ክፍል 2

በዳንኤል ብ . ተክሉ

danielekfta74@gmail.com

ቶሮንቶ ካናዳ

ላይ በርካታ የአሁኑ መንግስት የፕሮፓጋንዳና የአካሄድ ስልትን በተመለከተ ለመዳሰስ ሞክረናል። ባሁኑ ክፍል ደግሞ የዚህ የአሁኑ የፖለቲካ መድረክ መሰረታዊ ጉድለትን በተወሳሰበ ሳይንሳዊ መንገድ ሳይሆን እንደማንኛውም ሰው ማንም ሊረዳው በሚችል መልኩ ለማየት እንሞክር። የዶክተር ዓቢይ አሕመድ ማለትም ቲም ለማ በመባል የሚታወቀው ቡድን በራሱ በወያኔ ኢሕአዴግ ውስጥ የኦሮሞ ፓርቲ ማለትም የኦህዴድ ወኪል ሆኖ በሚሰራበት ወቅት በግንባሩ በኢህአዴግ ውስጥ አንጃ በመፍጠር የራሱን ግንባር በተለያዩ መንገዶች በመፈታተንና ለሃገሪቱ ጠላቶች ማለትም የታሪክና የፖለቲካ ጠላቶች ሃገራዊና ወታደራዊ ምስጢር እስከመስጠት የሄደ ከፍተኛ ሃገራዊ ክህደት በመፈጸምና የግንባሩን አንድነት በማፍረስ የራሱን የበላይነት ይዞ ሲወጣ በወቅቱ የህዝቡን ቁጣ ለማብረድ ሲል ስለ ሰላምና ስለ ምህረት እያወጀ ቢመጣም ቆየት ሲል ግን ውስጣዊ ባህሪው እየተገለጠና ሌላ ግጭት የሚጋብዝ መንገድ እየተከተለ መምጣት ጀመረ።
Full Website