በዚህች አለም ውስጥ ፣ ስዎች ተወልደን ፣ አድገን ፣ አርጅተን ፣ የማይቀረውን የዚህች ምድር ስንብታችን የተፈጥሮ የስው ልጅ እጣ ፋንታ ነው ። ቁም ነገሩ ተወልደን መሞቱ ሳይሆን ፣ መወለዳችንና ፡ ተወልደን ማለፋችንን የሚያመላክት ማህበረሰባዊ አሻራ ትተን ስናልፍ ፣ የወጣንበት ማህበረሰብ ስማችንን ከመቃብራችን በላይ ለተተኪው ትውልድ ታሪክ ሆኖ ይኖራል።

ለምሳል ዊልያም ጀፈርሰን ፣ አብርሃም ሊንከን ፣ ቭላድሚር ኤሊች ሌኒን ፣ ቸርማን ማኦ ቱስቲንግ ፣ ማህተመ ጋንዲ ፣ ኔልሰን ማንዴላ ፣ሳሞራ ማሽል ፣ ማርቲን ሉተር ኪንግ ፣ ማዘር ተሪሳ  ፣ መለስ ዜናዊ ፤ የወጡበትን ማህበረሰብ ከማገልገል ባሻግር ፣ ለአለም ጥሩ ምሳሌና ለህብረተሰባቸው እድገት የቻሉትን ያህል አስተዋፅኦ በማድረጋቸው አለም አቀፍ እውቅናን ተጎናፅፈው አልፋል ።

በተፃራሪው የነዚህን ግለሰቦች ማህበራዊ ለውጥ ኂደት የሚቃረን ተግባር በመፈፀም የመጡበትን ማህበረሰብና የአለምን ህዝብ ለሰቆቃና ለሃገራት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ውድቀት የዳረጉ መሪዎችም ይህች አለም አፍርታለች ።

ለምሳሌ አዶልፍ ሂትለር ፣ ቪኑቶ መሶለኒ ፣ ጆሴፍ ስታሊን ፣ ኢዲ አሚን ዳዳ ፣ መንግስቱ ሃይለማርያም ወ.ዘ.ተ መጥቀስ ይቻላል ። በዚህች አለም ሰዎች ለስልጣን ፣ ለገንዘብ ሲስገበገቡ ፣ ቀላሏን የሰው ልጅ ሂወት ውጥንቅጧንና ፍዳዋን ያሳይዋታል ።

እንደ ሰው ልጆች፣ እራቁታችን ተወልደን ፣ እራቁታችን እንደምንቀበር እንረሳለን ፤ በዚህች አለም ውስጥ ትተነው የምንሄድ እንጂ ፣ ይዘነው የምንሄድ ስልጣንም ሆነ ሃብት የለም ። የሂውት ጉዞ ይህችው ነች ፤የምጥቁ አእምሮ ባለቤት ክቡር ጠ/ሚ መለስ ዜናዊም ፣ ኢትዮዽያና ፡ የኢትዮዽያ ችግር ፣ ከዚህ በፊት ከነበሩት የኢትዮዽያ መሪዎች ፣ ለየት ባለመልኩ ፣ ጠለቅ ባለ ሁናቴ ፣ የሃገሪቱን ችግር ተረድቶ ለሃገሪቱ ይበጃል ያለውን ፖለቲካዊና ፣ ኢኮኖሚያዊ ንድፈ ሃሳብ ቀይሶ ፣ መሬት ላይ በሰራ እየተገበረ የሚታይና የሚጨበጥ ለውጥ ከማስመዝገቡም በላይ ፣ ሃሳቡን በምእራባውያን ተቀባይነት እያገኘ መሄዱን ፣ የአለም መሪዎች ኽእንደነ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ፣ አነ ጠ/ሚ ጎርደን ብራውን ፣ ቻንስለር አንጌላ ማርከል ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉትን መሪዎች የተሰልፈ ብቸኛው የአህጉሪቱ የአፍሪካ ወኪል ነው በመሆን ፣ የኢትዮዽያንና የአፍሪካን ኩራት በመሆን  በአለም መድረኮች ተንፈላሰዋል ። በኔ የግል አመለካከት ፣ በኢትዮዽያና የኢትዮዽያን ህዝብ ፣ መለስን ያክል የሃገሪቱ ችግር የተረዳ ምሁርም ይሁን ማሃይም የለም ፣ ለወደፊትም አይኖርም፣መለስን ለመረዳት የመለስን ንጝሮች በትክክል ተረድቶ ከሃገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታዎች ፣ ከሃገሪቱ ታሪካዊ እውነታዎችና ፤ ከአለም ተጨባጭ እውነታዎች ጋር ማገናዘብ ያስፈልጋል ።

ታጋይ በረኸት ስሞኦን ስለመለስ የምስክርነት ቃሉ ሲሰጥ ፣ ገና ኢትዮዽያን እንደተቆጣጠሩ ሁሉም የትግል ጏዶቹ ከስራ ስአት በኃላ እየተሰባሰቡ ሲጫወቱና ሲዝናኑ መለስ ከቢሮው ሳይወጣ ተደፍቶ መፃህፍት እያገላበጠ ለረጅም ስዓት ሲያሳልፍ ፣ አቶ በረኸት ቢሮው ድረስ ገብቶ ከጏደኞቹ ጋር ለምን እንደማይዝናና ሲጠይቀው መለስ የመለሰለት መልስ ፣ በረኸትን ያስገረመ ነበር ። የሰጠው መልስ ኮት ፨ ፈራሁኝ ፨ ነበር ያለው ፣ ለምን ? ብሎ ሲጠይቀው የኢትዮዽያ ችግር እንደምንጠብቀው ሳይሆን ከምንጠብቀው እጅግ የባሰና የከፋ ነው አለው ። ቀጥሎም የሃገሪቱ ችግር በኔ ትከሻ ላይ ነው ፤ እኔም ሃገሬን መታደግ አለብኝ ፣ ለዚህ ነው ተደፍቼ የማነበው ነበር ያለው ።

መለስ ሂወቱ እንደ ሻማ እስኪቀልጥ ሰርቶም ለውጥ አሳይቷል ፤ ከሱ በኃላ የመጡና የሃገሪቱ ህዝቦች ፤ እቅዱና ራእዩን የማስቀጠልም ሆነ ያለማስቀጠል የነሱ ፋንታ ነው ። ጆርጅ ዋሽንግተን ፣ የአሜሪካ ህገ መንግስት አስረቅቆ ፣በማፅደቅ ፡ ከሁለት መቶ አመት  በላይ ፡ እየተሻሻለ ፣ የሚጨመረውን እየጨመሩ ፣ የሚስተካከለውን እያስተካከሉ ፣ እንሆ እስከ ዛሬዋ እለት ፣ የአሜሪካ የሕጎች የበላይ ሕገመንግስት ያስተዳድራቸዋል ። አሜሪካኖችም ዘፋውንዲንግ ፋዘር በማለት ጆርጅ ዋሽንግተንን ህያው ስሙን ያከብሩታል።

አሜሪካ በባርያ ንግድ ተዘፍቃ፣ የስሜኑና ፣የደቡቡ ግዛቶቿ ፣ አውዳሚ የእርስ በርስ ጦርነት ፣ አሳዛኝ የወንድማሞች ጦርነት ከተካሄደ በኃላ , በአብርሃም ሊንከን አሸናፊነት የባርያ ንግድ ስርአትን አስወግዶ ፣ ሰሜንና ደቡብን አዋህዶ ፣ የነበረውን የአሜሪካ ህገ መንግስት አሻሽሎ ፣እንሆ ከአንድ መቶ ሰባ ዓመት በላይ አሜሪካ እስከነ ልዩነታቸው አለምን እየመሩ ይገኛሉ ። እኛ ቱልቱላዎቹ ፣ የወሬ ቛቶች ፣የ(3000) የሶስት ሺ ዘመን ስልጣኔ ያለን ህዝቦች ፣ እያልን ባለን እንደመጨመር ፤ የተገነባውን እያፈረስን ፣ በአፈ ታሪክ የምንኖር ጉዶች ነን ።

መለስን ለመረዳት የመለስ ንግግሮችን ማድመጥ ብቻ በቂ ነው ። በአንድ ወቅት ካቢኔውን ሰብሰቦ ሰለ ሃገሪቱ የትራንስፎርሜሽን እቅድ ሲያስረዳ ። መጀመርያ የራሳችን ነባራዊ ሁኔታ መረዳት አለብን ፣ ቀንደኛው ጠላታችን ድህነት ነው ፣ ድህነትን ለመዋጋት ደግሞ ፣ድህነታችንን አምነን መቀበል አለብን። ካልሆነ የ፫ሺ (3000) ዘመን ታሪክ አለን ፣ የአክሱም ሃውልት ባለቤት ፣ ላሊበላ የገነባን ፣ ፋሲለደስ ያለን ፣ እያልን ድህነታችንን የምንሸፋፍን ከሆነ ሃቁን እየሸሸን ለውጥ ማምጣት አንችልም ነበር ያለው። እንደ ሃገር መሪ ፣ ሃላፊነቱን በግልጽነትና ፣ በቅንነት ለካቢንዬውና ለህዝቡ በሚዲያም ጭምር ነበር በማስረዳት ወገንትኝነቱን ያሳየው ። ኢትዮዽያም ከተኛችበት ጥልቅ እንቅልፍ ባነነች ።

ትክክል ነበር ፣ ከዛ በኃላ ነበር የኢትዮዽያ ህዝብም መንቀሳቀሥ የጀመረው ። መለስ በርግጥ ድክመቶች አልነበሩትም ማለት ባልችልም ፣ የመለስን ሃሳቡ የተረዱት ሰዎች ግን በጣት የሚቆጠሩ ነበሩ ብዬ አምናለሁኝ ። በተለይ ሌብነትና ፣ ሙስና መንግስት በያንዳንዱ ቤት ገብቶ መቆጣጠር አይችልም ። ለምሳሌ በአንድ ወቅት ፖርላማ ቀርቦ ስለ ሙስና ተጠይቆ ሲመልስ ፣ እናውቃለን እስከ አንገታችን በሙስና እንደተጨማለቅን ፣ ግን ሁሉንም ደግሞ ማሰር አይቻልም ነበር ያለው ።መለስ እንዴት ለማኝ እንሆናለን የሚል የቁጭት መንፈስ በህዝቡ ሲያሳድር ፣ መሰንበት ደጉ ልመና እንደ ጀግንነት የሚሰብክልን መሪም ማየት ችለናል ። ይህ ምን ማለት ነው  ? ለሚገባው ህዝብ ሃገር በአንድ ስው ብቻ አይመራም ፣ ሁሉም የየራሱ ሃላፊነት ሲወጣ ሃገር ታድጋለች ። ለምሳሌ በኢትዮዽያ ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ የነፃነት ጮራ የፈነጠቀው በመለስ ጊዜ ነበር ፤ መለስ መላጣዬን እስካልነካቹህ የፈለጋችሁትን ፃፉ ፣ ነገር ግን ጥቁር ካልን ቀይ ብላቹህ ከፃፋቹህ እናግዳቹሃለን ነበር ያለው ። ወፈፌዎቹ የኢትዮዽያ ሚዲያዎች ፣ወጥ መርገጥ ሲጀምሩ፣  ለሰሩት ቅጥፈት ሃላፊነት እንደመውሰድ ፣ መንግስትን መወንጀል ጀመሩ።  መለስም ይጠረቅማቸው ጀመር ፣ ይህ ነው ሃቁ ለምሳሌ የ፺፯ቱን (97)ምርጫ እንመልከት ፣ ቅንጅት ፳፫ቱን(23) የአዲስ አበባ ወንበር አሸነፈ ፣ መለስም በትክክል አሸንፋችሃል አዲስ አበባን ተረከቡ አለ፣ አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል ሆነና ፣ የለም ድፍን ኢትዮዽያን ነው ያሸነፍነው ፣ በማለት ብርሃኑ ነጋ ሙጥኝ አለ ፣ መለስም ያልተወዳደርከው እንዴት ማሸነፍ ትችላለህ ብሎ ቢጠይቀው መልስ አልነበረውም ፣ በዚህ የተነሳም ብርሃኑ ነጋ አዲስ አበባ ላይ ሁከት ፈጥሮ ስልጣን ሲቛምጥ ፣ መለስ ጋ ቀልድ የለም ተገቢውንና ተመጣጣኝ ብሎ ያመነበትን እርምጃ ወስዶ ቀላዋጩ ብርሃኑ ነጋም ዘብጥያ አወረደው ። ሃገርን ስትመራ ከውሸትና ከፍርሃት ነፃ መሆን አለብህ ። መለስ የሚታወቀውም በዚህ በሳል አመራሩና ለውሳኔው ባለው ቆራጥነት ነው ።

ከዚሁ ሳልወጣ መለስ ቅን አስተዋይ ርህሩህና ብልጥ ነው ። ጠቅለል ባለ አገላለፅ አራዳ ያራዳ ልጅ ነው ፣ በዚህ ላይ ለክፉዎች ለተንኮለኞች ከነሱ የባሰ ክፉና ተንኮለኛም ነው ፣ ለምሳሌ ወይዘሮ ብርቱካን ሚደቅሳ የአሁና የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ፣ከነብርሃኑ ነጋ ጋር ዘብጥያ ከወረዱ የቅንጅት አባላት መካከል ነበረች ፣ ታድያ በዘመድ አዝማድ ተለምኖላት አጥፍቻለሁኝ ይቅርታ ብላ ከወጣች በኃላ፣ አውሮፓ ሂዳ እኔ ይቅርታ አልጠየኩም ብላ መቦጥረቅ ፣መለስም የዋዛ አይደለም ፣ ከጉዞዋ አገር ሰላም ብላ ስትመለስ ወህኒ  ወረወራት ።

ታድያ መለስ ምክኒያታዊ ነው ወይስ አይደለም ብለን ለመመዘን ፣ ከመለስ ባሻገር የራሳችንን ድርጊትና ፍላጎትን መሰረት በማድረግ, መለስን መረዳት አንችልም ።አንድ እውነተኛ ታሪክ ላጫውታቹህና ማነው ? ማንን ያልተረዳው ? ለሚለው ጥያቄ ትክክለኛ መልስ ይሆናል ብዬ ያመንኩበትን ውሳኔ ፣ በምሳሌ ላስረዳ ።ይህ ታሪክ በአክሱም ከተማ የተከሰተ ክስተት ነው ። ምህረይ ወልደ ዮውሃንስ የሚባሉ አዋቂ የቤተክህነት ምሁር ነበሩ ። ነዋሪነታቹው በዛና ወረዳ ሲሆን በአንድ ወቅት ድርቅ ገብቶ ስደት ይሄዳሉ ፣ መንገድ ላይ ችግር ፣ ርሃብ ፣ መከራ ፣ ሚስታቸው ልጆቻቸው ሲነጥቃቸው ፣ ከ፫ ዓመት ስደት በኃላ ወደ መንደራቸው ይመለሳሉ ።

አስቡት እኝህ ሊቅ ፣ የኔ የሚሉትን ሁሉ ተፈጥሮ ነጥቛቸዋል ። ወደ ቄአቸው ሲመለሱ ያቺ ተስፋ

አድርገውባት የተመለሱትን ጎጆአቸው ፈራርሳ ፣ መሬታቸው ደግሞ ጎረቤታቸው ሲያርሰው ይደርሳሉ እሳቸውም ምነው ? ወንድሜ መሬቴን ተመኘህ የኔኮነው ፣ ሲሉት ሂድና ክሰሰኝ አላቸው ፣እሳቸውም ሌላ አማራጭ ስላልነበራቸው ይከሱታል ። ታድያ ከቀነ ቀጠረው በፊት ፣ የወረዳው ዳኛና ተከሳሹ አብረው ሲጠጡ ያገኟቸዋል ፣ ብልሁ ቄስም በቀጠሮአቸው ቀን የአስከሬን መጠቅለያ ሰሊን ይዘው ፍርድ ቤት ቀረቡ    ምነው ? ምህረይ ቢሏቸው ፣ ከእንግዲህ እኔ የመኖሬ ትርጉም ምኑ ላይ ነው ? ግነዙኝ ፣ ቅበሩኝ አሉዋቸው ። ዳኛውም ለተከሳሹ ፈረደለት ። ምህረይም ዛናን ትተው ወደ አክሱምና ሽሬ እየተመላለሱ ቀሪውን የሂወት ዘመናቸው ገፉ ። ህብረተሰቡ እብድ እያለ እውቀታቸው በውን ሳይረዳ ፣ እስከ ህልፈተ ሂወታቸው ኖሩ ። ያበደው ህብረተሰቡ እንጂ ምህረይ አልነበሩም። አንዳንድ ጊዜ ግለሰቦች ከህብረተሰቡ ላቅ ያለ አስተሳሰብ ያላቸው እንደሆነ ፣ እነሱን የመረዳት አቅም ስላሌለን ፣ የነሱን አሰተሳሰብ በማጥላላትና በማንቛሸሽ የምንረካ ጉዶች መሆናችንን ብናውቅ ሃገራችን የት በደረሰች ነበር ። መለስን ውሃ ቀጠነ ብለው የሚተቹት ግለሰቦች ፣ ሃሳብን በሃሳብ የማሸነፍ ብቃትም ፣ ችሎታም የላቸውም ። ለምሳሌ የመለስ ፖለቲካዊ እምነት ልማታዊ መንግስት ከተቃወሙት ከኢትዮዽያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተጣምሮ ኢትዮዽያን ሊቀይር የሚችል የፖለቲካ ፕሮግራም አቅርቦ ማሸነፍ ነው ። እነሱ ግን ከኢትዮዽያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የማይሄድ የምእራባውያን አይዲዮለጂን ሊያቀርቡ ይፈልጋሉ ።
Full Website