Back to Front Page
ቀደም ሲል የሕገ መንግሥቱ አጣሪ ጉባዔ ባስተላለፈው ጥሪ መሠረት ሙያዊ አስተዋጽዖአቸውን ለማበርከት በኢትዮጵያና በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሕግ ባለሙያዎች ሜይ 16 እና 18 በሸራቶን ሆቴል በመገኘት ሰፋ ያለና በቀጥታ ለሕዝብ የተላለፈ ምናልባትም በታሪካችን የመጀመርያው የሆነውን ውይይት አካሄደዋል። በሆነ የግል ምክንያት የሚፈለግብኝን ለማበርከት ባልችልም አሁን አጋጣሚ ሳገኝ የሂደቱ ተካፋይ መሆኔ ይታወቅልኝ ዘንድ ይህንን አጭር ጽሁፍ ላካፍላችሁ ወሰንኩ። በአጣሪ ጉባዔው ፕሬዚዴንት ሊቀመንበርነት የተመራው ውይይት ብቸኛ ትኩረቱ ቀደም ሲል በሚዲያ ተቋማት በኩል ባቀረባቸው ሁለት ዓቢይ ጉዳዮች ላይ ነበር ። እነሱም፣

መሠረት ስልጣን ላይ ሊቆዩ የሚችሉት እስከ መስከረም ወር ብቻ ነው። ከዚያ በኋላ አገሪቷን ማን ሊመራ እንደሚችል ሕገ መንግሥቱ ውስጥ በግልጽ የተካተተ ነገር የለም። ሕገ መንግሥቱ አንቀጽ

በተቀመጠው መሠረት ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን የማጣራትና በሚያደርገው ማጣራት መሠረት ሕገ መንግሥቱን መተርጎም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ የውሳኔ ሃሳብ ማቅረብ ይችላል።

የሕግ የበላይነት ሊሰፍን አለመቻሉ ግን አስገርሞኛል። ይህ ደግሞ ሌላ ታሪክ ስለሆነ እናቆየው።

1 ) የቅድመ ምርጫ ዝግጅቶች እና ምርጫ በሚደረግበት ወቅት የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ ለማወጅ የሚያስገድድ ሁኔታ ቢከሰት፣ በዚህም የተነሳ ምርጫ ማድረግ የማይቻል ቢሆን የምርጫ ዘመናቸው ያበቃው ምክር ቤቶችና የአስፈጻሚው አካል የሥራ ዘመን ምን ይሆናል?

የምርጫ ዘመናቸው ያበቃ የምክር ቤቶችና የአስፈጻሚው አካል የሥራ ዘመን ምን ይሆናል ለሚለው ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ ውስጥ በግልጽ የተቀመጠ መልስ ስለሌለ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተውን የፌዴሬሽን ምክር ቤትን መጠየቁና የፌዴሬሽን ምክር ቤቱም የሕግ አጣሪ ጉባዔን ሙያዊ ሃሳብ መጠየቁ ሕጋዊ አሠራር ነው። የሕገ መንግሥቱ አጣሪ ጉባዔም ሕገ መንግሥቱ ባጎናጸፈው ሁለት ሥልጣኖች ማለትም፣ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን የማጣራትና በሚያደርገው ማጣራት መሠረት ሕገ መንግሥቱን መተርጎም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ የውሳኔ ሃሳብ ለማቅረብ ይረዳው ዘንድ ባለሙያዎችን ማወያየቱ ትክክል ነው። በኔ ግምት ከውይይቱ በኋላ የአጣሪ ጉባዔው ሊወስድ የሚችለው እርምጃ፣

ተጠቅሞ ሕገ መንግሥቱን አሻሽሎ ለችግሩ መፍትሔ ሊያገኝ ስለሚችል የሕገ መንግሥት ትርጓሜ አስፈላጊ አይደለም፣ ወይም፣

ን በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ስላካተቱ ሕገ መንግሥቱን በማሻሻል ለተነሳው ጥያቄ መልስ ማግኘት ይቻላል ባይ ነኝ።

ሥር በተደነገገው መሠረት ለዚህ ችግር መፍትሔ ሊሠጡ የሚችሉት የሉዓላዊው ሥልጣን ባለቤት የሆኑት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ናቸው። የኢትዮጵያ ሕዝቦችም ሉዓላዊነት ደግሞ የሚገለጸው በአንቀጽ ን ተጠቅሞ በቀጥታ ከክልል ምክር ቤቶች፣ ከሕዝብ ተወካዮችና ከፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ጋር ተወያይቶ ዲሞክራሲያዊ በሆነ ሂደት በቀረበው ሃሳብ ላይ በሚካሄደው ውይይት የማሻሻሉ ሃሳብ አብላጫ ድምጽ ካገኘ ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለወደፊትም ሊገጥመን ለሚችል ተመሳሳይ ጥያቄ መፍትሔ እንዲሆን ያንን በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ማካተትና ማጽደቅ ብቻ ነው።

አዎ! ሕገ መንግሥቱን ዝም ብሎ የመበወዝ (የማሻሻል) ባሕል ካዳበርን ራሱን የቻለ አደጋና የማንወጣው ቀውስ ውስጥ ሊከተን ይችላል የሚል ፍርሃት አለ። አሁን ያጋጠመንን የሕግ ክፍተት በሕገ መንግሥቱ መሠረት የምንሞላው ግን ዛሬ ሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት ዕድሜ ለማራዘም ሳይሆን፣ ከላይ እንዳልኩት ተፈጥሮ በራሱ ፕሮግራም መሠረት አንድ ቀን የሆነ ማህበረሰባዊ ችግር ቢያመጣብን የሚያስከትለውን ሕገ መንግሥታዊ ውዝግብ በቀላሉ ልንወጣው እንድንችል ይረዳናል ብዬ ስለማምን ነው። ሌሎችም አገራት ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ሁኔታ ሲከሰት ምርጫና የምክር ቤቶችን የሥራ ዕድሜ ለማራዘም ተመሳሳይ አንቀጾች በየሕገ መንግሥታቸው ውስጥ ማካተታቸው አንድ አሳማኝ ድርጊት ነው። ስለዚህ አንድ ራሱን የቻለ ለወደፊት ተመሳሳይ ችግር ሲያጋጥመን ልንጠቀምበት የሚያስችለንን አንቀጽ
Full Website