የሚል ድንቅ  ሙዚቃ አላት። አቀንቃኟ በዚህ ሙዚቃ የምታነሳሳውና የምትወቅሰው በወቅቱ በሃገርዋ የነበረውን ፈላጭ ቆራጭ ሙሰኛ ወታደራዊ መንግስት ለመውቀስና

ሚያዝያ 30 በዋለው የአማራ ክልል ፍርድቤት ችሎት አቶ በረከት ስምኦንና የትግል ጓዳቸው አቶ ታደሰ ካሳን ( ጥንቅሹ ) የስድስትና የስምንት ዓመት እስራት እንደተወሰነባቸው ስሰማ እኔም እንደ ዘፋኝዋ ልቤ ደማ አመረረ። እነዚህ ሰዎች በሙስና የሚታሙ ሳይሆኑበድርቅናቸው፣ በታታሪነታቸው፣ ላመኑበት ዓላማ በፅናት በመታገላቸው የሚታወቁ እንደሆነ ብዙዎች ይመሰክሩላቸዋል። እንደሌሎቹ ሆዳም ባለስልጣናት በግላቸው ይሄ ነው የሚባል ሃብት ያልተገኘባቸው ናቸው። በአዲስ አበባና በየመጡበት ክልል ዋና ዋና ከተሞች መሬትወስደው የቸበቸቡ፣ ከነጋዴ ጋር ተመሳጥረው የሃገርን ሃብት የመዘበሩ፣ የሃገርን ምስጢር ለጠላት አሳልፈው ሰጥቷል ተብለው የሚጠረጠሩ ወዘተርፈ በስልጣን ላይ ሰልጣን ሲሰጣቸው እያየን ነው። ሰዎችን የገደሉና ያስገደሉ፣ መፈንቅለ መንግስት ያካሄዱ፣ ህዝብን ብሄር ለይተው የጨፈጨፉና ለመናገር የሚቀፍ ወንጀል የፈፀሙ ( ከተለያዩ የአቃቤ ሕግ ክሶችና የፍርድ ቤት ብይኖች እንደሰማነው ) በምህረት ሲለቀቁ ወይም ክሳቸው ሲቋረጥ ምነው የነበረከት ጉዳይ የተለየ ሆነ ብለን ብንጠይቅ መልሱ የታወቀ ነው። የታሰሩበትና የተንገላቱበት ምክንያት የግል ወይም የቡድን ቂምበቀል፣ የቆዬ የፖለቲካ ቁርሾ (ያውም የተሸናፊዎች ) ፣ የውጭ ሃይል ጫና እና የፖለቲካ የፍየል መባ (scapegoat) ከመሆን አይዘልም።

ክሳቸው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስልጣን ክልል የሚታይ በመሆኑ ጉዳያቸው በአዲስ አበባ ከተማ መታየት ሲቻልና  ሲገባ ባህርዳር መውሰድ የተፈለገበት ምክንያት በግብዝና ደካማ የአማራ ክልል የዘመኑ ባለስልጣናትና ተጽእኖ  ፈጣሪ አክቲቪስቶች ሆን ተብሎ በተቀየሰ ክፍት የቀድሞ አመራሮቻቸውን ለማንገላታት፣ በስሜት በሰከሩ ወጣቶች ለማዋረድ እንዲሁም የፈለጉትን ለማድረግ እንዲመቻቸው የተደረገ ወራዳ ሴራ ነው። ይህ የአሳሪዎቹ የሞራል ዝቅጠትና የስነልቦና በታችነት ያሳያል። ይህንን ጸያፍ ድርጊት ያከናወኑት ሰዎች ለመገመት አዳጋች አይሆንም። የተከሳሾቹ ጠበቃ ለቢቢሲ የዜና አውታር እንደተናገሩት በአግባቡ እንዳይከራከሩና ምስክር እንዳያቀርቡ ተደርጓል። በመጀመሪያዎቹ ወራት ችሎት ሲቀርቡ ሲደርስባቸው የነበረው ወከባ፣ ስድብ፣ ዛቻና እንግልት በወቅቱ በሚዲያ መዘገቡ ይታወሳል። ምንም እንኳ ስሜቱ እየበረደ ወደበኋላ ቀለል ማለቱ ቢታወቅም ድርጊቱ የወረደ ነው። የፌዴራሉ መንግስትና ባለስልጣናትም ለዚሁ አጸያፊ ድርጊት ተባባሪዎች ነበሩ። ምክንያቱም ማድረግ የነበረባቸውን ባለማድረጋቸው
Full Website