በቀለ ብርሃኑ May 12, 2020

ይህ ጽሁፍ ዶር ኣበራ ዮሃንስ የጻፉትን መልአክት ተንተርሶ የተጻፈ ነው፥፥ ኣንባቢው በርከት አንዲል በሚል በኣማርኛ መሞከሩ የሚሻል ስልመሰለኝ ልምዱ ባይኖረኝም አነሆ፦

ዶክተር ዮሃንስ በጣም የምከታተላቸው ጸሃፊና ተንታኝ ናቸው፥፥ በብዛት የሚያቀርቧቸው ኣስተያየቶችና ኣስተሳሰቦች ከኔው ጋር ይመሳሰላሉ ወይም ይቀራረባሉ፥፥

ስሞኑንን ስለኢትዮጵያና ትግራይ ኣንድነት የጻፉት ቁም ነገር በጥሞና መታየት የሚገባው ነው፥፥ ስለዚህ ጉዳይ ወደፊት ኣጭር ነገር ለማለት አፈልጋለሁ፥፥ ለጊዜው ዋናው መገንዘብ ያለብን ነገር ግን የትግራይ ኢትዮጵያዊነት ፍጹም መሆኑ ነው፥፥ ማንም ተነስቶ በዘለፈንና ባስፈራራን ቁጥር የምናፈገፍግ ከሆነ ሌሎች ችግሮች በመጡ ቁጥር በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ላለመገኘታችን ዋስትና ኣይኖረንም፥፥

የዛሬው ኣስተያየቴ ምርጫን በሚመለከት የጻፉትን ይመለከታል፥፥ የምርጫ ማዘግየቱን ሃሳብ በተከፋፈለ ልብ ሳልቀበለው የምቀር ኣይመስለኝም፥፥ የኔ ምክንያቶችና ኣማራጭ መፍትሄ ግን ትንሽ ለየት ዪላል፥፥

ፒፒ ፓርቲና ህውሓት ላይ ያለኝ አይታም ከ ኣመሪካና አትዮጵያ አንግሊዝኛ በላይ ነው ብየ ገምታለሁ

ለመነሻ ይሆነን ዘንድ ፈደራሊዝምን በሚመለከት የኢትዮጵያውያን ኣመለካከት ወይም ኣረዳድ ኣንድ ኣይመስለኝም፥፥ የፈረንጆቹን የፈደራል ኣወቃቀር ከሆነ የምንከተለው አያንዳንዱ የፈደርሽኑ ኣካል የሆነ ክልል ወይም ግዛት የሚኖረው መንግስት ከፈደራሉ መንግስት በምንም መልኩ የተለየ ነው፥፥ ኣንድ ኣይነት የፖለቲካ አይታ ያላቸው ሆነው ከተገኙ ይህ ያጋጣሚ ጉዳይ ነው፥፥ ለምሳሌ ያክል በፈድራሊዝም ብዙ የማትታማው ኣሜሪካ አንኳ ፈደራል
Full Website