Back to Front Page

የት ይደርሳል የተባለ ጥጃ ቄራ ላይ ተገኘ

ከአብሳር

13/09/2013

የአገራችን መዋዕለ ዜና አስፈሪ ፤ ንጉሳችንም ጦር ሰባቂ  መንግስቱን ናፋቂ ሆነዋል ።የጦሩነት የባዶ ቤት ቱማታ ተመልሶ መጥተዋል ። ተመነደገች አደገች የተባለችው በእድሳት ጉዞ ከፍታን ስታማትር ሩቅ አዳሪ ብላ ሁላችንም  ያሳፈረች ጀልባ መቅዘፍያዋ ጠፍቶባት ትዋልላለች ። እንዳው ቆፈን ይዞናል።ብዕራችን እፎይታ መርጣ የቆየች ብትሆንም አገር እንደ ትሮይ ከተማ ለመፍረስ ጫፍ ላይ ስትደርስ የዝምታን ቆፈን መስበር የግድ ሆኗል።  የኢትዮጵያውያን ንጋት እየራቀ ሄደዋል። ፖለቲካችን ከግለሰብ ወደ ህዝብ ለማሸጋገር የተደረገው ትግል አደጋ ላይ ነው። ዲሞክራሲ ህዝቦችን ከግለሰብ ፈላጭ ቆራጭ አስተዳደር ነጻ ማውጣት መሆኑ ተረስቶ ህዝብ ጠፋ እንጂ መሪማ ተገኝተዋል  የሚለው ባልትም ሰማን።ህገመንግስታችንም በአንድ ሰው ቅድ እንዲበጅ ቀደዳውን ተጀምረዋል። ሰው ችግሩ የጋራ መሆኑን ዘንግቶ አንዱ በሌላው በጥርጣሬ እንዲተያይ እየተሰራበት ነው። ወገኖቻችን  ከአንዱ ገዢ ወደ ሌላው እየተሸጋገሩ ፍዳቸውን በማየት ላይ ናቸው። የዛሬዎቹ  ደግሞ ከሁሉም ቀደምት ገዢዎች ሲበዛ  በበግ ለምድ የተጀቦኑ ተኩላዎች ናቸው።የግጭት ጉም በመፍጠር በተመሰቃቅለ በአገራችን  ጫንቃ ላይ የተጫነው ቡዱን ያለን የእይታ ቅኝት  አስቀድሞ መግባባት ያስፈልጋል።አንዳንድ ወገኖች  ቡድኑ ከመጣበት ብሄር  አንጻር  የሚመለከቱት  ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል። ሆኖም እይታችን  መቃኘት  ያለበት  ከቡዱኑ ዕለታዊ ድርጊት እንጂ ከመጣበት ብሄር እንዳይሆን ጥንቃቄ ማድረግ አሰፈላጊ ነው።  ቡድኑን ማየት ያለብን እንደ ቀዱሞ ገዢ መደቦች ከሚያራምዳቸው  ፖሊሲዎች እንጂ  ከመጣበት ብሄር መሆን የለበትም አብይ የሚመራው ቡድን   በቀድሞው ኢህአዲግ መንግስት  ውስጥ እየፋፋ የመጣ ከውጭ ኒዮሊበራል ሃይሎች ጥብቅ ቁርኝት ያለው ሀገርን ለገበያ ያቀረበ  ቅንጣት ታህል የህዝብ ፍቅር የሌለው መንግስት ነው።  ወደ ስለጣን በመጣ ብዙ   ሳይቆይ ከኦሮምያ ታጋዮች ጋር የተጣላውም ለዚሁ ነው።ገዥዎች  ሰውን እያታለሉ  ብዙ መዝለቅ አይችሉም። እውነተኛ ማንነት መደበቅ የሚቻለው ለአጭር ጊዜ ብቻ ነው። የቀደሞ ገዢዎች   የኢትዮጵያን ህዝብ ሲያታልሉት
Full Website