲዳማ፣ ከሃረሪና ከአፋር ይልቅ ለትግራይ ህዝብ የክፉ ቀን ደራሽ የሚሆነው አማራ ነው የሚል ትርክት የሙጢኝ ብለው ይዘውት ኖረዋል። እርግጥ ነው፣ የሰው ልጅ ወዳጄ ነው በሚለው አእምሮ ውስጥ በድብቅ ስለሚብላላው ተንኮል ለማወቅ የአምላክን ድጋፍ ይፈልጋል። የትግራይ ህዝብ አማራን በሚመለከት ያሳደረው የእምነትና የመዘናጋት ስሜት፣ አማራ ስሜቱን የመደበቅ ካለው ጥልቅ ክህሎት ጋር ሲገናዘብ፣ እንደጅልነት የሚያስቆጥር አይደለም። በሚገባ እንደ ጅልነት መቆጠር የሚኖርበት አሁን በአማራ አእምሮ ውስጥ ተደብቆ አጋጣሚ ሲጠብቅ የኖረው ትግራይን የማጥፋት ፍላጎት ወደ ተግባር ተተርጉሞ በታየበት አጋጣሚ ነው። በአማራና በትግራይ "ዝምድና" ላይ ሁለቱም ያላቸው አመለካከት ለየቅል ብቻ ሳይሆን ግጭት ያለበትም ነው። 1. አማራው ከትግራይ ጋር ያለው የታሪክ፣ የባህል፣ የሃይማኖትና የስርወ ቋንቋ ጋርዮሽ በአማራ የበላይነት የሚመራ አድርጎ ይወስዳል። ይህንን ለማስረገጥ የሚቀርቡ አንዳንድ አስገራሚ ትርክቶች አሉ። "የአክሱም ስልጣኔ የአማራ ስልጣኔ ነው ይልና ተጋሩ  ከየመን የመጡ አገልጋዮች ነበሩ" ይላል። ይህ ማለት የኢትዮጵያ 3000 አመት የአማራ መር ስልጣኔ እድሜ መሆኑ ነው። አማራው ከአክሱምና አካባቢው በትኛው አውሎ ንፋስ ተጠራርጎ እንደወጣ ምስጢሩን የሚናገር የለም። ዳይኖሶሮች ተወርዋሪ ኮኮብ ወርዶ አጠፋቸው ይባላል። አማራን ከአክሱም/ ትግራይ ያስወጣው አስትሮይድ ታሪክ ግን እስካሁን አልተሰማም። 2. የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ማእከል አክሱም በመሆንዋና በትግራይ እጅ ውስጥ መሆኗ የሚጎመዝዘው አማራ ማእከሏን ወደ አማራ ክልል ለማዛወር ያልተሰራ ድርጊትና ያልተፈጠረ ተረት የለም። አቡነ ሰላማን በአቡነ ተክለሃይማኖት፣ አክሱም ፅዮንን በደብረሊባኖስና በጣና ገዳማት ለመተካት ያልተደረገ ጥረት የለም። 3. የግእዝ ፊደላትና ያሬዳዊው ዜማ መነሻው የትግራዩ አክሱም ሳይሆን ዋሸራ እንዲሆንም ያላሰለሰ ትግል ተደርጓል። 4. ለግእዝ እጅግ የቀረበውን የትግርኛን ቋንቋ "የተበላሸ አማርኛ" ነው በሚል አማስኖ ድራሹን በማጥፋት በአማርኛ እንዲተካ ብዙ ተለፍቷል። ከመጀመሪያው ብጀምር፣ 3000 አመት የሚባለው እንኳንና የሌላው የኢትዮጵያ ክፍል አማራውም ቢሆን የሚጋራው አይደለም። በርግጥ ሁሉም እንደየ ታሪኩ የየራሱ 3000ም ከዛ በላይም እድሜ ይኖረዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ለቱሪስት ፍጆታ የሚቆጠረው 3000 አመት አማራውን አይመለከትም። ከዳአማት ስልጣኔ ጀምሮ እስከ አክሱም ዘመን ፍፃሜ ድረስ የነበረ 2000 አመት የትግራይ እንጂ አማራን የሚጨምር አይደለም። ይህ ዘመን አክሱም በመካከለኛው ምስራቅና በቀይ ባህር ጂኦፓለቲካል ማእቀፍ ውስጥ ከህንድ፣ ከአረብ፣ ከሮም፣ ከኑብያና ከግብፅ ጋር የነበረውን ንግድ ስትመራ የኖረችበት ነው። አክሱም ወደ ደቡብ ከነበረው አካባቢ ጋር የነበራት ግንኙነት እንደ የዝሆን ጥርስ ያሉ በአለም አቀፉ ንግድ ተፈላጊነት የነበራቸው እቃዎች በማግኘቱ ላይ ብቻ የተወሰነ ነበር። የአክሱም ስልጣኔ ወራሽ የሆነችው ትግራይ ከመካከለኛው ምስራቅ ባህላዊና ታሪካዊ ማእቀፏ ወጥታ ከአማራ ጋር የተገጣጠመችው ታሪክ በፈጠረውና ውሎ አድሮ ለትግራይ የፍዳ ኑሮ እንድትመራ ያደረጋት አጋጣሚ ነበር። ይህም ከአክሱም ክርስትና ሃይማኖት መቀበል ጋር የተያያዘ ነው። በእስልምና ሃይማኖት በቀይ ባህር ዙሪያ መስፋፋት ምክንያት ከኖረችበት ቀጠና ክርስትናን ይዛ የተገለለችው አክሱም የነበራት ብቸኛ አማራጭ ወደ ደቡብ በኩል ከነበረውና ክርስትናን ከአክሱም ተቀብሎ ሲያስፋፋ ከነበረው የአማራና አገው ህዝብ ጋር መገጣጠም ነበር። የእስልምናው አለም አክሱምን በወረራ ወደ እስልምና ያልቀየረው ነብዩ መሃመድ ለተከታዮቻቸው  "አክሱምን ሳትነካችሁ እንዳትነኳት" ብለው ስለነበረ ነው። ይህ ባይሆን ኖሮ የአሁኒቱ ትግራይ የመካከለኛው ምስራቅ አካል እንደሆነች ትቀር ነበር። ሳይቆጫት ይቀራል ትላላችሁ? ትግራይና አማራ አቢሲንያ ተብለው ከተገጣጠሙ የአንድ ሺህ አመት ቆይታ አድርገዋል። ቆይታው ግን ለአንድ ቀንም ቢሆን ስምምነትና መፈቃቀር ያለበት አልነበረም። አማራው ሊለውጠው የማይችል ግን በእጅጉ የሚቀናበትን የአክሱም/ትግራይ የ3000 አመት የቆይታ ዘመን፣ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ማእከልነት፣ የዜማና የፊደላት ምንጭነት፣ የጥንታዊ ቅርሶች ባለቤትነትን ትግራይን በማጥፋት ወይንም በማዳከም ይህ ሁሉ ታሪክ የራሱ እንደሆነ ለአለምና ለመላ ኢትዮጵያውያን ማሳወቅ ይመኛል። ምኞቱ አደገኛ የአእምሮ በሽታ ሆኖበትም፣ ናዚዎች ስድስት ሚልዮን አይሁዶችን በአምስት አመት ፈጁ ሲባል በአምስት ወር ስድስት ሚልዮን ተጋሩን ለማጥፋት ተነሳ። ግራም ነፈሰ ቀኝ አማራና ትግራይ የጋራ የሆነ ነገር የላቸውም። አንድ ሃይማኖትና አንድ ባህል አላቸው ስለተባሉ ብቻ አንድ አይሆኑም፣ ዝምድና ቋንቋ ነው እንደሚባለው። አጥፊና ጠፊ አንድ ላይ ሆነው እንጀራ አይቆርሱም። "እስራኤልና ጀርመን እኮ ተቀራርበው እየኖሩ ነው፣ አማራና ትግራይም እንዲህ ሊሆኑ ይችላሉ" የሚሉ ተስፈኞች አሉ። ሁለቱም ታሪኩ የተለያየ ነው። "የልብን ሰርቶ ይቅር በሉኝ፣ ምንስ አጠፋሁ ምን በደልኩኝ፣....ቂምን በሆዱ ይዞ መታረቅ፣ ይቅርታ አርጉ እያሉ መራቀቅ፣ አጉል ነው ከንቱ መበሻሸቅ።"  አንዳንድ ደፋሮች የሚሉትን ጉድ ልንገራችሁ። "በርግጥ የትግራይ ህዝብ እገነጠላለሁ ቢል ተቃውመን የምንናገርበት አፍ የለንም፣ የትግራይን ህዝብ ስናስበው ግን ተስፋ አለን" ። ምን እያሉ እንደሆነ የገባው ሰው አለ? የትግራይ ህዝብ ጅል ነው፣ ቢገድሉትም ከሰማይ ቤት ሆኖ ይቅር ይላል ነው። ከዱላ በላይ አንጀት የሚያቃጥለው የደካማ ንቀት ነው። ሌላው ኢትዮጵያ አየር ላይ እንደዳመና በመንሳፈፍ ላይ ያለው አጉል አመለካከት በህወሓት ላይ የተወሰደውን እርምጃ እያወደሱ ስለተጎዳው የትግራይ ህዝብ የአዞ እንባ ማንባት ነው። "ያሳዝናል፣ የጦርነት ውጤቱ ይኸው ነው፣ ህወሓት ኑ ግጠሙኝ እያለች ህዝቡን አስፈጀችው፣ ነካክታ ነካክታ የኤሪትርያንና የአማራን ጦር ወደ ትግራይ እንዲዘምት አደረገችው፣ የሰሜን እዝንም መታ የትግራይን ህዝብ ለጥይት ዳረገችው፣ ወዘተ።" በዚህ አባባል የትግራይ ህዝብ ያለቀው በበራሪ ጥይት ነው፣ በመቶ ሺዎች የተሰደደው በራሪ ጥይት እንዳይመታው ፈርቶ ነው፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች የተደፈሩት ኢላማውን በሳተ ጥይት ወይንም ቦምብ ነው፣ መላ የትግራይ ሃብትና ንብረት ወደ አስመራ፣ ጎንደርና ባህር ዳር የተጓጓዘው ጦርነት ላይ በተማረከ ትራክ ላይ ተጭኖ ስለተገኘ ነው?  እነዚህ ሰዎች ማጭበርበር የሚችሉት በአይን በብረቱ እያየ ያለውን ህዝብ ሳይሆን ራሳቸውን ብቻ ነው።
Full Website