የሚነሳው፤ አንድም በሃገር ጉዳይ እና በሕግ ጥሰት ከልብ በሚቆረቆሩ ሰዎቸ ሲሆን፤ ሌላ ደግሞ፤ በምርጫ ተወዳድረው፤ የሕዝብን አዎንታዊ ፈቃድ አግኝተው ሥልጣን ለማያዝ በማይችሉ የፖለቲካሃይሎች በአቋራጭ ሥልጣን ለማግኘት የሚያነሱት ጥያቄ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት ስለሕገ መንግስት ቀውስ መኖር የሚናገሩ ሰዎች፤ ከልብ ስለሕግ አስበው እና ለሃገር ተቆርቁረው ነው ለማለት ያስቸግራል። አንዳንዶቹ ሕግ ሲጥሱ፤ ሲያስጥሱ እና አሁንም ሕግ በመጣስ ላይ ያሉ መሆናቸው ነጋሪ አያሻውም። ኢትዮጵያ በመጀመርያ፤ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ቀውስ ውስጥ ነው ወይ ብሎ ከመመለስ በፊት፤ የሕገ መንግስት ቀውስ ምንድነው የሚለውን ጥያቄ መመለስ ያስፈልጋል። ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ጁልያ አዛሪ የተባሉ የማርኰት ዩኒቨርስቲ አሶስየት ፕሮፌሰር እና ሴት ማስኬት የተባሉት የዴንቨር ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር ያስቀመጡትን መመዘኛ መመለከቱ ይበጃል። በነዚህ የፖለቲካ ሳይንስ ልሂቃን አመለካከት፤ የሕገ መንግስት ቀውስ ተፈጠረ የሚባለው አራት ነገሮች ሲከሰቱ ነው። እንዚሀም ፩. ሕገ መንግስቱ ስለተነሳው ጉዳይ ምንም ሳይል ሲቀር፤ (፪) የሕገ መንግስቱ ትርጓሜ አውዛጋቢ ሲሆን (፫) ሕገ መንግስቱ ምን መደረግ እንዳለበት ግልጽ ቢሆንም፤ ሕገ መንግስቱ ተግባራዊ እንዳይሆን ፖለቲካዊ ሁኔታው የማይቻል ሲያደርገው፤ (፬)ተቋማቱ በራሳቸውውድቅ ሲሆኑ ወይም ሲፈርሱ ነው። እነዚህን መመዘኛዎች ስንገመገም፤ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ቀውስ ላይ ነው ለማለት እጅግ ያስቸግራል። በአሁኑ ሰዓት ሕገ መንግሥቱ ቀውስ ውስጥ ገብቷል የሚሉን ሰዎች፤ ሕገ መንግሥቱን በቅጡ ያልተረዱ እና ያላነበቡ፤ወይም፤ እኩይ የፖለታካ ዓላማ አንግበው፤ ደጋፊዎቻቸውን በሃስት በማነሳሳት፤ ከሕገ መንግስታዊ አሰራር ውጭ፤ ያለሕዝብ ፍላጎት እና ፈቃድ፤ በራሳቸው አነሳሽነት በሚፈጠር ቀውስ እራሳቸውን ወደ ሥልጣን ማምጣት በሚፈልጉ ሃይሎች ሊሆን እንደሚችል አልጠራጠርም። የሕገ መንግስትቀውስ አለ ሲሉ የሚከራከሩብት ምንም ዓይነት ተጨባጭ መረጃ አያቀርቡም፤ አላቀረቡምም። ለሃሳባቸው መከራከርያ የሚያነሱት፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ፤ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ሊካሄድ ስለማይችል፤ አሁን ያለው የመንግስት የሥልጣን የጊዜ ገደብ በመስከረም ያበቃል፤ ከዛ በኋላ ይህ መንግሥት እንደ መንግሥት ሊቀጥልበት የሚችል ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣን የለውም የሚል ነው። ይህ ክርከር፤ ትንሽም ቢሆን ሕገ መንግስቱን አተኩሮ ካየ ማንም ዜጋ የሚጠበቅ አይደለም። የእነዚህ ሰዎች ክርክርም፤ጭብጥ በመመርኮዝ የሚደረግ ክርክር ሳይሆን፤ የሰዎችን ስሜት በመኮርኮር ቀውስ ለመፍጠር እና በአቋራጭ ወደ ስልጣን ለመምጣት የሚደረግ “በአሸዋ ላይ የቆመ” ክርክር ነው።
Full Website