የ2012 ሰኔ 15 የሰማዕታት ቀን - የሰማዕታት እናት አታለቅስም

ሐዱሸ ፀጋየ

ሰኔ 15 2012

ከአዲስ አበባ

የትግራይ ህዝብ በአስራ ሰባት ዓመታት መራራ የትጥቅ ትግል ጉዞው ፋሽስት ደርግን በመፋለም ከስልሳ ሺ በላይ መስዋዕትነት ከፍሏል። በብዙ ሺ የሚቆጠሩ አካላቸው ጎድላል። ይህ የከፈሉት መስዋዕትነት በህወሓት መሪነት የተደረገ ተጋድሎና የፋሽስት ደርግ ሚልዮን የሚጠጋ ሰራዊቱ በመደምሰስ ግቡን አሳክታል። በዚህም የኢትዮጵያ ህዝቦች ለብዙ ዓመታት ባልተደራጀ መንገድ ያደረጉት የነበረውትግል ውጤት ሳያመጣና ከባድ መስዋዕትነት ሲያስከፍላችው የነበረው ታሪክ ቀይራል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች በተደራጀ መንገድ ባደረጉት ትግል በደርግ መቃብር የህገመንግስት ባለቤት በመሆን ህዝባዊ መንግስት መመስረት ችለዋል። በየብሄራቸውም ራሳቸው ማስተዳደር ችለው ነበር የነውጥ ለውጥ እስኪመጣ ድረስ።

በኢህአዴግ አብዮታዊ ዲሞክራሲና ልማታዊ አቅጣጫም በመመራት የኢትዮጵያ ህዝቦች ከድህነት አረንቋ ለማውጣት የሚያስችል ልማታዊ ዕድገት ማስመዝገብ ተችሏል። ብዙ ሚልዮኖች ከአስከፊ የድህነት ወለል ወጥተው ኑሯቸው መሻሻል ጀምሯል። ትምህርት ይደርስባቸዋል ተብለው የማይገመቱ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች ተከፍተው ሚልዮኖች የትምህርት ዕድል አግኝተዋል። አንድ ዩኒቨርስቲ ብቻ የነበራት አገራችን በሰማዕታትና አካላቸው በጎደሉት ደምና አጥንት ከአርባ በላይ ዩኒቨርስቲዎች በአጭር ጊዜ ተከፍተዋል። በጤና፣ በትምህርትና በመሰረተ ልማት ግንባታ ብዙ ተዓምራዊ ለውጦች ታይተዋል። ለውጡ በሁሉም አካባቢዎችና በሁሉም ዘርፎች የተከናወነ ነበር።

ይህም ሆኖ በሚልዮኖች የሚቆጥሩ የአገራችን ህዝቦች ከተስፋ ባለፈ ገና ከድህነት ወለል ያልወጡና የፈጣን ልማቱ ትሩፋት ተቃዳሽ ለመሆን በተስፋ የሚጠባበቁ ነበሩ። ይሁንእንጂ የህዝቡን ፍላጎት ረስተው የስልጣን ጥማቸውን ብቻ በሚያዩ በኢህአዴግ ውስጥ ተሰግስገው የነበሩ ጥገኞች የትግሉን ዓላማ ቀልብሰው ሪፎርም በሚል ስም ስልጣን በመያዛቸው አገራችን ከልማት ጎዳና ወጥታ በችግር አረንቋ ላይ እንድትወድቅ ፈርደውባታል። የሰማዕታት ዓላማ ለጊዜውም ቢሆን ገተውታል። በመሆኑም የዘንድሮ ሰኔ 15 ለየት ባለ ሁኔታ ላይ ሁነን የተሰውትን ሰማእታቶቻችን እንዘክራለን።

የኢትዮጵያ የሰማዕታት ሐውልት የሆነውና በሁሉም ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች አጥንትና ደም የታነፀው ህገመንግስታችን እነዚህ ጥገኛ ሀይሎች ላለፉት ሁለት አመታት በከፍተኛ ደረጃ ሲሸረሽሩት ቆይተው አሁን ደግሞ በግላጭ ምርጫ አይደረግም ብለው ወስነዋል። ምርጫ ማድረግ ልጆቻችን፣ ወንድሞቻችን፣ እህቶቻችን እና ወላጆቻችን መስዋዕትነት የከፈሉበት የትግል ውጤት በመሆኑ ምርጫ የግድ እናደርጋለን፤ ምርጫ የማድረግ መብታችን ማንም አይከለክለንም ብለው ብፅናት የቆሙትን ህዝቦችን ጥገኛው አምባገነን መንግስት ማስፈራራት ጀምራል፡፡ ጦርነት ከፍቼ እናቶችን አስለቅሳለሁ እስከ ማለት ደርሳል።

የትግራይ እናቶች ልጆቻቸውን እንዳልቀበሩና በልጆቻቸው ሞትም እንዳላለቀሱ አያቅም እንዴ? የትግራይ እናቶች የማያለቅሱት የልጆቻቸው መስዋዕትነት ውጤት የሆነው ህገመንግስት ሲፀድቅ፣ ሲከብር እና በየአካባቢው የልማት ውጤቶች ሲመረቁ እልልልልል…የሚሉት ለዚህ ሲባል የተሰው ልጆቻቸውን በማስታወስ ነው። የትግራይ እናቶች የሚያለቅሱት ህገ መንግስቱ ለአንዴና ለመጨረሻ ሲጣል ነው። የሚያለቅሱት ኢትዮጵያችን ስታለቅስ፣ ስትበታተን እና ስትፈራርስ ነው። አሁንማ የትግራይ እናቶች እየታገሉ ነው። ለምን ያለቅሳሉ! የትግራይ እናት በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በሶማሊ፣ በሲዳማ፣ በወላይታ፣ በአፋር፣ በቤንሻንጉል፣ በሐረር፣ በጋምቤላ እና በሌሎች አከባቢዎች ህገመንግስቱ ይከበር የሚሉና እንዳይሸረሽር የሚታገሉ ህዝቦች እያየች ለምን ታለቅሳለች? ልጆችዋን የሚመስሉና የልጆችዋን ዓላማ ያነገቡ የኦሮሞ ወጣቶች፣ የሶማሊ ወጣቶች እና የሁሉም ብሄር፣ ብሄረሰቦች ህዝቦች ወጣቶች  ሲታገል እያየች የራስዋም ወጣቶች ’’ናይ አያታትና ሓደራ አይነዕብርን!’’ (የአባቶቻችን አደራ አናስደፍርም) እያሉ እየታገሉ እያየች ለምን የትግራይ እናት ታለቅሳለች? የዛሬዋ ኬርያ ኢብራሂም እንደ የትላንትናዋ ማርታ አልንበረከክም ብላ ለህዝብ የማላገለግልበት ከሆነ ስልጣን አልፈልግላቹሁም እያለች እንዴት የትግራይ እናት ታልቅስ? የትግራይ እናቶች፣ የአማራ እናቶች እና የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች እናቶች የሚያለቅሱት የታጋይ ሰማዕታት ዓላማ ውድቅ ሆኖ አገራችንና ህዝቦችዋ ሲበታተኑና ሲፈርሱ ካዩ ብቻና ብቻ ነው!

በአሁኑ ወቅት አገራችን እንዳትፈርስና ህዝቦችዋ እንዳይበታተኑ በሁሉም አቅጣጫዎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ተስፋ ሰንቀው ትግል እያካሄዱ ናቸው። ይህ ጥገኛና አምባገነን መንግስት ተገርስሶ በዲሞክራሲያዊ መንገድ በምርጫ የህዝቦች መንግስት ለመምስረት እየታገሉ ነው። Down! Down! Abiy! Down! Down! PP! እያሉ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ ከሰሜን እስከ ደቡብ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች ይህን መፈክር አንግቦው ዳግም እየታገሉ ናቸው። ህዝባችን ዳግም መስዋእትነት እየከፈለ ነው። ስለዚህ ይህ የትግራይ እናት አያስለቅሳትም። ይህ ማለት ግና አሁንም ዳግም መስዋዕትነት መክፈል፣ ከሰላምና ልማት ወደኃሊት ጉዞ እንድትጋዝ መገደድዋ አያሳዝናትም ማለት አይደለም፡፡ ያሳዝናታል። ቅርም ይላታል።

አሁን ያለንበት ሁኔታ የሰማእታት ቃልና አደራቸውን እንጠብቅ በሚሉና አደራቸውን በበሉና በተፃራሪ ዓላማ ተሰልፈው ፀረ-ህዝብ በሆኑ ክፍሎች መካከል ቅራኔ ተፈጥሮ ትግል የምናካሂድበት ወቅት ነው። ለምሳሌ ኢህዴን ጥቂቶች ያልተንበረከክነው ነገ አዕላፍ እንሆናለን ብለው ቆርጠው ታግለው በአስር ሺዎች አሰልፈው በሺዎች መስዋዕት ከፍለው ደርግን ገረሰሱ። የሰማዕታት አደራ ጠብቀው ትንሽ ተጉዘው ድህነት ኃላቀርነት በሽታ የሚጠፋበት መንገድ ተከትለው ልማት፣ ዕድገት፣ የትምህርት ጮራ መፈንጠቅ ሲጀምር፣ ጤንነት መስፈን ሲጀምርና ግስጋሴው እያየለ ሲመጣ መተካካት ተብሎ ሆዳሞች፣ ቅጥረኞችና ስልጣን ፈላጊዎች ድርጅቱን ተቆጣጠሩት። ከጥቂቶች ያልተበረከክነው ብለው ከዘመሩትም አዳልጧቸው ለጥቅም ሲሉ ከጥገኞች ጎራ ገብተው ቀሩ። ሰማዕታትን ረሱ። ወሎ፣ ጎንደር፣ ጎጃም፣ ሰሜን ሽዋ፣ አምቦ፣ ጅማ … ወዘተ  የተሰውት፣ የተቀበሩት፣ አደራ ያሉት ሰማእታት አደራቸው ተበላ። ኢህዴን/ብአዴን አለኝታየ ብለው አካላቸው የጎደሉ፣ ማየት የተሳናቸው፣ እጃቸው ወይም እግራቸው ተቆራርጦ በየሸንተረሩ የቀበሩትም አደራ ተበላ። እናትና አባት ልጆቻቸውን ሸኝተውና ሰውተው የጠበቁት ዓላማ ተሳክቶ ግን በጅምር ተኮላሽቶ ሲያዩ እርር ኩምትር ብለው በወለደ እንጀታቸው እያዘኑ ይገኛሉ። ግን የአማራና የትግራይ እናቶች አላለቀሱም።

ፍቅር እስከ መቃብር በሚል በቃል ሳይሆን በዓላማ ጥምረት ፈጥረው ሲጋዙ የነበሩት ህወሓትና ኢህዴን የየመንገዳቸው ይዘው ተለያዩ። አደራ የጠበቀና አደራ የበላ ሁነው ዳግም ላይገናኙ አሰላለፋቸውን አሰመሩ። የትግራይ እናት ይህን ክስተት ስታይ አዝናለች። ግን አላለቀሰችም። ህወሓትን ይዛ ለበለጠ ትግል ተነሳሳች እንጂ።

ህወሓት በልማት በዕድገትም ብንሆን ህዝባዊነታችን እየተሸረሸረ ነው እንታደስ ብሎ፣ የሰማዕታትን አደራ ጠብቆና ታድሶ፣ ራሱን አርሞ ለመቀጠል ሲወስን ኢህዴኖች በነፍጠኞች ተገዝተው ሰማዕታትን ረስተው ቆራጥ አመራሮቻቸውን ጥለውና አስረው ከደርጎች ጋር አብረው የሰማዕታትን አደራ ሙልጭ አድርገው በሉ። ህወሓትንም መጥላታቸው ሳይበቃ ሁሉንም ሀጥያትና የራሳችው ጉድም ሊያሸክሙት አላቅማሙም። ለስልጣን ያበቃቸውን ወርቁን ኢህዴንን አፍርስው ጥገኛውን አዴፓ ፈጥረውና መንደርደርያ ተጠቅመው ብግላጭ ኢሰፓ የሚሸተውን ብልጥግና ላይ ተወሸቁ። ጭልጥ ብለው ጥገኛ የኒዩ-ሊበራል ሀይል ሁነው አረፉት። የህወሓት የበላይነት ነበር ብለው ዋሽተው የእውነታቸውን በአብይ አህመድ የበላይነት የኃሊት መንገድ ጀመሩ። ህገ መንግስት ይቀየር! ኢትዮጵያ አሀዳዊ ስርዓት ነው የሚያዋጣት ብለው ሲያበቁ በሌላ በኩል ደግሞ የአማራ ድንበሩ እስከ ሁመራ ሰቲት ነው፣ ራያ የኛ ነው፣ የአክሱም ታሪክ የኛ ነው ብለው አክራሪ ብሄርተኛ ሆነው አረፉት። ቤንሻንጉል ገብተው ይጨፈጭፋሉ። ቅማንትን እንደ ዘር ለማጥፋት ለአራት ዓመታት ሳይታክቱ ህዝቡን ገደሉ፣ አቆሰሉ፣ ለስደት ዳረጉት ንብረቱን ዘርፈው መዝረፍ ያልቻሉትንም አቃጠሉት። በልማት መገስገስ ጀምሮ የነበረው ክልልና ህዝብ አሁን ሰላም ርቆት፣ ፍትሕ አጥቶ፣ ስርዐተ አልበኝነት ነግሶበት፣ የነበረው ልማትና ዕድገት ተረት ሆኖበት ግራ የተጋባ ክልል ሁናል። ሰለም የነበረው ክልል ግድያ ተበራክቶበት የክልሉ መገለጫ ግድያ ሆኗል።

Full Website