የትግራይ ህዝብ መዋእል ከትግልና  ከጀግንነት የተቆራኘ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። የትግራይ ህዝብ ብቻውን ሆኖም ይሁን ከሌሎች ኢት ን/ት ወገኖቹና ኤርትራውያንወንድሞቹ በጋራ ከበርካታ የውጭ ወራሪዎችና ተስፋፊዎች ፊትለፊት ተጋጥሞ ጠላትን አሳፍሮ መልሰዋል። የራሱንና የሃገሩን ክብር አስጠብቋል። ይህ በታሪክ ድርሳናት የተከተበ ሃቅ ነው። ሆኖም ግን ይህ በመስዋእትነት የታጀበ  አኩሪ ገድላዊ ታሪኩ በሚያሳዝን ሁኔታ በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ልሂቆችና ገዢዎች ዘንድ የሚገባውን ክብር አላሰጠውም። የትግራይ ህዝብ ግን ራሱን አውቆ የሚያከብር ከስሜታዊነት የራቀ በጊዚያዊ ትርፍም ኪሳራም ቦታውን የማይለቅ ህዝብ በመሆኑ እጅግ አስቸጋሪና ውስብስብ በሆነ የረጅም ጊዜ ታሪኩ ማንነቱን ጠብቆ ኖሯል። ሆኖም ግን በዚህ አጭር ጽሁፍ ለመዳሰስ በማይሞ ከሩ ውስብስብ ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት በአንድ ወቅት ከነበረበት ቁንጮ የስልጣኔ ማማ ወርዶ በድህነትና በኋላቀርነት ለመኖር ተገዷል። በቅርቡ ባደረገው መራራ ብረታዊ ተጋድሎ በተጎናጸፈው ድል ምክንያት ወደነበረበት የስልጣኔ ማማና የሚገባውን ክብር ለመመለስ እርምጃ ለመጀመር የሚያስችሉ ሁኔታዎች ተፈጥረው ተስፋ መሰነቅ በጀመረበት ወቅት በራሱ አመራሮች በተፈጠሩ ድክመቶች እንዲሁም በታሪካዊ ተቀናቃኝ ሃይሎችና የጊዜን ሁኔታ ጠብቀው የሚነጥቁ የውስጥና የውጭ ጩሉሌዎች (opportunistic) ቡድኖች በጋራና በተናጠል በሰሩት አሻጥር የትግራይ ህዝብ ለተለያዩ ጥቃቶች ተጋልጦ ይገኛል። አሁንም ማንነቱን ለመጨፍለቅ፣ ክብሩን ለመግፈፍና የማደግና የመልማት ራእዩንና ጥረቱን ለማሰናከል በገዛ የራሱ ሃገር መንግስት ያውም ከድርሻው በእጅጉ የበዛ መስዋእትነት ከፍሎ ከውድቀት በታደጋት ሃገር የተቃጣበትን ያልተገባ ዙሪያ መለሽ ጥቃት እየተፈጸመበት ይገኛል። በቀጣይም ጥቃቱን የመንግስት ይሁንታ ምናልባትም ትብብር ጭምር በተሰጣቸው የተለያዩ ቡድኖች፣ የመንግስት ተቋማትና የውጭ ሃይሎች እየቀጠለ ይገኛል።አንዳንድ የዋሆች ወይም አውቆ አጥፊዎች ሃገር አይበድልም ይላሉ። ሃገር የሚወከለው በተቋማቱ ነው። በነዚህ ለጋራ ጥቅም በተቋቋሙ የተለያዩ የገንዘብ፣ የጸጥታ፣ የህግ፣ የንግድና ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እንዲሁም የህግ አውጭ ተቋማት በአንድ ህዝብ ላይ ጥቃትና  በደል ሲፈጸም ሃገር እንደበደለ ይቆጠራል።

የትግራይ ህዝብም ይህንን በህልውናውና በደህንነቱ ላይ ያነጣጠር ውስብስብ  አደጋ በአግባቡ በመገንዘብ እንደወትሮው አንድነቱን ጠብቆ ከመቼውም ጊዜ በላይ በመመከት ላይ ይገኛል። መላ ህዝቡና  የክልሉ መንግስት በወሰዱት ፈጣንና ቆራጥ ዝግጅት ምክንያት የታሰበውን ጥቃት ለጊዜ ለማክሸፍ ችሏል። ለሚመጣውም በተጠንቀቅ ላይ ነው።

የትግራይ ህዝብ በታሪኩ ከጭቆና፣ከድህነትና ኋላቀርነት ለመውጣት ባካሄደው የረጅም ጊዜ የትግልና  የጀግንነት ጉዞ ውስጥ ጥቂት ተጋሩ ከዚህ በታቃራኒ ቆመው አሳፋሪና ወራዳ ተግባር መፈጸማቸው አሌ የማይባል ሃቅ ነው። በአብዛኛው ያልተሳካ የባንዳነትና ህዝብን ለጠላት አሳልፎ የመስጠት ይቅር የማይባል ታሪካዊ ስህተት የፈጸሙ ግለሰቦች በየዘመኑ ተፈጥረው እንደነበሩ ከታሪክ እናስታውሳለን። የትግራይ ህዝብም በየአጋጣሚው በማንሳት ለማስተማሪነት በሚሆን ልክ ድርጊታቸውን በቁጭት ያስታውሰዋል ለትውልድም ያስተላልፏል። አንዳንዶቹከጠላት የወገኑ ከሃዲዎች ታሪካቸውን ከማጠልሸት የዘለለ አደጋ ሊያደርሱ አልቻሉም። በቁጥር እጅግ ትንሽ የሆኑ ግለሰቦች ግን በተለያዩ ወቅቶች በትግራይ ህዝብ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል ፈጽሟል። ይህ ክህደትም በተለያዩ የታሪክ ምዕራፎች አጋጥሟል። ከነዚህ ጥቂት ለግል ስልጣን ወይም በተራ ቂምበቀል ወይም በድንቁርና ታውረው ለጠላት ያደሩ የውስጥ መረጃዎችን ለጠላት አሳልፈው የሰጡ ወይም በቀጥታ ተሰልፈው የትግራይን ህዝብ የወጉ፣ ያደሙና ለታሪካዊ ውርደት የዳረጉ አንዱ ሓንታ ገብሩ እንደሆኑ በታሪክ ተዘግቦ ይገኛል።
Full Website