mahbereseytan@gmail.com

ዳግም የከሸፈው የዐቢይ አህመድ ዓሊ ዕቅድና የዲፕሎማቶቹ ሽሽት በአሜሪካ

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል  07-14-21

መንደርደሪያ፥ ‘እናቴ የ7 ዓመት ህጻን ልጅ ሳለሁ 7ኛ የኢትዮጵያ ንጉሥ ትሆናለህ ብላኛለች’ ብሎ የሚያምን የውሸት ቫይረስ ተሸካሚ ዐቢይ አህመድ ዓሊ የልጅነት ምኞቱና ፍላጎት ለማሳካት፥ ከሱዳን ጋር መክሮ፣ ኃይማኖት አልባው የአማራ ኢንተርሃምወይ ሚኒሻና ታጣቂ አስተባብሮ፣ የኤርትራና የሶማሊያ እልፍ አእላፍ ሠራዊት አስከትሎና በኢምሬት ድሮን ታጅቦ ትግራይ በሁሉም አቅጣጫዎች ከበባ ውስጥ በማስገባትና በመነጠል ላለፉት ሰባት ወራት በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጸመው ማንነት መሰረት ያደረገ የዘር ማጥፋት ወንጀል ታሪክ ፈጽሞ የማይረሳውና ይቅር የማይለው የጋለሞታይቱ የኢትዮጵያ የክህደትና የደም አረመኔያዊ ገጽቷ ሆኖ በታሪክ ተከትቧል። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ከጠላት መንግስታትና አገራት ጋር በመምከርና ግንባር በመፍጠር በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጸሙት አረመኔያዊ ወንጀል ጥልቀት የ21ኛው ክፍለ ዘመን ሰው አእምሮ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ያደረገው አንዱ ገጽታው፥ ምግብ ተርፎ በሚደፋባት ዓለም ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከጥይት የተረፈ ህዝብ በረሃብና በወረርሽኝ ለመጨረስና ለመጨፍጨፍ የተጓዘው ርቀት ነው።  ቀደም ሲል የህዝቡ የእህል ክምችት ጎተራዎች በመዝረፍ የተጀመረ የትግራይ ህዝብ በረሃብ የመጨረስ ዘመቻ የገበሬ ማሳ ወደ ማቃጠል፣ ማውደምና መሬቱን እንዳያርስ በመከልከል በአከባቢው የምግብ እጠረት እንዲከሰት መደረጉ ይታወሳል። መንገድ በመዝጋትና የእርዳታ ሠራተኞች በመግደል፣ ለእርዳታ የተላከው እህልና ቁሳቁስ በትግራይ ለተሰማራ የኢትዮጵያና የኤርትራ ወራሪ ሠራዊት ቀለብና ስንቅ እንዲውል በማድረግ፣ አሁንም ለእርዳታ የተላከው እህልና ዘይት ለአማራና ለኤርትራ ነጋዴዎች በመሸጥ በትግራይ የምግብ እጥረትና እጦት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲከሰትና እንዲባባስ በማድረግ ምግብ እንደ ጦር መሳሪያ በመጠቀም ዐቢይ አህመድ ዓሊ ህጻናትና እናቶች ጨምሮ በርካታ ተጋሩ ህይወታቸው በአሰቃቂ ሁኔታ እንድታልፍ አድርጓል እያደረገም ይገኛል።

ዐቢይ አህመድ ዓሊ በትግራይ ላይ የገጠመው ዓለም ያስደመመ መጠነ ሰፊ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሽንፈት ተከትሎ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚ ላይ በግላጭ እየታየ ያለ የነገሮች መቃወስና አለመረጋጋት እንደተጠበቀ ሆኖ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከኤርትራ ሠራዊት ጎን በመሰለፍ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጸመው አስቀያሚና አረመኔያዊ ወንጀለኛ ድርጊቱ የከነከናቸውና የሰቀጠጣቸው ምዕራባውያን በጊዜ የሚጠበቅባቸው ያህል ጠንካራና አፋጣኝ እርምጃ ሲወስዱ ባይስተዋሉም ዐቢይ አህመድ ዓሊ በሰብአዊነት ላይ እየፈጸመው ያለ የለየለት ወንጀል በመቃወም በመጠኑም ቢሆን እየወሰዳቸው የሚገኙ ዲፕሎማሲያዊ እርምጃዎች የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባለ ሥልጣናትና ሹማምንት ከመቼውም ጊዜ በላይ እንቅልፍ እያሳጣቸው መጥቷል። ይህን ተከትሎ ከተፈጠሩ ስውር ጦርነቶች መካከል አንዱ ታድያ የዲፕሎማቶቹ ሽሽት ተጠቃሽ ነው።

የዲፕሎማቶቹ ሽሽት በአሜሪካ

‘ይዘጉ’ ተብሎ ትዕዛዝ የወጣባቸው ኢምበሲዎችና የቆንስላ ጽ/ቤቶች ብቻ ሳይሆን ክፍት ሆነው ይቀጥላሉ ተብለው የተተዉ ኢምበሲዎችና የቆንስላ ጽ/ቤት ሠራተኞች ሳይቀሩ እስኪጣራ ድረስ መሸሽ ነው የሚያዋጣው እያሉ ሠራተኞቹ ወደ ኢትዮጵያ ላለመለስና በወጡበት ለመቅረት የተቻላቸውን ሁሉ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ ኢቲቪ፣ ፋና ዋልታ የመሳሰሉ መንግስታዊ ልሳኖችና ከመከላከያ ሠራዊቱ ወጪ ተደርጎ ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸው ሐሰተኛ የፈጠራ ዘገባዎችና አሉባልታዎች ሲያናፍሱና ሲያሰራጩ ጸሐይ የምትጠልቅባቸው እንደ እነ ኢሳት፣ ዘሐበሻ፣ የኔታ ትዩብና ሌሎች በርካታ የፕሮፕጋንዳ መሽኖች በመጠቀም ኢትዮጵያውያን ማደንዘዝና ማታለል ስለተቻለው በውጭ የሚገኙ ኢምበሲዎችና ዲፕሎማቶች እኔን በመከተል CNN, BBC, New York Times, Washington Post, The Gardian, AP, France 24, AFP በተመሳሳይ መንገድ በመጠቀም ገዴታቸው አልተወጡም የሚለው ዐቢይ አህመድ ዓሊ በኢምበሲዎቹ ላይ ቂም ከቋጠረ ወራት ተቆጥሯል። ኢምበሲዎቹ የማፈራረስና ዲፕሎማቶቹ የመበቀል ፍላጎት እንዳለው ካሳየም ሰናባብቷል። ኢምባሲዎች ፍሬ አልባ ናቸው፣ ለኢምባሲዎቹ የምናወጣው ወጪ በመቀነስ በጀቱ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የሚገኙ፥ እንደ‘ነ ኢሳት፣ ዘሐበሻ፣ የነታ ትዩብና ሌሎች ዩቲበሮች ተጨማሪ ድጎማ ቢደረግላቸው የተሻለ ስራ ይሰራሉ የሚለው ዐቢይ አህመድ ዓሊ ግምታዊ ድምዳሜው ወደ መጨረሻ የመጣ ይመስላል።

‘የምዕራቡ ዓለም ፊቱ በእኔ ላይ ያዞረበት ምክንያት እናንተ ሥራችሁ በአግባቡ መስራት ባለመቻላችሁ ነው፤ ሌላው ይቅር እኔ የተናገርኩትና የምለው ነገር መድገምና መናገር የተሳናችሁ ዋጋ ቢሶች ናችሁ’ በሚል ቀላል የሚመስል መላላጥና ኩርፊያ የተጀመረ አለመግባባት አድጎ ጉዳዩ በፓርላማው ሳይቀር እንዲነሳ በማድርግ “ወጪ ለመቀነስ” የሚል ውሃ የማይቋጥር ሐሰተኛ ምክንያት ሰጥቶ በመላ ዓለም ከሚገኙ ኢምበሲዎች መካከል ከግማሽ በላይ የመዝጋትና ዲፕሎማቶቹ ወደ አገራቸው እንዲገቡ የማድረግ፤ ኢምበሲዎች በእነ ነአምን ዘለቀ የሚመራ የትምክህት ኃይል የሆነው የግንቦት 7 አመራርና አባላት ለመተካት ታስቦ የተጀመረ ዘመቻ ዛሬ ያልተጠበቀ አቅጣጫ ይዞ አውሮፓና አሜሪካ ሳይቀሩ ተጨማሪ የጦርነት ቀጠናዎች ወደ መሆን ተሸጋግረዋል። በአሁን ሰዓት በመላ ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኢምበሲዎችና የቆንስላ ጽ/ቤቶች የሁከትና የጦርነት አውድማ ሆኗል። በአውሮፓ የሚገኙ አጋጣሚ ሆኖ የሌላ አገር ቪዛ ይዞው የነበሩ ዲፕሎማቶች አሜሪካ ጨምሮ ወደ ሌላ የአውሮፓ አገራት ሽሽት ላይ ሲሆኑ የኦሮሞ ተወላጅ ከሆነችው ከአንዲት ሰራተኛ (ወ/ሮ አስቴር) በቀር ሠላሳ የሚሆኑ በዋሽንግተን የሚገኘው የኢምበሲው ሰራተኞች ወደ ኢትዮጵያ ለመመስለ ፈቃደኞች አይደሉም። ዐቢይ አህመድ ዓሊ አለቦታው የተቀመጠ ሰው እንደሆነ ምሬታቸው በመግለጽ ላይ የሚገኙ እነዚህ የኢምበሲና የቆንስላ ሠራተኞችና ዲፕሎማቶች፥ ኢትዮጵያ ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት የገነባችው መልካም ስምና ክብር በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠልሸት በዓለም መድረክ እያዋረዳት የሚገኘው ‘መሪ’ ለአገሪቱ መፈራረስ ብቸኛ ተጠያቂ ሰው ነው ሲሉም ይከሳሉ።

ዲፕሎማቶቹ፥ በተለይ በምዕራቡ ዓለም የሚገኙ ኢምበሲዎችና የቆንስላ ጽ/ቤቶች ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እንደሆኑና እንደነበሩ በመጥቀስ ‘ወደ አገራችሁ ግቡ’ ተብሎ የተላለፈ ትዕዛዝ እንደማይቀበሉት፤ የጉዳዩ መንስኤም በዋናነት “ወጪ ለመቀነስ” ተብሎ እንደ ተነገረው ሳይሆን ዲፕሎማቶቹ በትግራይ ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተባባሪዎች ለመሆን ፈቃደኞች ሳይሆኑ በመቅረታቸውና የገለልተኝነት አቋም በማንጸባረቃቸው የተወሰደባቸው የበቀል እርምጃ እንደሆነ በመግለጽ ቆይታቸው ለአንድ ዓመት በማራዘም ሌሎች አማራጮች ለመጠቀም እንደሚገደዱ እየገለጹ ይገኛሉ። እንደ ዲፕሎማቶቹ ገለጻ ዐቢይ አህመድ ዓሊ በትግራይ ላይ የፈጸመው ወረራና እየተካሄደው ያለ ጦርነት በመደገፍ ዲያስፖራውን እንዲያስተባብሩ፣ የውጭ ሚድያዎች በመጠቀም የመንግስት አቋም እንዲያንጸባርቁ፣ በተጋሩ የሚደረገው ማንኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ እየተከታተሉ የማክሸፍና የመቋቋም ስራ እንዲሰሩ፣ ያለው መዋቅራዊ ፕሮቶኮል በመጠቀም አለመታከት አገራቱን የማሳመን ስራ እንዲሰሩ የሚወተውትና የሚገፋፋ ከዐቢይ አህመድ ዓሊና አማካሪዎቹ ቢሮ በቀጥታ የተጻፉ በርካታ ቁጥር ያለው መንግስታዊ ደብዳቤዎችና ኢሜይሎች እንደ ማስረጃ ይዘው የሚቀርቡ እነዚህ ተንሳፋፊዎች በተለይ የአሜሪካ መንግስት ትኩረት እንዲሰጣቸው ለማሳመን አሁን ያለው የአገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ የሚያስረዳ ጠንከር ያለ አቤቱታ በተናጠል ከማዘጋጀታቸው በተጨማሪ ዲፕሎማቶቹ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ እንደሆነ እስር ጨምሮ ሌላ የከፋ ቅጣት ሊገጥማቸው እንደሚችል የሚያስረዳ ኬዝ እየጻፉና እያስጻፉ ለመሆኑ ለማወቅ ተችሏል።

የከሰመው ግብጽን እንደ መሰላል የመጠቀም ዕቅድ

ትግራይ የምትባል አገር ከካርታ፥ ትግራዋይ የሚባል ህዝብ እንደ ህዝብ ህልውና ላይኖሮ ፈጽሞ መጥፋትና መፋቅ አለበት የሚለው የኢሳይያስ አፈወርቂ፣ የዐቢይ አህመድ ዓሊና የአማራ ልሒቃን እምነትና ፍላጎት ከእንግዲህ ወዲህ በተጨባጭ እውን ሊሆን ቀርቶ በህልማቸውም ቢሆን አጀንዳው ዳግም ላይታያቸው በትግራይ መሬት ላይ ተቀብሯል። ኦፕሬሽን ራእሲ አሉላ አባ ነጋ ተከትሎ ሰማያት በላያቸው ላይ የተደፋባቸው እነዚህ ጣምራ ጠላቶች መናደፊያቸው ተመንግለው ከትግራይ መሬት ተነቅለው እንዲወጡ ከተገደዱ በኋላ የማትሞት ትምክህተኛ ምላሳቸው እያወጣወጡ “በራሳችን ጊዜ ነው የለቀቅነው” እያሉ ህዝባቸውን ሲያደናግሩና ሲያወናብዱ ተስተውሏል። ሐቁ ግን፥ ትግራይ ለመውረርና የትግራይን ህዝብ እንደ ህዝብ ለማጥፋትና ለማብረስ የትግራይ መሬት የረገጡ የኢትዮጵያና የኤርትራ የሠራዊት አባላት ያቀፉ ክፍለ ጦሮች አብዛኞቹ ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ ወድሟል የተቀሩም ቁስለኛና ሙርከኛ ሆኗል። በመሆኑም፥ ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት እንደ አገር ለመጠራት የሚያስችል ቁመና ካላት አገሪቱ ዳር ድንበርዋን የሚያስከብር መከላከያ ሠራዊት የሌላት የዓለማችን ብቸኛ አገር ለመሆኗ ምንም አያከራክርም። አንድም፥ “የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት” ህልውና ያለው የውሸት ቫይረስ ተሸካሚ የሆነው ዐቢይ አህመድ ዓሊ ምላስ ብቻ ላይ ነው ሊሆን የሚችለው። ከዚህ ውጭ የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ፎቶ ግራፈር ለዓለም እንደገለጠው የጋለሞታይቱ የኢትዮጵያ ሠራዊት በትግራይ መሬት ላይ በአሰቃቂና አሳፋሪ ሁኔታ ተቀብሯል።

ሦስት ሴት ልጆቹና አንድ በጉዲፈቻ የተነኘ ወንድ ልጅ በሞቀ አዳራሽ አስቀምጦ የድሃ እናት ልጆች መማገድ የማይሰለቸው ዐቢይ አህመድ ዓሊ ታድያ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የወታደር ልብስ አልብሶና መሳሪያ አስይዞ ወደ ትግራይ በላካቸው ቁጥር የመርዶ ዜና ከመስማት አልተገላገለም። ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ መሳሪያ ሞልቷል - የሰው ኃይል ችግር የለንም፣ በሁለት ሳምንት ውስጥ ግማሽ ሚልዮን ሠራዊት ማስታጠቅና ማሰለፍ ይቻላል! እያለ በይፋ በአደባባይ ሲቀደድ ግለሰቡ ምን ያህል ኃላፊነት የጎደለበትና የማይሰማው መሆኑን ብቻ ሳይሆን ይህ ዓይነቱ ኃላፊነት የጎደለበት አባባልና አነጋገር ተናጋሪው ለከፋ እልቂትና ደም መፋሰስ ያለው ትልቅ ሸውሃት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። ከዚህ ቀደም በፓርላማ ፊት ቀርቦ በተደጋጋሚ ባደረጋቸው ንግግሮች ላይ፥ ወደ መከላከያ የሚቀላቀል ሰው የለም፣ ከፍተኛ የሰው ሃይል እጥረት አለብን፣ በፌስቡክ አገር ነጻ አትወጣም፣ ከመቶ አስር ሚልዮን ህዝብ ወደ መከላከያ የተቀላቀለው አምስት ሺህ ብቻ ነው ያሳዝናል ያሳፍራልም እያለ ምሬቱን በመግለጽ የሚታወቅ ሰውዬ ዛሬ ምን ቢገኝ ነው ግማሽ ሚልዮን በሁለት ሳምንት ማስታጠቅ ይቻላል እያለ የሚፎክረው? ብሎ የሚጠይቅ ሰው የተነገኘ እንደሆነ በእውነቱ ነገር አስተዋይ ነው።

በርግጥ ድራማው አብቅቷል። ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከኦፕሬሽን ራዕሲ አሉላ አባ ነጋ በኋላ ሠራዊት መልምሎና አስታጥቆ ወደ ትግራይ ይመለሳል የሚል እምነት ያለው ተስፈኛ ሰው የተገኘ እንደሆነም ሲበዛ የዋህ ነው። ይህን ዓይነቱ ቅዠት በዐቢይ አህመድ ዓሊ አእምሮ ውስጥም ተፈልጎ አይገኝምና። ቢሞክራትም፥ ግማሽ ሚልዮን ይሁን አንድ ሚልዮን የሰራዊት መለዮ የለበሰ ወጣት በላከ ቁጥር ወይነ ትግራይ የወራሪው ኃይል መሳሪያ እየተቀበለ በሬሳ ላይ ሬሳ እየደረደረ እንደሚቀብረው ዐቢይ አህመድ ዓሊና እርባና ቢስ የሰራዊቱ አለቆች ከማንም በላይ አሳምረው ያውቃሉ። ከአሁን በኋላ ሰዉ ይህን ሁሉ ሙት፣ ቁስለኛና ሙርከኛ እየተመለከተ ዓይኑ እያየ የብርሃኑ እና የባጫ ጥሪ ተቀብሎ ወደ ሠራዊቱ በመቀላለቀል ወደ ትግራይ የሚዘምት ያበደ ኢትዮጵያዊ ወጣት ይኖራል ተብሎ አይገመትም። ዐቢይ አህመድ ዓሊ ግማሽ ሚልዮን ሠራዊት በሁለት ሳምንት ውስጥ ማስታጠቅና ማሰለፍ እችላለሁ ያለበት ምክንያት፣ ይህን ለማድረግ ያስችለው ዘንድ ያቀደውና ሰሙኑ የከሸፈበት ዕቅድ ታድያ ምንድ ነው? በማለት ይጠይቁ ይሆናል።

ዐቢይ አህመድ ዓሊ ግብጽ ለአንዲት ደቂቃም ብትሆን በኢትዮጵያ ላይ ወታደራዊ እርምጃ የመውሰድ ፍላጎት እንዳላት የሚያሳይ ነገር እንድታደርግ፣ ምልክት/ፍንጭ እንድታሳይ ያላጨሰው የዕጣን ዓይነት የለም። ይህ የሚደርግበት ምክንያት በዋናነት ቀደም ሲል በስፋት እንደተገለጸው በትግራይ ላይ የገጠመው ሽንፈት ተከትሎ አለኝ እያለ ሲኩራራበት የከረመው ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ ከጨዋታ ውጭ ሆኖ በመፈራረሱ ዳግም ሠራዊት ለመመልመል የሚያስችለው መጋበሪያ ሆኖ ሊያገለግለው የሚችል፣ የፕሮፓጋንዳ ሜሽኑን በሚገባ ሊያንቀሳቅስለትና ሊያርበደብድለት የሚችል የኢትዮጵያውያን ስስ ብልት የሚኮረኩር ወቅታዊ ርዕሰ ጉዳይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ስለሚፈልግና ዐቢይ አህመድ ዓሊ በኢትዮጵያውያን አእምሮ ውስጥ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊፈጥረው ለሚፈልገው ውዥንብርና ሽብር ከአባይ ግድብ ጋር በተያያዘ ግብጽ አመቺ ስለሆነች ነው። ዐቢይ አህመድ ዓሊ ሽንፈትና ውርደት የተከናነቡ ኢትዮጵያውያን ለማጽናናት አስቦ ‘መስከረም እመለሳለሁ’ የሚለውም ይህን ተማምኖ ነው። አጋጣሚው ወታደር ለመመልመል እንዲጠቀምበት ስለሚረዳው ክረምት ከማለፉ በፊት ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር መሳሪያ ሊያማዝዝ የሚችል የሆነ ነገር እንድትልና እንድታደርግ ዐቢይ አህመድ ዓሊ አጥብቆ ይሻል። ግብጽ አይደለም ተዋጊ ጀቶችዋን ወደ ኢትዮጵያ አየር አስገብታ እንዲሁ ጠንከር ያለ መግለጫ የሰጠች እንደሆነ ሐሰተኛ መረጃ በመስጠትና በማሰረጨት ኢትዮጵያውያን ለማስበርገር ምላሱን ወልውሎ የሚጠብቀው ዐቢይ አህመድ ዓሊ በውድቅት ሌሊትም ቢሆን ወታደራዊ መልዮውን ለብሶ ‘ግብጽ ልትወረን ነው፥ ኢትዮጵያ በልጆችዋ ታፍራና ተክበራ ትኖራለች!’ የሚል መፎክር በማሰማት ህዝቡን በማስበርገግ አገሪቱ ልትቀበለው ከምትችለው በላይ የሆነ ሠራዊት ማሰለፍና ማስታጠቅ እንደሚችል በመተማመን ሲጠባበቅ ቢስነብትም ዝምታ ነው መልሴ! የሚለው የግብጻውያን ምላሽ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ክፉኛ አስከፍቷል፤ አደናግጦታልም። ትግራይ ብቻዋን ለዐቢይ አህመድ ዓሊ ያሸከመችው ዕዳና ያከናነበችው ሽንፈት እየተመለከቱ ግብጻውያን ዝምታን በመምረጣቸው ዐቢይ አህመድ ዓሊ ክፉኛ ታውኳል። በነገራችን ላይ፥ ግብጽ በትክክልም የሆነ ነገር ብትልና ብትፈጥር ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከግብጽ ጋር ጦርነት ይገጥማል ማለት አይደለም። እንደው ጩኸቱን ለማድመቅና የግብጽ አጀንዳ ተጠቅሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በማስበርገግ ሠራዊት ለመመልመል እንዲጠቀምበት ነው እንጅ በግብጽ አሳብቦ ከሚያስተጋባው ፕሮፓጋንዳ የተነሳ የጦር ካምፕ ማሰልጠኛዎቹ መሙላታቸው ያረጋገጠ ቅጽበት ሳይውል ሳይድር ነው ጉዳዩ በሰላም እንፍታው ለማለት የሚሯሯጠውና በግብጻውያን ደጅ ላይ የሚጸናው።

Full Website