ኮቪድ -19 እንጂ ሐሳብ አይገድልም / የኢትዮጵያ ፖለቲካ መረጋጋትን ይጠይቃል ።

ልኡል ገብረመድህን ( አሜሪካ ) 5.16.2020

ሆኖም ከመንግስት ሆነ መንግሥት ከሚቃወሙ የፖለቲካ ድርጅት አባሎች ጠንከር ያሉ ዛቻና ማስፈራሪያ አዘል ንግግሮች እና አስተያየቶች ሲንጸባረቁ ይታያሉ ። የፖለቲካ ሰልጣን የፕሮግራም ጉዳይ ነው ። ለኢህአዴግ ስርአት ውለታ የቻረው የደርግ ስርአት እንጂ በነበረው የፖለቲካ ጥራት አይመሰለኝም። የደርግ አገዛዝ ከግድያና አፈና ይልቅ ለሐሳብ ውይይት የተከፈተ በር ቢኖረው መልካም ነበር ። ግን አልሆነም ፣ አልነበረም ። የደርግ ስርአት ከሐሳብ ውይይት ይልቅ የሐይል ሚዛን መከተሉ ስህተት ነበር ። የአንድ አገር የውስጥ ችግር ለመፍታት ሐይል መጠቀም አዋጪ ሐሳብ አይደለም ። የውስጥ ችግር በሁለት ዋና የአፈታት ተሰልቶ መከናወን ይኖርባቸዋል ።የመጀመሪያ እና አዋጪ ሰልት በሐሳብ ልዕልና መወያየት እና መደራደር ነው ። ይህ ማለት በተፈጠሩ የውስጥ ችግሮች የጋራ መፍትሄ ለማቅረብ የሚከናወን የመፍትሄ ሐሳብ ነው ። ሌላኛው ህጋዊ መፍትሄ ነው ። ይህ ማለት በውይይት እና ድርድር መፍትሄ ያላገኙ ጉዳዮች መፍትሄ የሚያገኙበት አካሄድ ። ከላይ የተጠቀሱ ሁለት የመፍትሄ ተሰልቶ ከሴራ የፖለቲካ አሰተሳሰብ በተቃራኒ የቆሙ በመሆናቸው የጠራ የፖለቲካ አሰተሳሰብ እና የሐሳብ ልዕልና መሸከም የሚችል አሰተሳሰብ በእጅጉ ያሰፈልጋል ። የሐይል እርምጃ ህጋዊ መፍትሄ አይደለም ። ህጋዊ መፍትሄ በህጋዊነት ዙሪያ ፣ በህግ እና ህገመንግስት መዳኘት ማለት ነው ። ይህ የሚያስፈፅም ተቋም ደግሞ ከፍተኛ የፌዴራል ፍርድ ቤት ነው ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የመሪነት በትረ ሰልጣን ሲጨብጡ ውሰጠ ወይራ ባላውቅም ከፍተኛ ድጋፍ እና አድናቆት የተቻራቸው ከህዝባዊ ወያነ ትግራይ (ሕወሓት ) ነበር ። ሆኖም ድጋፉ እና አድናቆቱ በሂደት እየቀነሰ መጥተዋል ። ሕወሓት በግዞት የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች አገራቸው ተመልሶ ሰላማዊ የስልጣን ትግል እንዲያደርጉ የበኩሉን ሀላፊነት ተወጥተዋል የሚል እምነት አለኝ ። ይህ ከሆነ ደግሞ ሕወሓት የለውጡ ተሳታፊ ነበረ ማለት ነው ። ሌላው እና በተግባር የታየው በዘመነ ኢህአዴግ ሲፈፀሙ የነበሩ የህግ ጥሰቶች ሕወሓት አልካደም ። ሆኖም በዘመነ ኢህአዴግ ለተፈፀሙ ስህተቶች እና የህግ ጥሰቶች የጋራ ስህተቶች በመሆናቸው በጋራ እንጠይቅ የሚል አቋም መያዙ አያስወቅሰውም ። ይልቁንም የሚያሰመግነው ተግባር ነው ። ሕወሓት ደም ለሰጠ የትግራይ ህዝብ ንጹሕ የመጠጥ ዉሃ ማቅረብ ያልቻለ የፖለቲካ ስብስብ ቢሆንም  ለትግራይ ህዝብም በግልጽ ይቅርታ የጠየቀ ይመሰለኛል ። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሰርአት ሆነ የመንግስት ስርአት ገና ከባንዳነት አመለካከት አልወጣም ። ሁሉም ባንዳ ይላል ። ሆኖም ባንዳ የፖለቲካ መሪ ራሱን መፈተሽ ይኖርበታል ። ሕወሓት ራሱ የባንዳ አመለካከት ያለው ፣ ተገቢ ያልሆነ ጠላት እና ወዳጅ ለይቶ የሚያጠቃ ፣ በሴራ ፖለቲካ የተካነ ፣ በሐሳብ ልዕልና የከሰረ ፣ ኢትዮጵያን እየጠላ ኢትዮጵያ ሲገዛ የነበረ ፣ የአምባገነን ሰልት መገልገያ የነበረ የግምገማ የሚሉት የድንቁርና አሰራር አራማጅ ድርጅት ነው  ። ሆኖም ሕወሓት ለኢትዮጵያ ህዝብ ካጠፋው ይልቅ መልካም የሰራው ይበልጣል ።  ሕወሓት ሰልጣን ከመያዙ በርካታ ዘመናት የኢትዮጵያ ህዝብ የነበረበት የኑሮ ሁኔታ መለስ ብሎ መፈተሹ ተገቢ ነው ። በእኔ እምነት የስራ ጊዜያቸው ተጠናቆ የሚመረቁ የልማት ስራዎች በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ የሕወሓት አሰተዋጽኦ አለበት ። ለዚህም የኢትዮጵያ ህዝብ የሕወሓት አሰተዋጽኦ እውቅና ሊሰጠው ይገባል ። የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሰተዳደር አንዱ ችግር ለሚገባው ተገቢውን ምስጋና ክብር መሰጠት ያለመቻል ይመሰለኛል ። የሕወሓት አመለካከት እና አሰተሳሰብ መጥላት የሕወሓት መልካም የልማት እና የእድገት አሰተዋጽኦ መጥላት አይቻልም ። ምክንያት የሕወሓት የልማት አሰተዋጽኦ መጥላት ምክንያታዊ አይሆንም ። በኢትዮጵያ መንግስት ሆነ የመንግሰትነት ሰልጣን ለማግኘት መንግስት የሚቃወም ሁሉ ህግ እና ህገ መንግስት በተግባር ተግባራዊ ስራ ሲሰራበት አልነበረም ። የመንግስት ሀላፊዎች ራሳቸው ህግ ባለማክበር በሚፈፅሙት ስህተት ለህግ ተገዢ ይመሰል ህግ ይከበር ሲሉ መሰማት ምንኛ ያሰፍራል ። የህዝብ መሪ ሆኖ ህግና የህግ ጥሰት እየፈፀመ ሌላውን በህግ ጥሰት መወንጀል አይቻልም ። የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ከመግቢያው ጀምሮ ችግር ያለበት ነው ። ህገ መንግሰቱ የአገር እና የህዝብ  አንድነት በልዩነት ይላል ። ይህ ደግሞ ከፍተኛ ፌዝ እና ትያትር ነው ።  የህገ መንግስት አርቃቂ አካል ለአገረ ኢትዮጵያ የፃፉት ህገ መንግስት መስሎ አይሰማኝም ። ሆኖም የህገ መንግስት ክፍተቶች ለማረም በህገ መንግሰቱ በተቀመጠው የማስተካከያ ሂደት መሄዱ ለአገር እና ለህዝብ የሚጠቅም ጉዳይ ነው ። አማራጭም የለውም ። በውጩ ቀመር የካቲት ወር 1987 ጀምሮ በተግባር ያለ የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አምሰት አገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ ለማከናወን የቻለ ህገ መንግስት ነው ። ምርጫው ተከታታይ ምርጫ ነበር ። የምርጫ መዛነፍ የነበሩ ቢሆንም በውጩ ቀመር 1995 ፣ 2000 ፣ 2005 ፣ 2010 ፣2015 በዚሁ በ1987 በፀደቀው ህገ መንግስት በሚፈቅደው መሠረት መርጫ ተከናውነዋል ። በተካሄዱት የምርጫ አመታት በድህረ ምርጫ ብዙም የከፋ ግጭት አልነበረም ብሎ ማለፍ የሚቻል አይሆንም ። መንግስት የድህረ ምርጫ ግጭቶች በውይይት ከመፍታት ይልቅ የሐይል እርምጃ ሲጠቀም ነበር ። ይህ በመሆኑ ደግሞ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ተሳትፎ እና ለውጥ ላይ ችግር አስከትለዋል ። ለበርካታ የፖለቲካ አመራሮች እና አባሎች ለስደት እና እስራት ተጋብዘዋል ። ከአገር እንዲወጡ የተገደዱ የፖለቲካ አመራሮች እንደ አማራጭ የሌላ አገር እገዛ ሲያፈላልጉ ቆይተዋል ። ከግብፅ ሆነ ከኤርትራ መንግስት ድጋፍ ሲደረግላቸው የነበሩ አሁን አገራቸው የተመለሱ የፖለቲካ ድርጅቶች እና አመራሮች እንዳሉ ይታወቃል ። የዚህ ሁሉ ችግር ከሐሳብ ውይይት ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለ የሚያሳይ አብነት ነው ። የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ በየአምስት አመት እንዲከናወን ይገልጻል ። ከኮቪድ -19 ወረርሽኝ በሽታ ጋር በተያያዘ ምርጫ እንዲያስፈፅም በህገ መንግስት ሙሉ ሰልጣን የተሰጠው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ስድስተኛ አጋር አቀፍ እና ክልላዊ ምርጫ ማከናወን እንደማይችል ከፍተኛ ሰልጣን ላለው የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል ። በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ስራው በሚገባ መሰራቱ ምስጋና ይገበዋል ። ህግ ማክበር ከዚህ ይጀመራል ። የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የስራ ዘመኑ ሊያበቃ በጣት የሚቆጠሩ ወራት ይቀሩታል ። በተመሳሳይ የህዝብ ምክርቤት ስራ ሲያቆም የመንግስት ሰልጣንም ከምክር ቤቱ ጋር ያበቃል ።  የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ህዝብ የሚጎዱ ተፈጥራዊ ሆነ ሰው ሰራሸ ክስተቶች በሚያጋጥሙ ወቅት የመንግስት ሰልጣን ለማራዘም የሚያግዝ ህጋዊ ማዕቀፍ አንቀጽ አልጠቀሰም ። በመሆኑም የመንግስት ሰልጣን ለማራዘም ህገ መንግሰታዊ መፍትሄ ማፈላለጉ የሚበጅ አማራጭ ይመሰለኛል ። መንግስት ከራሱ ሆነ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በግልፅነት ጥልቀት ያለው ወይይት ማድረግ ለአገር ሆነ ለህዝብ በጎ ወጤት ያመጣል ። የጠቅላይ ሚኒሰትር ዶክተር አብይ አህመድ አሰተዳደር ከፖለቲካ ድርጅት አመራሮች ጋር መወያየት የተጀመረው ጅምር መልካም ነው ። ሆኖም ውይይቶች በጥላቻ እና ቂም በቀል ሳይሆን በሐሳብ ልዕልና አማራጮች ላይ ውይይት ማድረግ ተገቢነት ያለው አካሄድ ነው ። መንግስት ሆነ ተቃዋሚ የፖለቲካ ሐይሎች ዋልታ ላይ ሆኖ ቃላት ከመወራወር ተቆጥቦ ለአገር እና ለህዝብ የሚበጅ አለ የሚሉት ሐሳብ ላይ ተቀራርቦ ውይይት ማድረግ የአስተሳሰብ ልዕልና ነው ። መንግስት ሆነ ተቃዋሚ የፖለቲካ አመራሮች ቅድሚያ መፍትሄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ መረባረብ ይኖርባቸዋል የሚል እምነት አለኝ ። አሁን ለኢትዮጵያ የሚያስጨንቃት ምርጫ ማካሄድ አይደለም ። አሁን የኢትዮጵያ የቅድሚያ ቅድሚያ የኮቪድ -19 አለምአቀፋዊ በሽታ በትኩረት መከላከል ነው ። ከዚህ ቀዛፊ በሽታ በላይ አንገብጋቢ ጉዳይ የለም ። በሽታው ከጦርነትም በላይ ነው ። በሸታው  ከፖለቲካ ሰልጣን በላይ ነው ።  ሰው እየሞተ ምረጥ መባል ያለበት አይመሰለኝም ። በጦርነት ጊዜ ውጊያ በሌለበት አካባቢ የሚኖር ህዝብ ይመርጥ ይሆናል ። በሽታው በየቀየው ባለበት ወቅት ምርጫ ለማካሄድ ማሰብ በራሱ ንፁህ ወንጀል ነው ። የዘንድሮ ምርጫ በጥንቃቄ መያዝ ያለበት ጉዳይ ነው  ። የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የወሰነው ውሳኔ ህጋዊ በመሆኑ መከበር አለበት ። የህጋዊ ተቋማት ህጋዊነት ውሳኔ ለፖለቲካ ሰልጣን ሲባል ህጋዊነት ውሳኔ ማጣጣል በህጋዊነት የሚያምን የፖለቲካ ድርጅት ባህሪ አይደለም ። የጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ መንግስት ምርጫ ማራዘም የሚያሰችሉ የመፍትሄ ሐሳቦች ማቅረብ ስህተት ባይሆንም አቀራረቡ ላይ ግን ከፍተኛ ስህተት ተፈፅመዋል ። ስልጣን ያለው መንግስት ራሱ ተወያይ እና ተደራዳሪ እንጂ ራሱ የምርጫ ማራዘም ደራሲና ተዋናይ መሆን አይችልም ። ምርጫ የማራዘም ጥናት ምክረ ሐሳብ መቅረብ የነበረበት በፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክርቤት አልያም በፌደሬሸን ምክርቤት ፣ አልያም በገለልተኛ የህግ እና የህገ መንግስት ባለሙያዎች አማካኝነት መሆንአማካኝነት ። በእኔ ምልከታ የጠቅላይ ሚኒሰትር ዶክተር አብይ አሰተዳደር ጥያቄ ምልክት ውስጥ የገባ ይመሰለኛል ። የሴራ ፖለቲካ መንገድ የሚከተሉ ይመሰለኛል ። ይህ ከሆነ ደግሞ የህዝብ ተቀባይነታቸው አደጋ ውሰጥ ይገባል ። ከመስከረም 25 በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት ይፈርሳል ፣ ፖሊስ ሆነ መከላከያ ፣ እንዲሁም ህዝብ ለመንግስት አይታዘዝም የሚሉ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት አመራሮች ከስህተታቸው ቶሎ መውጣት ይኖርባቸዋል ። የጋራ መፍትሄ ከማፈላለግ ዛቻና ማስፈራሪያ ንግግሮች አስተያየቶች መሰንዘር ከተቃዋሚ ፖለቲካ አመራሮች የሚጠበቅ አይሆንም ። ፖሊስ ፣ የአገር መከላከያ ፣ እና ህዝብ ለመንግስት አይታዘዝም የሚል አሰተያየት በራሱ ደረቅ ወንጀል ነው ። በህግ ያስጠይቃል ። በወንጀል የሚያሰጠይቁ የፖለቲካ አስተያየቶች የህግና ህገ መንግስት ባለሙያ ማማከር የተሻለ አማራጭ ይመሰለኛል ። ችግሩ ጥቂት የኢትዮጵያ የፖለቲካ አመራሮች ሁሉም እናውቃለን ባዮች በመሆናቸው በቀላሉ የፖለቲካ ሰብራት (ኪሳራ) ሲያጋጥማቸው ይታያል ። የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች በምክንያታዊ ሐሳብ ከመከራከር ይልቅ ዛቻና መናናቅ ያስቀድማሉ ። ዛቻና መናናቅ ጎጂ የፖለቲካ ባህል ነው ። ዛቻና መናናቅ የባንዳነት ባህሪ ነው ። ትግራይ እየገዛ ያለ የፖለቲካ ድርጅት (ሕወሓት ) ዘንድሮ ለማካሄድ እቅድ ተይዞለት የነበረ ምርጫ መራዘም የለበትም ፣ ምርጫ መካሄድ አለበት ፣ ምርጫ ለማስፈፀም የሚያቆመኝ ምድራዊ ሐይል የለም ማለቱ ግልጽነት የጎደለው አካሄድ መሰሎ ይሰማኛል ። ሕወሓት የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ መመሪያ መከተል እና መቀበል አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው ። ክልላዊ ምርጫ ሲፈፀም ህጋዊነት እና ቅቡልነት ማግኘት አለበት ። በኢትዮጵያ ምርጫ ማስፈፀም የሚችለው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ነው ። የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ወረቀት ማከፋፈል ፣ የምርጫ ሂደት ታዛቢ ሐይል ማሰማራት ብቻ ሳይሆን ህጋዊ እውቅናም ይሰጣል ። ሕወሓት በትግራይ ክልል ምርጫ አከናውናለሁ ካለ የትግራይ ህዝብ ለሉአላዊነት ጥያቄ  ለመመለስ ከባድ ይሆናል ።  በመሆኑም ምርጫው የሰላም ምርጫ ከመሆን አልፎ የጥፋት ምርጫ ይሆናል ። በመሆኑም ሕወሓት ተረጋግቶ ማሰብ ይጠበቅበታል ። ሕወሓት ለብቻው ምርጫ ማካሄድ በራሱ ላይ የማያገግም ጥፋት ማወጅ ይሆናል ። በመሆኑም የጋራ የመፍትሄ ሐሳብ ይዞ ከፌደራል መንግስት ጋር በመፍትሄ ሐሳብ ላይ መወያየት እና መደራደር አለበት ። ሕወሓት በትግራይ ምርጫ ማካሄድ ለትግራይ ህዝብ የሚያመጣው አንዳች ፋይዳ የለውም ። በመሆኑም ለዜሮ ውጤት መሰራት ያለበት አይመሰለኝም ። ከእልህ እና የሴራ ፖለቲካ ተላቆ በመፍትሄ ሐሳብ ዙሪያ ተኩረት ተሰጥቶ ለውይይት መቅረብ ከሁሉም የተሻለ አማራጭ ነው ። የጠቅላይ ሚኒሰትር ዶክተር አብይ አህመድ አሰተዳደር በሕወሓት ላይ የሐይል እርምጃ ውሰጥ መግባት ጥፋት እንጂ  መልካም የፖለቲካ መረጋጋት አያመጣም ። የሐይል ሚዛን መጠቀም የአምባገነን መሪ አሰተሳሰብ ነው ። የፖለቲካ አሰተሳሰብ እና አሰላለፍ በሐይል መደፍጠጥ ከቶ አይቻልም ። የፖለቲካ አሰላለፍ እና አመለካከት በምክንያታዊ ሐሳብ ለመቀራረብ መጣር እንጂ  በፖለቲካ ሴራ ከቶ አይፈታም ። የሕወሓት አንዱ መሠረታዊ ችግር ራሱ በሐሳብ ልዕልና የሚመራ የፖለቲካ ድርጅት በመሆኑ ከውስጥ ሆነ ከውጭ የሚያጋጥሙት ፖለቲካዊ ችግሮች ከትግራይ ህዝብ ጋር የማስተሳሰር የጥገኝነት ባህሪ ያለው ፣ ለትግራይ ህዝብ የሚመጥን ንፁህ የፖለቲካ ፣ የማህበራዊ ፣ የምጣኔ ሀብት ፣ እንዲሁም ዲሞክራሲ በተግባር ችግር ያለባት የፖለቲካ ድርጅት ነው ። ሕወሓት ዘመኑ የሚጠይቀው የፖለቲካ አሰተሳሰብ ለውጥ ማድረግ ይኖርበታል ። የፖለቲካ የሐሳብ ልዕልና መያዝ ይኖርበታል ። ክልላዊ እና አካባቢያዊ አልፎም አህጉራዊ የፖለቲካ የሚተርፍ የፖለቲካ አስተሳሰብ ለውጥ ያሰፈልጋል ። ሕወሓት በፍጥነት የፖለቲካ ፣ ኢኮኖሚ ፣ ማህበራዊ ፣ እንዲሁም  ዲሞክራሲያዊ ፕሮግራም ለውጥ ካልተደረገ የውስጥ ሆነ የውጭ የፖለቲካ ጫና በዘላቂነት መመከት የሚታሰብ አይሆንም ። የመደራደር አቅም በምክንያታዊ ሐሳብ ማዳበር ያሰፈልጋል ። በትግራይ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በጋራ መሰራት መቻል ራሱ የቻለ ለውጥ ነው ። ለውጥ ካለ ድግሞ  የህዝብ አመኔታ ይጨምራል ፣ የህዝብ አንድነት ይጎለብታል ። በትግራይ ሰም የፖለቲካ ተሳትፎ ከሚያደርጉ የፖለቲካ ድርጅቶች ከጥላቻ በፀዳ ፣ በነፃነት ፣ በምክንያታዊነት ሐሳብ ተቀራርቦ መወያየት እና የጋራ የመፍትሄ ሐሳብ ማጠናከር ተገቢነት ያለው ጉዳይ ነው ። የመጨረሻ ፍርድ ሰጪ ህዝብ በመሆኑ በትግራይ ክልል በህገ መንግሰት መሠረት የፖለቲካ ተሳትፎ የሚያደርጉ ገዢ መንግስት የሚቃወሙ የፖለቲካ ድርጅት በሕወሓት ጫና ሊደረግባቸው አይገባም ። የጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ አሰተዳደር ከሕወሓት አመራሮች ጋር በምርጫ መራዘም ሆነ ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ መወያየት እና የጋራ መፍትሄ ማበጀት ተገቢነት ያለው አካሄድ ነው ።  ከምክንያታዊ ውይይት ምክንያታዊ መፍትሄ ይፈጠራል ። የእልህ እና ጥላቻ አሰተሳሰብ ውጤት ሐይል መጠቀም ያስከትላል ። የጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ አሰተዳደር በግልጽ ባይገለፅም መንግስታቸው ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ለህዝብ ግልጽ አድርገዋል ። በእኔ እይታ ሕወሓት ያነሳው ጥያቄ ህጋዊ ፣ ህገ መንግሰታዊ ነው ። በመሆኑም ህጋዊ መልስ ያሻዋል ። የፌዴራል መንግስት በሕወሓት ላይ የሚወሰደው ህጋዊ እርምጃ ህጋዊነት አይኖረውም ። የተሻለ አማራጭ ተቀራርቦ ፣ ተወያይቶ ፣ ተደራድሮ የጋራ መፍትሄ ላይ መድረሱ ተገቢነት ያለው እና ተመራጭም ነው ። ትግራይ ከኤርትራ ጋር ያላት ማህበራዊ ሆነ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት በአጭር ጊዜ ውሰጥ ለማሳለጥ ሕወሓት ከፌዴራል መንግስት ጋር የሚኖረው መልካም ግንኙነት ላይ የተመሰረተ ነው ። በመሆኑም ሕወሓት በሐሳብ ልህቀት የተሻለ ስራ መሰራት አለበት ። ምክንያታዊ የፖለቲካ የሐሳብ ልዕልና ለሕወሓት በእጅጉ ይጠቅማታል ። ቅድመ ኮቪድ -19 ሆነ ድህረ ኮቪድ -19 ያሉት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች በተናጠል የሚፈቱ አይሆኑም ። በተለይ ድህረ ኮቪድ -19 የአለም የፖለቲካ ሆነ የኢኮኖሚ ለውጥ ማስከተሉ የማይቀር ጉዳይ በመሆኑ ለጋራ ጥቅም የጋራ ጉዳዮች ላይ በጋራ መረባረብ ያሰፈልጋል ። በህግ ማዕቀፍ ውሰጥ ሆኖ የጋራ ጥቅም ማስጠበቅ የፌዴራል ስርአት ተግባራዊ ሂደት ነው ። ሆኖም ህጋዊ ለመሆን ህግ መጣስ ተገቢነት የለውም ። በመሆኑም ሕወሓት ምርጫ ሂደት ውሰጥ ከመግባቱ በፊት በቂ የህግ እና የህገመንግስት ባለሙያዎች ሙያዊ አሰተያየት ማዳመጥ ተገቢ ነው ።
Full Website