አሳ አጥማጅ ባህሩ ፀጥ ሲል አይወድም ምክንቱም አሶቹ ስለሚረጋጉ መረቡን አይተው ሊሸሹ ይችላሉ ወይንም ከባህሩ ጥልቀት ውስጥ ሊሆኑ ያችላሉና፡፡ ባህሩ ወጀብ ሲመታው አሶች ወደላይና ወደ ዳርቻ ሊገፉ ይችላሉ፤ በተጨማሪም ግራ ተጋብተው ሳያውቁት ወደ መረቡ እየዘለሉ ሊገቡ ይችላሉ፡፡ “በታመሰ ዉሃ አሳ ማጥመድ“ የሚለው የኢንግሊዝኛ ተረት የፖለቲካ ጥቅም የሚፈልጉ ግለሰቦች ወይንም ቡድኖች ህዝቡ ተረጋግቶ እንዳያስብና በውጥረትና በጭንቀት የነሱን መከታነት እንዲሻ የሚያደርጉበት ቅንነት የጎደለው ዘዴን ለማመልከት የታለመ ነው፡፡ ይህ ዘዴ የአሳው መኖሪያ የሆነው ባህርን ቀውጢ በማድረግ አሳው የመጣበትን አደጋ በእርጋታ እንዳያስተውል ሲያደርግ በአሳው የተመሰለው ህዝብም ኑሮው በውዝግብ የተሞላ በማድረግ የግለሰብ ፖለቲከኞች ሆነ የፖለቲካ ቡድኖችን ድብቅ አላማ ለማስተዋልና ጠንቅቆ ለመገንዘብ እንዳይችል ይሆናል፡፡ ሚድያዎን አፍነው ይዘው ከመፋቀር ይልቅ መጣላትን የሚያስቀድሙ፤  “ይቅር በኛ ያብቃ ትውልድ ይዳን“ ከመባባል ይልቅ ቁስል ላይ ስንጥር በመትከል የጥላቻ ስሜት ተባብሶ ወደ ቀጣዮቹ ትውልዶች እንዲሻገር ለማድረግ ቀንና ሌሊት የሚታክቱ፤ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ እንዳትበቅል የሚሉ ላለፉት 50 አመታት ከስልጣን የተገለሉ ሶስት መንግስታትና ተከታዮቻቸው፡ ቀጣዩ መንግስት ከነሱ የባሰ እንዲሆን በማስደረግ ህዝብ እንዲናፍቃቸውና ወደፊት ሳይሆን ሁል ጊዜ ወደ ኋላ እያየ እንዲኖር የሚጥሩ፤ ኢትዮጵያ ያለችበት ጂኦፖለቲካዊ አቀማመጥና የነፃነት ተምሳሌት ሆና የመኖሯም ታሪክ ለሚያበሳጫቸው ሃይሎች ጥቃት ምቹ ሆና ብትገኝ የማያስጨንቃቸው፤ የግል ኑሯቸው የተደላለደለ እስከሆነ ድረስ በደሃው ህዝብ ላይ ቢነግሱ የማይጎረብጣቸው ኢትዮጵያ ሳትዘራቸው የበቀሉ አገሪቱን ወደ ጥፋት ጎዳና እየመሯት ነው፡፡ ስልጣን ጥቅም ከሌለው ማንም አይፈልገውም፤ ለህዝብ ራሱን አሳልፎ የሰጠ የመልአክ ዝርያ ያለው ካልሆነ በስተቀር፡፡ ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ የሚብስ ይመስላል፡፡ “ኢትዮጵያውያን እርስ በርስ ይፋቀራሉ፤ አገራቸውን ይወዳሉ“ የሚሉ “የላም በረት“ የማይባልባቸው ተረቶች አሉ፡፡ እንዲህ አይነት አባባሎች በተግባር አይታዩም፡፡ “አገር ማለት ሰው ነው“ የሚለው አባባል ይመቸኛል፡፡ ለጋራና ሸንተረሩ እየዘፈኑ ጋራና ሸንተረሩ ላይ የሚኖረው በሚልዮኖች የሚቆጠረው ድሃ ወገን ተረጋግቶ የእለት ህይወቱን እንዳይገፋ ያለውን ልዩነትን እየለጠጡ አዲስም እየፈጠሩ ሰላም ማሳጣት ምኑ ላይ ነው አገር ወዳድነቱ? ባሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ እጅግ አስጨናቂ ነው፡፡ ለልማት ዋስትና ይሆነኛል ብላ የጀመረችው የግድብ ግንባታ ታላቅ ፈተና ገጥሞታል፤ ቀላል መፍትሄ ያለውም አይመስልም፡፡ አገራቸውን ወደው ፍላጎቱን ለማስፈፀም ቆርጠው በተነሱት ግብ አካሄዱን አይተው ሸክሙን ይቀሙታል“ የሚባል ተረት አለ፡፡ ቀማኛ በተፈጥሮው ፈሪ ነው፡፡ብርም ንብረትም ቀምቶ በሰላም ቤቱ ገብቶ ለመጠቀም እንጂ በቅሚያ ላይ “በጀግንነት“ መሞት አይፈልግም፡፡ለዚህም ነው የሚቀማውን መንገደኛ አቅም በአረማመዱ የሚለካው፡፡ይህ ተረት ለቀማኛ የተፈጠረ አይደለም፡፡ ደካማ ሰውና ደካማ አገር ፈሪም ቢሆን እንደሚደፍረው ለማመልከት ነው፡፡ ግብፅ የኢትዮጵያን አረማመድ በሚገባ አስተውላለች፡፡ ለዚህ የተልፈሰፈሰ አረማመዷ ግብፅ በሰፊው አስተዋፅኦ አድርጋለች፤ ቢሆንም ተጠያቂ አይደለችም፡፡ ተጠያቂው “አገሬን እወዳለሁ፤ ውለታ ሰርቼላታለሁ፤ ከወያኔ አፅድቻታለሁ“ እያለ ሲፎክር ከርሞ በወያኔ ጊዜ የነበረውን አንፃራዊ ሰላም የሚያደፈርሰው ነው፡፡ ለኢትዮጵያ አንድነት መሰረት የሚሆነው መከባበር ነው፡፡ አንዱ ህዝብ ሌላውን ካላከበረው በመልሱ አክብሮትን መጠበቅ የለበትም፡፡ እኔ የምሰራው ሁል ጊዜ ትክክል፤ አንተ የምትሰራው ሁል ጊዜ ስህተት ነው የሚባባል ከሆነ ራስን የአምላክ ባህርይ አላብሶ ሌላውን ማሰይጠን ይሆናል፤ ይህን የሚቀበልም አይኖርም፡፡ የዚህ አይነት መነጋገር ሳይሆን ለየብቻ መናገር ውጤቱ መደነቋቆር ነው፡፡ በደርግ ጊዜ ሲዳሞ በዘመቱት የእድገት በህብረት ዘማቾች ላይ በሬድዮ የተነገረው መግለጫ ከዚህ ጋር የሚሄድ ነው፡፡ “በጩኸት የፈረሰች አገር ብትኖር ኢያሪኮ ብቻ ናት“ ይላል የመግለጫው ርእስ፡፡ መልእክቱ በጩኸት አገር አትፈርስም ነው፡፡ አገር በጩኸት ልትፍርስ የምትችለው ጩሀቱ እንድ አይነት ሲሆን ሳይሆን የተለያየና
Full Website