Back to Front Page
ክህደትም ሲወስድ እያሳሳቀ ነው--እንደ ውሃ!
ክህደትም ሲወስድ እያሳሳቀ ነው--እንደ ውሃ!

Tsegaye Regassa Ararssa Jan 2020


ብልፅግና የሚባል የኦሮሞ ፓርቲ የለም። In fact, ብልፅግና የሚባል በሕግ አግባብ የተዋቀረ ፓርቲም የለም--ሕገወጥ የሆነ (ግን በሕገወጡ ምርጫ ቦርድ እውቅና የተቸረው) ስብስብ እንጂ። በመሆኑም ብልፅግና Gaaddisa Hoggansa Oromoo ውስጥ አባልነትም ሆነ አንዳች የሚሰራው ተግባር ሊኖር አይገባም። የብሔር አደረጃጀት አይስማማኝም ብሎ ከኦሮሞ ብሔርተኛ ድርጅትነት እራሱን የሰረዘ ፓርቲ በኦሮሞ ብሔርተኛ ድርጅቶች ስብስብ ውስጥ አባል የሚሆንበት ተጠየቅ የለም።

ብልፅግና የኦሮሞ ሕዝብ፣ የኦሮሞ መሪዎች፣ እና የኦሮሞ ፓርቲዎች ጠላት እንጂ አጋር አይደለም። ከኦሮሞ ፓርቲዎች ጋር በአንድ ጥላ ሥር የመሰብሰብ፣ የመምከርም ሆነ የምርጫ ውድድር አሰላለፍ ላይ የመደራደር መ ብትም፣ የሞራል ብቃትም፣ የሕግ ተቀባይነትም የለውም።

ለብልፅግና ፓርቲ የወንበር ድልድል ለመስጠት የሚደራደሩ/የተደራደሩ "የኦሮሞ" ፓርቲዎች በሙሉ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ደመኛ ጠላቶች ናቸው። ከብልፅግና ጋር ተጠራርገው ይጠፋሉ። ታሪክም በከሃዲነትና በትግል ሻጭነት ሲያስታውሳቸው ይኖራል።

ብልፅግና ያዋጣኛል ያለችውን አደረጃጀት መርጣለች። ያ አደረጃጀት ከኦሮሞ ሕዝብ ድጋፍ ያስገኝልኛል ብላ ወስናለች። ድጋፍ ይኖራት አይኖራት እንደሆነ በምርጫው ይታያል--ምርጫ የሚኖር ከሆነ።

ከምርጫ በፊት በምርጫ ውጤት ላይ ከኦሮሞ ፓርቲዎች ጋር መደራደርና የተወሰነ የወንበር ቁጥር መለመን (ወይም መግዛት) ግን አንዳችም ተቀባይነት አይኖረውም። ይሄ፣ ዴሞክራሲን ጠልፎ መጣል ነው። ከምርጫ ሕግ እና ሂደት መንፈስ ጋር የሚጣረስ የወንጀል ተግባር ነው። ይሄ፣ ምርጫ ከመደረጉ በፊት ውጤትን በመወሰን፣ የሕዝብን ድምፅ ማፈን ነው። ይሄ፣ ሕዝብን መናቅ ነው። ይሄን ለሚፈቅዱ "የኦሮሞ" ፓርቲዎችም፣ ይሄ፣ ከሞት የከፋ ውርደት ነው። ሌብነት ነው። የሚያሳየው አንድ ነገር ቢኖር የአመራሩን ሆዳምነት ብቻ ነው።

ወደ ዴሞክራሲ የሚደረግ ሽግግር ከሚመጣበት መንገድ አንዱ፣ ድርድር (negotiated settlement) እንደሆነ ይታወቃል። ይሄ ማለት፣ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ፣ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች ተደራድረው ሥልጣን በመጋራት በሽግግር መንግሥትነት አገርን እያስተዳደሩ፣ ለዴሞክራሲያዊ ምርጫ አስፈላጊ ሁኔታዎችን የሚያመቻቹበት ሂደት ነው እንጂ፣ የምርጫን ሂደት (ቀኑን ጨምሮ)፣ የፉክክሩን ሁኔታ እና ውጤት አስቀድመው የሚወስኑበት ሂደት ነው ማለት አይደለም።

ምርጫ፣ የሕዝብ ድምፅ የሚገለፅበትና ሕዝብ ሥልጣኑን የሚጠቀምበት ዕድል የምንፈጥርበት ነፃ ሁኔታ እንጂ፣ የፖለቲካ መሪዎች የሚደራደሩበት፣ በስምምነት የሚካፈሉት ቅርጫ አይደለም።

ኢሕአዴግ "ያሻግራል" ተብሎ አደራ ሲሰጠው፣ በድርድር የሚቋቋም የሽግግር መንግስት (transitional government of a negotiated settlement) የሚለው አማራጭ ውድቅ ሆኗል። ኢሕአዴግ (ብልፅግና) የመመረጥ ተስፋው ሲመናመን፣ የምርጫውን ውጤት (እንደ ቅርጫ) ለመከፋፈል እንደራደር ማለቱን መኮነን ሲገባ፣ "አይ፣ የለም፣ ተደራድረን የተወሰነ ወንበር እንልቀቅለት!" ማለት (ያውም ለገንዘብ በመማለል)፣ የቅሌት ቅሌት ነው።

ይሄን የቅሌት መንገድ ያዘጋጁትም፣ የቅሌቱ ተጠቃሚ አብይም፣ የቅሌቱ ተዋናይ (ገንዘብ ተቀባይ የየድርጅቶቹ መሪዎችም)፣ ከተጠያቂነት አይድኑም።

ከዚህ በፊት በጥቂቱ የተጀመረ "የጉቦ" ጨዋታ፣ ድሩን እያደራ ድምፅና ወንበር ወደ መግዛት እየተራመደ ነው። እያየን እንዳላየን ዝም አንልም። ቅሌትም እንደውሃ እያሳሳቀ ሲወስዳችሁ ዝም አንልም።

ከድርጅቶች በፊትም፣ ከድርጅቶች በኋላም፣ የኦሮሞ ሕዝብና ፍትሃዊ የመብት ጥያቄዎቹ ይኖራሉ። ጥያቄዎቹ እስካልተመለሱ ድረስ ትግሉ ይቀጥላል--ያለ ድርጅቶችም ቢሆን። የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄ ግን፣ የመሪዎች ጥሪት ማሰባሰቢያ እንዲሆን አንፈቅድም።

ልብ ያለው ልብ ይበል፦ ብልፅግና የኦሮሞ (እና የጠቅላላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች) ጠላት ነው።

ዛሬ እንታገለዋለን። ነገ እንፋረደዋለን። ሌቦችን፣ ከሃዲዎችንና ደላላዎችንም እንዲሁ።

Back to Front Page
Full Website