የዛሬው ርእስ የወሰድኩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በተከበረው የኢትዮጵያ ፓርላማ ፊት ከተናገረው የተወሰደ ነው። በሴራ ጀምሮ በሴራ የሚኖረውአብይ የፖለቲካ ሴራ ተባብሷል መንግስትም ሴራው ውስጥ ይገባልብሎ ክብሩን ደጋግሞ በደፈረው የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት (ፓርላማ) ፊት ነው የገለፀው። እኔደሞ መቼ ከሴራ ፖለቲካ ተለይተህ ታውቃለህና? እንበለው እላለሁ።

አብይ ሲጀመር የሴራ ፖለቲካ ተጠቅሞ ነው ስልጣን ያገኘው። በሴራ ፖለቲካ ስልጣን ከያዘ በኃላ ወድያውኑ በህዝብ ተወዳጁ የታላቁ ህዳሴ መሃንዲስ ስመኘውን በሴራ ገድሎ ግብፆችን በደስታ አስፈንደቀ። ሴራው ቀጠለና ሰኔ 16 ቦምብ ተወረወረብኝ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ያለውና ጉዳዩ ለአገራቸው ታሪክ ሲሰሩ የቆዩትን የደህንነት ሐላፊዎችና ሰራተኞች ላይ አላክኮ ማሰርና ማሳደድ ጀምረ፡፡ አገራችን የነበራት ቡቁ የደህንነት ተቋም ቦዶ አስቀርቶ የውጭና የውስጥ ጠላቶች አገራችንን እንዳሻቸው ሰላም እንዲነሷት አደረገ።

አብይ በሴራ ፖለቲካው ለሁሉም ችግር ‘የህወሓት የበላይነት ነው’ በሚል ዘመቻ ተጠመደ። ሁሉንም የኢህአዴግ ድሎች ደምስሶ ሃያ ሰባት ዓመት ሙሉ ‘ጨለማ የህወሓት አገዛዝ’ በሚል ከነገዱና ደመቀ በሚስጥርና በግላጭ በማበር የትግራይ ህዝብ ስምና ክብርን አጠቆሩ። ስልጣን ከመያዛቸው በፊት የጀመሩትን ፀረ ህወሓትና ፀረ የትግራይ ህዝብ ደባና አሻጥር ውስጥ ለውስጥ መሆኑ አብቅቶ በግላጭ በአደባባይ በመግለፅ ሴረኝነታቸውን በአንደበታቸው ገለፁ። ሰለዚህ አብይ ሆይ! ሴራ ልጀምር ነው ያልከው? የተካንክበትን! ብንለውስ።

አብይ በሴራ ፖለቲካ በሶማሊ ክልላዊ መንግስት ጣልቃ በመግባት በህዝብ የተመረጠውን መንግስት አፍርሶ ህገመንግስታዊ ባልሆነ መንገድና በማን አለብኝነት ፕሬዚደንቱ አሰረ። የውጭ ዜግነት ያለውንና የአንድ መ.ያ.ድ (NGO) ሐላፊ የነበረውን ሞስጠፌን ሽሞ ህገመንግስቱን ጣሳ። በፖለቲካ ሴራ እነ አምባቸውን እነ ጀነራል ሰዓረን ገደለ። አሁን ደግሞ የላካቸውን ገዳዮች ለለውጡ ሲባል ነፃ አላቸው። ገዳይም ፈራጅም የለውጡ መሪ፡፡ የፌደራል ይሁን የክልሎች ሕገመንግስት አይገድበው፡፡ የካቢኔ ሹመት ይመስል የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሉአላውነት ጥሶ በአምባቸው ፈንታ የራሱን ሰው ተመስገንን ሾመ። በኦሮሚያም ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ ሽመልስን ሾመ። ወጎኖቼ ሳናውቀወ የጠቅላይ ሚኒስቴሩ ስልጣን ተሻሽሎ ይሆን?

በሴራ ፖለቲካ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄዎቹን አድበስብሰውና አታልለው ሳይመልሱለት ሲቀርግዜ ጥያቄዬን መልሱልኝ ሲል ደግሞ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ የአስቸካይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ በወለጋ፣ በኢሉአባቦራ፣ በአምቦና በጉጂ ጭፍጨፋውን ቀጠለ። ራሱ የፈጠረው ችግሩ መሆኑ እየታወቀ ችግሩ ሶስተኛ ወገን ላይ ለጠፈው። በአብይና በጆሃር የነበረ ቅዱስ ያልሆነ የፖለቲካ ሴራ ላይ የተመሰረተ ቅንጅት ሲፈርስ አብይ ሌላ ሴራ ሸርቦ በደህንነቱ ሹም ደምመላሽ ገ/ሚካኤል አማካይነት የነበረው ድብቅ ሴራ ለመሸፋፈን በጆሃር ላይ የግድያ ሙከራ አደረገ። በዚህ ጦስ ምክንያትም በሁለት ቀናት ብቻ ከሰማንያ በላይ ሰዎች ተገድሉ፡፡ በጉዳዩም የተጠየቀ አካል የለም። ሴራው ግን አሁንም አልተቋረጠም። ሴራ ደግሞ የአብይ አህመድ ዋና መርሆ ሆኖ ቀጥሏል።

የፖለቲካ ሴራ ትጥቁ ያደረገ አብይ ፊቱን በጨው አጥቦ በአገሪቱ ፓርላማ ፊት ቀርቦ የፖለቲካ ሴራ ተፈፀመብኝ እኔም ወደ ሴራ ልገባ ነው አለ፡፡ ስንት ሴራ ሲያቦካ እንዳልቆየ የተከበረው ፓርላማን ለማሳመን ሲያስመስልና ሲተውን ዋለ፡፡ ሁኔታው ካለፉት የፈፀማቸው ሴራዎች ጋር የተሳሰረ ሌላ አዲስ ሴራ ሊፈፅም እየተዘጋጀ ያለ እንደሆነ ንግግሩ ያመላክታል። እንዲያውም ትልቅ ሴራ ሳይሆን አይቀርም!

አብይ ሴራ የጀመረው ወደ ስልጣን ከመምጣቱ በፊት ነው። በዩ.ኤስ.አይ.ዲና በያማማቶ፣ በግብፆች፣ በጆሃርና በሌሎች አማካይነት የኢትዮጵያን ሉአላዊነት አሳልፎ ለመስጠት ተደራድሮ ነው ስልጣን ላይ የወጣው፡፡ ልመናው ስልጣን ላይ አቆናጥጣቹሁ እንድደላደል አድርጉኝ እንጂ እኔም የፈለጋችሁትን አደርጋለሁኝ ብሎ ነው መሃላ የፈፀመው፡፡ ለዚህ ነው ኢንጅነር ስመኘውን ጀነራል ሰዓረን ገለል አድርጎ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ፈዝዞ እንዲቀር ያስደረገው። የግብፆች የነብስ አባቶች የሆኑት አሜሪካ፣ አይ.ኤም.ኤፍ.እና የዓለም ባንክ አደራዳሪ ያደረገው። የነበረንን ከአስራ አንድ ለአንድ (የአባይ ተፋሰስ አገሮች በአንድ በኩል ግብፅ ብቻዋ በሌላ በኩል) አቅም ስናስታውስ ህዝባዊ አርበኛችንና ምርጥ ዲፕሎማት መለስ ዜናዊና እሱ ይመራው የነበረው ልማታዊ መንግስትን ማስታወሱ ተገቢ ነው። ቀድሞ አገራችን መሸጥ የጀመረው ሃይለማርያም ደሳለኝ ነበር፡፡ ያኔ ነበር የነበረን አቅም ወደ ሁለት ለአንድ (ኢትዮጵያና ሱዳን በጋራ ግብፅ ለብቻዋ) እንዲወርድ ያደረገው። ይህም ሆኖ ኢትዮጵያ በግዜው የበላይነት ነበራት። አሁን ግን አገራችን አራት ለአንድ ተከባ (ግብፅ፣ ሱዳን፣ አሜሪካና የዓለም ባንክ በጋራ ኢትዮጵያ ደሞ ለብቻዋ) ድርድሩ ቀርቶ ሽምግልና ውስጥ ገብታለች። በዚህም ምክንያትም ትራምፕ እባክህ ለይምሰል አታንገራግር ፈርም! ብለው በስልክ ለአብይ ትዕዛዝ የሚሰጡበት ደረጃም ደርሰናል። የቀረው ነገር አብይ ዋሽንግቶን ዲሲ ሄዶ በትራምፕ ፊት ከአልሲሲ ጋር ሲፈራረሙ ማየት ነው (እንዳውም አልሲሲ ቀድሞ ሳይፍርም አልቀረም እየተባለ ነው፡፡ አብይ ትናንት ለአልሲሲ የላከው የልምምጥ ደብዳቤም ይህንኑ ነው የሚያመለክተው)፡፡ ከዚህ ዓይነት የአገርን ተፎጥራዊ መብት ከመሸጥ ሴራ በላይ ምን ሴራ ሊኖር ይችላል? ታድያ ከዚህ በላይ ምን ሴራ ሊያሴራ ፈልጎ ይሆን በፓርላማ ፊት መንግስትም የፖለቲካ ሴራ ሊገባ ነው ያለው?

አብይ ኢህአዴግን ከነፕሮግራሙ አፈራርሶ ፒፒ የሚባል የውጭ ተላላኪ ፓርቲ ፈጠረ። በሴራ! የኢህአዴግ ወራሽ ነኝ ብሎም በህዝብ ባልተመረጠ ፕሮግራም ስልጣን ይዞ ፒፒ ነው ገዥ ፓርቲ ብሎ በድፍረት ኢህአዴግን ወክለው በህዝብ የተመረጡትን የፓርላማ አበላት ፊት ተናገረ። ህገ መንግስቱ ደፍሮና ያልተመረጠ ፓርቲ ይዞ በጌቶቹ የውጭ ሃይሎች ድጋፍ ስልጣን ተቆጣጥሮ ፓርላማውን አብጠለጠለ። ከዚህ በላይ ምን ሴራ ሊፈፅም አስቦ ይሆን ፓርላማ ፊት መንግስትም ሴራ ውስጥ ይገባል ብሎ እንዲለፈለፍ ያስደረገው?

ሴራው ሲቀጥል ፓርላማ ላይ ይህ እንደተናገረ በነገታው ምርጫ ቦርድ ተብየው የአብይ አሻንጉሊት ኢህአዴግ ፈርሷል የሚል ዘግይቶ የደረሰን ዜና አሰማን። ለነገሩ ነው እንጂ አብይ ኦስሎ ላይ ምርጫ ማካሄድ አለብህ ብለው ፈረንጆቹ ሲያዙት እዛው ሆኖ እሱም በተራው ለምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ አወረደ። በነገታውም ብርቱካን ሚዲቅሳ ወጥታ የምርጫ ጊዜ ወሰንኩኝ አለች። ይህ የፖለቲካ ሴራ ካልሆነ ምን ሊባል ይችላል? ከፌደራልና ከአዲስ አበባ መንግስታዊ መዋቅር ከሶስት መቶ በላይ የፒፒ አባል ያልሆኑ ሰዎችን ከስራቸው እንዲሰናበቱ አደረገ። ሁሉም ሰራተኞች በሚባል ደረጃ የህወሓት አባል ስለሆኑና ትግርኛ ተናጋሪ ብቻ ስለሆኑ ጭምር ነው። ይህ ሴራ አይደለም?

ሰውዬው አሁን አሁን እንደድሮ ከህዝብ ጭብጨባ እያገኘ አይደለም። ይህ ውስጣዊ ብስጭት እየፈጠረበት ቆይቷል። የሚቀርቧቸው ሰዎችም ግማሹ ከሃጥያቱ የለንበትም እያሉ እየራቁት ነው። የሙጥኝ ብለው ቀረቤታቸውን ያልተዉ ደግሞ ይህ የሚባል ድጋፍ  የሚሰጡ አይደሉም። የታወቀ ነው ከብርሃኑ ነጋ የቀረበ እና በግላጭም በድብቅም ተቀናጅቶ የሚሰራ ሰው ሁሉም አይቀናውም። እንደ ብርሃኑ ነጋ ስንት ድርጅት ፈጥሮ የከሰረ የፖለቲካ ነጋዴ የለምና። ቀስተ ደመና፣ ቅንጅት፣ አሸባሪው ግንቦት ሰባትና አርበኞች ግምባርና ኢዜማ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ማድረግ የሚችሉት ከፒፒ ጋር ከተቀናጁ ወይም አሁን እንደሚያደርጉት በምርጫ ቦርዱ የቁርጥ ቀን ወዳጃቸው ብርቱካን አማካኝነት የውስጥ ድብቅ ግንኙነት ማጥናከር ሊሆን ይችላል። አንድ መታወቅ ያለበት ጉዳይ ግን በሰው ሰርግ የሚሞሸረው ብርሀኑ ነጋ አብይንም ይዞት እንዲሚጠፋ ነው። ይህ የማይታበልና የሚታይ ሀቅ ነው፡፡

የስልጣን ዕድሜን ለማራዘም የሚሸረብ ሴራ ዘላቂ ውጤት አይኖረውም። ህጋዊነት የሌለው የአስቸካይ ግዜ አዋጅ ከስልሳ በመቶ በላይ የአገሪቱን ስፋት ቢሸፍንም ሰላም ማረጋገጥ አብይ ከተሳነው ቆይተዋል። ፓርላማ ላይ ሲቀድ ከመስመጥ አደጋ አዳንካት ያላትን አገር በአዋጅ ሰላም ማስፍን እንኳን ሳይችል ቀርቶ ሊያሰምጣት ቀርቧል። በኢኮኖሚ ወደ ኃሊት እንድትጋዝ ያደረጋት አገር ህዝብዋ የኑሮ ውድነት ምሬቱ መፍትሔ ያጣበትና ቀጣይ ጉዞውም የጨለመበት ሁኔታ እየታየ ነው። ምኑን ይዞ ምኑን እንደሚፈታ ግራ የተጋባ አብይ በብስጭት ፓርላማውን በአስቸካይ ሰብስቦ የተናገረው ንግግር ነው ብሎ መገመት ይቻላል። ነግር ግን ዲስኩሩ ፍንጭ የሚሰጥ ንግግር ነው። አምባገነኖችና ገዳዮች ሁሌም ስህተታቸውን ማየት አይችሉም። ሌሎችን መክሰስ ይቀናቸዋል። በሚከሷቸው ላይም ሴራ ለመሸርብ አያቅማሙም። ፍንጩም ይህንን እውነታ ነው የሚያንፀባርቀው፡፡

ከንግግሩ በቅርብ ወቅቶች የፈፀማቸውን ድርጊቶች በማየት ምን ሴራ ሊፈፅም አስቦ እንደሆነ መገመት ይቻላል። በቅርቡ በድንገት አብይ አስመራ መጓዙ ጤነኛ ተልእኮ ይዞ እንዳልሆነ በግልፅ መናገር ይቻላል። አሁንም የጉዞው ዓላማ ለኢትዮጵያ ህዝቦች ግልፅ አልተደረገም። የሶማሊያው ፎርማጆም የታደሙ ቢሆንም የኢሳያስ ልጅ ሰርግም ነበር ቢባልም በአብይና በኢሳያስ የሁለትዬሽ ምስጥራዊ ስብሰባ ምን ሸርበዋል? የሚል ወቅታዊ ጥያቄ ሆኗል የሁሉም ሰው ጥያቄ፡፡ የኢትዮጵያዊውም የኤሬትራዊውም። ሁለቱም ኢሳያስና አብይ የህወሓትና የትግራይ ህዝብ ነገር Game over ያለቀለት ነው ቢሉም የተመኙት ሆኖ ስላላገኙት በሴራ ላይ ሴራ እየፈፀሙ ቆይተዋል። ብቻቸው አይደሉም። ከውስጥም ከውጭም የሚደግፏቸው ሴረኞችም አሉ።

በቅርቡ በአማራ ክልል በአብይ የተሾመው መንግስት ከትግራይ የተላኩ አሸባሪዎች ይዣለሁ ብሎ የፈጠራ ትርክት መጀመሩ ተራ ክስ ሳይሆን የአንድ ትልቅ ሴራ አካል ነው። ይህን ድራማዊ ትርክት ይዞ አብይ ከውስጣዊ የመደመር ደቀ መዛሙርቱ ጋር በመሆን ሴራ ተሰራብኝ በማስተዳድረው ግዛቴ እያለ ነው። ሁለት ወር ሙሉ ስለታገቱ የዩኒቨርስቲ ወጣት ልጆች ምንም ያላለ የአማራ ሚድያ በጎንደር ይዞ ቶርቸር አድርጎ በትግራይ ተልከናል በሉ አሰኝቶ ያናገራቸውን ምስኪኖች ሰበር ዜና ማድረጉ እየታሰበ ላለው ታላቅ ሴራ ፍንጭ ነው። አብይ በፓርላማ አማርሮ ሴራ ተሰራብኝ ብሎ የተናገረው ያዘጋጀውን ሴራ ከፓርላማ በግልፅ የቀረቡለት ጥያቄዎች ስለ አበሳጩት በብስጭት አምልጦት የተናገረው ነው። ያ እንዳይቀርብ የተደረገው የህዝብ ተወካዮች ድምፅ ቢቀርብማ ጨርቁን ጥሎ ወደ ሰባተኛ አካባቢ ይገኝ ነበር። ሆኖም አብይ የደበቀውን የሴራ እቅድ በብስጭት አወጣው።

ሌላው ከሰኞ ማክሰኞ ቀደመ የሆነው የኖቤል ሽልማት በኢትዮ-ኤርትራ ምንም የሰላም ስምምነት ውጤት አልተገኘበትም ስምምነቱም ለሁለቱ ህዝብ ግልፅ አልተደረገም። ተጀምሮ የነበረው የድንበር ግንኙነትም በኢሳያስ ትዕዛዝ ተዘግቷል። ግንኙነቱ በሰማይ ብቻ ለዛውም ከአዲስ አበባ አስመራ ብቻ ተገድቧል። ትራምፕ የኖቤል ተሸላሚው እኔ  መሆን ነበረብኝ፣ ሳውዲም እኛም ትልቅ አስተዋፅኦ አድርገናል ሲሉ አብይ (ስለታገቱት ምንም ሳይል የከረመው ሰውዬ) በድንገት ብቅ ብሎና ተበሳጭቶ የሸለመኝን ድርጅት ጠይቁ! እኔን ምን ትሉኛላቹሁ አለ። ኢሳያስም አብይ ብቻውን ተሸለመበት ብሎ ቆሸቱ ሳያር አልቀረም። ለዚህም ሊካስ ይፈልጋል። ለዚህ ደግሞ ከአብይ ጋር መጀመርያ አዲስ አበባ በቅርቡ ደግሞ አስመራ ላይ በህወሓትና በትግራይ ህዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ያሉትን ሴራ ዶልተዋል፡፡ አብይ ከአሰመራ መልስ ፓርላማ ላይ ቀርቦ ለ’ንጉስ የማይመጥን’ ጥያቄ በእውነተኞቹ የህዝብ ተወካዮች በግልፅ ሲቀርብለት ተበሳጭቶ ሴራ ላይ እገባለሁ ብሎ እቅዱን የዘረገፈው።

ከዚህ ሴራ ጋር በተያያዘ የአብይ ነብስ አባቱ (coach) የሆነው የአሜሪካው አምባሳደር ማይክል በአገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ነውርነቱ የረሳ እስኪመስል ድረስ በአፋርና በትግራይ እየተዘዋወረ በግልፅ ምርጫ ይደረግ አይደረግ አብይን ነው የምንደግፈውና እናንተም ለምን ፒፒ አትቀላቀሉም ሲል ተደምጧል። ለማ መገርሳንም አገራቸው ድረስ ወስደው አዝናንተው ከህወሓት ጋር አትሞዳመድ ብለውታል። ኦነግንም ኦኦንኤልኤፍም ሌላ ፌደራሊስት ግምባር ፍጠሩ እንጂ ከህወሓት ጋር አትቅረቡ ብለው ግፊት እንደፈጠሩላቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው። እውነቱ ግን ሁሉም ድርጅቶች ለፌደራሊዝም ባሉበት እስከታገሉ ድረስ ውጤቱ አንድ ነው። ጊዜ የሚወስድና ትግሉን ከባድ እንዲሆን ከማድረግ ውጭ ሌላ ፋይዳ አያገኙበትም።
Full Website