Tignen Tidmek 02-21-20

እንደሚታወቀው ለአምስት አመት አገራችን ለማስተዳደር የተመረጠው ኢህአዴግ እንደሆነ የኢትዮዽያ ህዝብና እናንተም የምታውቁት ጉዳይ ነው ። ኢህአዴግ የተመረጠበት ዋናው ምክንያትም ያነገበው የፖለቲካ ሪኦተዓለም እሱም አብዮታዊ ዴሞክራሲ ነው ከዚህ በተጨማሪም የአገራችን ከፍተኛ ስልጣን ያላችሁ አካል ናችሁ

ታድያ አሁን ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ስናየው በርካታ የህገመንግስት ጥሰቶች እየተፈፀሙ ያሉበት ወቅት ያለን ይመስለኛል ለምሳሌ ያህል በስረ አስፈፃሚው አካል ከተለያዩ አገሮች እየተፈፀመ ያለው ውሎች ምክርቤቱ የሚያውቀውና የተስማማበት አይመስለኝም ከነዚህ ስምምነቶችም አንዳንዶቹ ያገራችን ሉአላዊነትና ክብር የሚደፍር ሊሆኑ ይችላሉ ።ይህን ዓይነት የህግ ጥሰት ሲፈፀም ፓርላማው ጠቅላይ ሚኒስትሩን በጥብቅ መጠየቅ ያለበት ይመስለኛል ።በጠራራ ፀሃይ የህዳሴ ግድባችን ምርጥ ማኔጀር ላገሩ ሌት ተቀነ በበረሃ ላገሩ ግድቡን ለመፈፀም እየተጋ በነበረበት ጊዜ በሴራ ሲገደል ፣ ብርቅዬ ጄነራሎቻችን በሴራ ሲገደሉ ፣ ከፍተኛ የክልል አሰተዳዳሪዎች በሴራ ሲገደሉ ፣ የጃዋር መሓመድ ጠባቂዎች ለተመሳሳይ ግድያ አይነት ለመፈፀም የሚመስል አይነት ድርጊቶች ሲከሰቱና እነዚህን ያሴረና ግድያውን የፈፀሙ በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ሲገኙ አላየንም የፍርዱ ሁኔታና ዘገምተኝነት ስናየው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ተሳትፎ ያላችው መሆኑን የሚያስጠረጥር ዱጋይ ሆኖ እያለ ፓርላማው በገለልተኛ አካል እንዲጣራና ሃቁ እንዲወጣ ፓርላማው ያደረገው የሚረባ እንቅስቃሴ አላደረገም በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ተፈናቅሎ የሚላስ የሚቀመስ አጥቶ የድረሱልኝ ጥሪ በሚያሰማበት ጊዜ ፓርላማው በተወካዮቹ በኩል ጉዳዩን ለማወቅ ብሎም አስቸኳይ መፍትሄ እንዲያገኝ እቦታው ድረስ ሆዶ ማየትና ማጣራት ሲገባው ይህ ነው የሚባል እንቅስቃሴ ሲያደርግ አልታየም የህዳሴው ግድብ በተመለከተ አገራችን አሁን ያለችበት ሁኔታ መሰረት ወደ ድርድር የሚስገባ እንዳለሆነና ስንረጋጋ ማድረግ ውይም ደግሞ ከዚህ በፊት በተነደፋው በናይል ተፋሰስ ሃገሮች ብቻ መታየት አለበት የሚል አቋም መያዝ ሲገባ የኢትዮዽያን ጥቅም በማያስከብር ሁኔታ የሶስተኛ ወገን ባለበት ድርድር እየተካሄደ ፓርላማው ዝም ብሎ ማየት በጣም አሳዛኝ ነው

በተጨማሪም ደቡብ ክልልና ምዕራብ ኦሮምያ የህዝብ ተወካዮች በማያወቁት ሁኔታ በኮማንድ ፖስት እየተዳደረ ነው ያለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮዽያ ህዝብ ስም የተገኘ በቢልዮን የሚቆጠር ብር ለቤተመንግስትና ለመሳሰሉት ማስዋብያ ሲያዝና ወጪ ሲያደርግ ህገ መንግስታዊ ጥሰት መሆኑ ታውቆ ፓርላማው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠርቶ በጥብቅ መጠየቅ ያለበት ይመስለኛል በአጭር ጊዜ በርካታ የሚኒስትሮች ሹምሽር ማካሄድ ውጤታማነቱ ሳይፈተሽ እንዲሁ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማሾም ስልጣን ስላለው ብቻ ለሹምሽር ሚኒስትሮችን ለሹመት ሲያቀርብ ያለምንም አሳማኝ ምክንያት ፓርላማው እንዲሁ መራቂና አፅዳቂ ብቻ መሆን ያለበት አይመስለኝም

እነዚህንና የመሳሰሉት የህግ ጥሰቶች በተከታታይና በስፋት እየተፈፀሙ የኢትዮዽያ የህዝብ ተወካዮች እያዩ እንዳላዩ መሆን በከፍተኛ ደረጃ የተወከሉበትን የህዝብ አደራ ያለመፈፀም ብቻ ሳይሆን ለወከሉት ህዝብም መካድ እንደሆነ ያመላክታል እነዚህ ጥቂት ለአብነት ያህል የተጠቀሱት እንደ የተወካዮች ምክርቤት አባል አላወቅኩም አልሰማሁም ፣  እንደ አንድ ጉዳይ ተነስቶ አያውቅም እንዳትሉ በተላያዩ ማህበራዊና ዓለማቀፋዊ ሚድያዎች በተደጋጋሚ ሲራገብ እንዳለ ስለሚታወቅ ማመካኘት እንደማትችሉ ብትገነዘቡ ጥሩ ይመስለኛል ስለዚህ ከምርጫም በኃላም ቢሆን እያንዳንዱ የፓርላማ ተወካይ የኢትዮዽያ ህዝብ የጣለበትን ከፍተኛ የህዝብ አደራ ባለመወጣቱ መጠየቅ እንዳለበት ብሎም ከፍተኛ የሚባለው ቅጣት ሊጠብቀው እንደሚችል መገንዘብ ያለበት ይመስለኛል በአሁኑ ወቅት የሰው መብት መረገጥና የህገ መንግስት ጥሰቶች ሲፈፀሙ ከማንኛውም ኢትዮዽያዊ ዜጋ በላይ ሊያንገበግበውና ሌት ተቀን መስራት ያለበት እያንዳንዱ የምክርቤት አባል ይመስለኛል ስለዚህ እኔ እንደ አንድ ኢትዮዽያዊ እያንዳንዱ የህዝብ ተወካይ የተመደበለት አምስት ዓመት ወደ መገባደዱ ቢሆንም ከተገባደደ በኃላ በህግ እንዲጠየቅ መደረግ አለበት የሚል አስተያየት አለኝ ሌላው በጣም የሚያሳስበው ጉዳይ ደግሞ በቅርቡ እንደሰማነው እያንዳንዱ የምክርቤትአባልም እንደሚያውቀው ኢህአዴግ ፈርሰዋል የሚል ነው
Full Website