Back to Front Page
ጣረ ሞቱ ሲያንዣብብ

ጣረ ሞቱ ሲያንዣብብ

የጽንፈኛ አሃዱአውያን ቱልቱላዎች መንፈራገጥ ጀምሯል። መሳይ መኮነን በፊተውራሪነት ተሰልፏል

ገረመው በየነ

1-12-20

መሳይ መኮነን ማን ነው መሳይ መኮነን ግዜ የማይሽረው የጸረ ህዝብነት ታሪክ ተምሳሌት ነው።

ትላንትና የትግራይ ህዝብ በጎንደር እንዲጨፈጨፍ በውሳኔ ያነሳሳ፣ ቅማንቶች ሲጨፈጨፉ መዘገብን ኣሻፈረኝ ያለ፣ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን የእምነት ቦታቸውና ጥረው ግረው ያፈሩት ንብረታቸው ተቃጥሎ ግፈኞች ከበው ሲጨፍሩ አልዘግብም የሚል፣ የኦሮሞ� ህዝብ ኡኡታው በዓለም ህዝብ እንዳይሰማ ስልክና ኢንተርኔት ተቋርጦበት በድብቅ አዋጅ በኮማንድ ፖስት ሲጨፈጨፍ አልዘግብም የሚልና ወደ ትግራይ የሚወስደው መንገድ ለሁለት ዓመት ሲዘጋ እንዳልሰማ ፊቱን የሚያዞር፣ የህዝብ ዓይንና ጀሮ ነን እያለ የኢትዮጵያ ህዝብን በማታለል ገንዘብ በመሰብሰብ ላይ የተሰማራ የአሃዱአውያን ልሙጥ ባንዴራ ጎታቾች አውራና ፊተውራሪ በመሆን በጋዜጠኝነት ስም ኢሳት ከሚባል የዜና ተቋም ውስጥ የመሸገ ትላንትና የግንቦት ሰባት ዛሬ ደግሞ በግልጽ የኤዜማ በድብቅ ደግሞ የብልጽግና ካድሬ ነው። ለዚህ ምንም ማስረጃና ትንተና አያስፈልግም። በገዛ ራሱ በቪድዮ ያሰራጨውን ብቻ ደጋግሞ ማዳመጥ በቂ ነው። የዚህ ሰው ጸረ ህዝብ ተግባር በሙሉ መዘርዘር አስቸጋሪ ቢሆንም በቅርቡ አየር ላይ ያዋለውን ቪድዮ የቅርብ ግዜ ትዝታ በመሆኑና አገርን ከመበተን አንጻር ካለው አፍራሽ ሚና አንጻር በኢትዮጵያውያን በተገቢ መንገድ እንዲታወቅ እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ።

በመሳይ መኮነን ወደ ህዝብ የተበተነው ቪድዮ መሰረታዊ ይዘቶች የሚከተሉትን ያካትታል።

ሀ/ በህወሃት ላይ ያነጣጠረ መልእክቱ

� ህወሃት የጃጀ የገረጀፈ ትንፋሹ የሚቆራረጥበት በሞት ሰረገላ ላይ ሆኖ ወደ መቃብሩ የሚያዘግም ነው። ኣብቅቶለታል።

� የመስመር የኣላማ ዝባዝንኬ ልዩነት ምናባዊ ነገሮችን መጥቀስ ጅልነት ነው።

� የተዘረጋላቸውን የሰላም እጆች ወደ ጎን ገፍተዋል።

� የቁም ተስካር በሚመስል ህወሃት 4 ውሳኔዎችን ኣስተላልፏል።

1. ከብልጽግና ፓርቲ ጋር እንደማይዋሃድ

2. ከኢህኣዴግ ጋር ሆኖ ያፈራቸውን ሃብቶች ለመከፋፈል

3. ከፌደራል መንግስትጋር ስለሚኖረው ግኑኝነት

4. በቀጣይ ኣብሮ� ለመስራት የሚፈልጋቸው ሃይሎች እነማን እንደሆኑ ገልጿል ይልና እነዚህ ድልም ፍትህም ኣያነግሱለትም የመጨረሻ ኑዛዜ ናቸው ይላቸዋል።

ለ/ የብልጽግና ፓርቲ ታማኝ ተላላኪነቱንና የብሄር ብሄረሰቦች መብቶችን መደፍጠጥ የሚያሳይ መልእክቱ

� ህወሃት የብርሃኑን የብልጽግናውን መንገድ ትቶ ጨለማውንና የውድቀት መንገዱን� መርጧል።

� ከብልጽግና ጋር መፋታቱ ከሌሎች ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርገውን ያሳጣዋል

� የምር ዴሞክራሲና ፌደራሊዝምን እከተላለሁ ከሚለው ከብልጽግና ፓርቲ ጋብቻ� አልመሰርትም ማለቱ ግራ መጋባት ነው። የሚጠቀመው ከብልጽግና ጋር ሲሆን ነው ምክንያቱም ወደ ከርቸሌ ከመግባት ያድነዋል

ሐ/ እንደ ኮለኔል መንግስቱ ሃይለማርያም የትግራይ ህዝብን ማብጠልጠልና የፌደራል መንግስት በትግራይ ህዝብ ላይ ግፍ እንዲፈጽም የማነሳሳት መልእክቱ

� ህወሃት በቀጭን ትእዛዝ የትግራይ ምድር በኢንዱስትሪ እንዲሰምጥ አድርጓል

� በበጀትና በሌሎች በጥገኝነት ያለውን ክልል የሚያስተዳድር ፓርቲ እንዴት የንብረት ክፍፍል ይጠይቃል

� ትግራይ 85 ከመቶ� በጀቷ ከፌደራል መንግስት ነው ለማእከላዊ መንግስት የምታዋጣው ኢምንት ነው። ትግራይ የደም ስሩ የተገመደው ከማእካዊ የሃገሪቱ ክፍል ጋር ነው። በራሱ መቆም አይችልም። በሌላ ትከሻ ካልተንጠለጠለ በቀር ኣንድ ስንዝር ወደፊት ኣይንቀሳቀስም።

� ተጋዳላይ የሚል ቅስቀሳ አሁን የሚሰራ አይደለም

� ፌደራል መንግስት አያሌ አስገዳጅ አቅሞች አሉት

� ለጸጥያና ደህንነት የሚሰጠውን በጀት ብቻ በመቀነስ ሊያሽመደምደው ይችላል

� ልዩ ሃይልና የሚልሻ ሰራዊትን የማፍረስ ተግባር የፌደራል መንግስት የመጀመርያ እቅዱ ከመሆን አያልፍም

መ/ የ ህብረ ብሄራዊ ሃይሎችን እንደ ከፍተኛ ስጋት የሚመለከታቸው ስለመሆኑ የሚመለከት መልእክቱ

� ከሌሎች ፌደራል ሃይሎች ጋር ተደራጅቸ ብልጽግናን አጠፋለሁ የሚል ውሳኔው ቀቢጸ ተስፋ ነው

� ኣቶ በቀለ ገርባ ፍላጎት እንዳለው ምልክት ኣሳይቷል

ሰ/ ማጠንጠኛ ፍላጎቱ፣ ህልሙና ስጋቱ የሚያንጸባርቅ መልእክቱ

� ወደ ቀና መንገድ ተመለሱ ግዜው አልረፈደም የሚል ነው። ዝርዝሩን ለማዳመጥ የሚከተለውን ሊንክ ይክፈቱና ጉድ በይ አገሬ አመኬላ አበቀልሽ ይበሉ።

���������� https://youtube/kFHq7C7ozSc

Videos From Around The World

የመሳይ መኮነን አመለካከት እንደ ፊተውራሪነቱ አነሳሁ እንጂ ይህ አመለካከት የጸረ ሕገ መንግስቱ፣ የአሃዱአውያን፣ በስመ አንድነት የብሄር ብሄረሰቦችን ህልውናና ማንነት የማይቀበሉ፣ፌደደራሊዝሙን በጂኦግራፊ ገነጣጥለው ኢትዮጵያን ለመበታተን የሚዶልቱ በግልጽና በድብቅ የልሙጡ ባንዴራ ተሸካሚዎች አመለካከት ነው።

ይህን የመልስ ምት መልእክቴ በተላላኪው ካድሬአቸው በመሳይ መኮነን በኩል እንዲደርሳቸው ልኬዋለሁ ይከታተሉት። ይህ መልእክት የጻፍኩት የህወሃት ካድሬ ስለሆንኩ ወይንም ህወሃትን እንደጣኦት የማመልክ ስለሆንኩ አይደለም። በመሳይ መኮነን �የተነሳው ብትር በህወሃት አማካኝነት የኢትዮጵያ አስኳል አድርጌ ወደ እምመለከተው ወደ ትግራይ ህዝብ ያቀና መሆኑን ስለተገነዘብኩ፣ አገራችንን ለመበታተን የሚያጋልጥ አደጋ ስለሆነና የነመሳይ የብልጽግና ተላላኪነት መጋለጥ አለበት የሚል እምነት ስላደረብኝ ነው።

የእነ መሳይ ጣረ ሞት ምንድን ነው

ኢትዮጵያን የሚገነቡና የሚያጠናክሩ ሁሉም ብሄርና ብሄረሰብ ተሰባስበው ነው። እነዚህ ዜጎች በህገ መንግስት በመተማመን ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊዝምን ለመገንባት ቆርጠው የተነሱ ናቸው። እነዚህ ናቸው ለእነ መሳይ መኮነን ጣረ ሞት የሆኑባቸው። እነ መሳይ ብሄር ብሄረሰብ የሚሉ ቃላቶችንና ህብረ ብሄራዊ ስርዓትን እንደ ጣረ ሞት ይመለከቷቸዋል። ይህ የነ መሳይ ጣረ ሞት ደግሞ ክንዱን አፈርጥሞ ጉዞውን ጀምሯል። ፍጥነቱም እየጨመረ ስለሆነ መሳይና መሰሎቹ ደራሽ ውሃ ሆኖ እንዳይጠራርጋቸው ስጋት ላይ ወድቋል። ለዚህ ነው መሳይ በፊተውራሪነት የተነሳው። እነ መሳይ የሚፈልጉት በስመ አንድነት መደፍጠጥ ነው። ሩቅ ሳንጓዝ በአማራ ክልል ውስጥ እንዲተገበር እየተጉበት ያለውን እንመልከት። እንደ ማንኛውም ክልል በአማራ ክልል ውስጥም የተለያዩ ብሄረሰቦች ይኖራሉ። አማራ፣ አገው፣ቅማንት፣ኦሮሞ፣ ዓፋር፣ አርጎባ ወዘተ ብሄረሰቦች ከነዛ ውስጥ ናቸው። እነመሳይ እነዚህ ብሄረ ሰቦች የራሳቸው ቋንቋ ባህልና ነጻ ማንነት ያላቸው ህዝቦች መሆናቸውን መቀበል አይፈልጉም። ይልቁንስ አገው አማራ፣ ቅማንት አማራ፣ አርጎባ አማራ እያሉ ብግድ አማራ ናችሁ ይሏቸዋል። አገው አገው ነው� እንጂ አማራ ሊሆ ን አይችልም።ቅማንትም ቅማንት ነው እንጂ በምንም መመዘኛ በአማራ ክልል ስለተካለለ ብቻ አማራ ሊሆን አይችልም። ለምን በዚህ ማንነታቸው ኮርተው እንዲኖሩ እንደማይፈልጓቸው አንባብያን ልብ በሉ። አማራ ክልል ውስጥ የሚኖር ኦሮሞን ለምን ኦሮሞ አማራ አይሉትም አይቻልማ ኦሮሞ� ኦሮሞ ነው። እነመሳይ ይህን ሃቅ አፋቸውን በግድ ከፍተህ ልትግታቸው ካልሆነ በስተቀር ሊውጡት አይችሉም። እንኳንና በአንድ ክልል በአገቱ በሞላ ያሉትን� ኦሮሞ� ኢትዮጵያዊ፣ ትግራዋይ ኢትዮጵያዊ፣ ሶማልያ ኢትዮጵያዊ፣ ወላይታ ኢትዮጵያዊ፣ዓፋር ኢትዮጵያዊ ወሸተ ነኝ የሚሉትን ብሄር ብሄረሰቦች ማንነት የላችሁም ዝም ብላችሁ ኢትዮጵያውያን ነን በሉ እያሏቸው አይደል ��

የፊተውራሪ መሳይ መልእክቶችን አንድ በአንድ እንያቸው

ሀ/ መሳይ በህወሃት ላይ ያነጣጠረ መልእክት ምንድን ነው �

ህወሃትና እህት ድርጅቶቹ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የፈጸሟቸውን ጸረ ዴሞክራሲያዊ ተግባሮች፣ ራሳቸው ላጸደቁት ሕገ መንግስት ተገዥ አለመሆናቸው፣ በሙስና መጨማለቃቸው፣ የህግ የበላይነትን መጣሳቸው፣ ነጻና ገለልተኛ ተቋማት አለመገንባታቸው አምርረው ከሚቃወሟቸው ኢትዮጵያውያን አንዱ ነኝ። የአንበሳውን ድርሻ ደግሞ ህወሃት ቢሸከመው እስማማለሁ። ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ ድርጅቶች ኢትዮጵያን በድርብ አሃዝ እንድታድግ በማድረጋቸው፣ አባይን ደፍረው በመገደባቸው፣ በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን የአፍሪካ የሰላም አስከባሪ እንድትሆን ማድረጋቸው፣ የመገናኛ የህክምና የዩነቨርሲቲዎች ብዛት ኢትዮጵያን እንዲያጥለቀልቁ በማድረጋቸው አገር ወዳድ ጀግኖች ናቸው ከሚሉ ኢትዮጵያውያንም አንዱ ነው። አሁንም የነዚህ ድሎች የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው ህወሃት ነው ከሚሉ ዜጎች ጋር እስማማለሁ።

ዘመኑ የህዝቦችን ማንነት የማይቀበሉ፣ በስመ አንድነት የተለያየ ማንነት ያላቸውን ኢትዮጵያውያውያንን ለመደፍጠጥ የሚከጅሉ ጸረ ህገ መንግስትና ኢትዮጵያን በጂኦግራፊ በጣጥሰው አገር እንድትበተን የሚዳዱ፣ አገሪቷን አስኳል በመሆን ጠምሮ� ይዞ� የነበረውን የህብረ ብሄራዊ ሃይልን ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ እየተቀባበሉ በማምታት የኢትዮጵያ ህዝብን አደናግረው አስኳሉን ካዳከሙ በኋላ አገርን ወደ ገደል አፋፍ እየገፈተሩ ያሉ ልሙጥ ባንዴራ ተሸካሚዎች አንድ መዝሙር የሚዘምሩበት ዘመን ከሆነ ሁለተኛ ዓመታችን የምናስቆጥርበት ዘመን ሆኗል።

በሌላ በኩል ደግሞ በጉም መሃል ፈንጥቃ እንደምትወጣ ጸሃይ በጀግንነት በረጋግደው ብቅ ማለት የጀመሩ የህብረ ብሄራዊ ሃይሎች እየተሰባሰቡ መሆናቸውን በአይን በብሌናችን የምናይበት ዘመን ነው። ይህ ዘመን የህዝቦች ማንነት ለምንቀበልና በህብረ ብሄራዊ ፊደራሊዝም ለምናምን ታላቅ የምስራች ሆኗል። ለደፍጣጮች ግን ጣረ ሞት ነው። ይህ ጣረ ሞት በነዚህ ጸረ ህገ መንግስት ላይ እያንዣበበ ስለሆነ ደግሞ መንፈራገጡን ጀምረውታል። መንፈራገጡን በግምባር ቀደምትነት የጀመረውም ትላንትና የትግራይ ህዝብን ጨፍጭፉ ብሎ የጎንደር ህዝብን የቀሰቀሰና በቅርቡ ደግሞ የኦሮሞ ወጣት ጀግኖች ቄሮዎችን በመንጋነት የፈረጀው የኢሳቱ ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ነው።

መሳይ በህወሃት ላይ ያነጣጠረው ምን እያለ ነው ለምንስ ነው

የመሳይ አለቃ ኤዜማ ደጋግሞ ለብልጽግና ሮድ ማፕ የምንሰጠው እኛ ነን እያለ ሲነግረን ከርሟል። ኤዜማና ብልጽግና አንድም ሁለትም መሆናቸውም ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በቤተመንግስት ውስጥ የብልጽግና ፓርቲ ውይይት መሪ አድርጎ ብግልጽ አሳይቶናል። መሳይ የነዚህ ተስፈኛ ነው። ለዚህ ነው ዓይኑን በጨው አጥቦ የብልጽግና ጉዞ የሰላም፣ የብርሃንና የብልጽግና ጉዞ ነው� ህወሃት የብልጽግናን መንገድ ትቶ� ጨለማውን መንገድ እየመረጠ ነው እያለን ያለው። መሳይ መች ያፍርና ህወሃት እዚያ ከረጢት ውስጥ ካልገባ በቃ ሞተ ተናዘዘ እያለን ነው።

ለመሆኑ መሳይ የፖለቲካ ፓርቲ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያውቃል ብልጽግና ፓርቲኮ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ� ከ140 ከሚጠጉ ፓርቲዎች አንዱ ነው። የመንግስት መዋቅር አይደለም። የሚስማሙ ፓርቲዎች አንድ ላይ እንሰራለን ሲሉ የማይስማሙ ደግሞ ለብቻቸው ከሚመስላቸው ጋር ይሰባሰባሉ። ለምሳሌ የልሙጡ ባንዴራ� አምላኪዎች አንድ ላይ ሲሰባሰቡ የህብረ ብሄራውነት ፍቅር ያላቸው ደግሞ ለብቻቸው እየተደራጁ ነው።� ህወሃት የብልጽግና ፓርቲ አይስማማኝም፣ አሃዱአዊ አመለካከት አለው፣ ህጋዊ አይደለም፣ የአገር ክብር አሳልፎ� የሚሰጥ ነው፣ ኢትዮጵያን ሰላምና መረጋጋት አሳጥቶ እየበተናት ነው፣በትግራይ ህዝብ ላይ ግፍ እያስፈጸመ ነው፣ ፓርላማ ባልወሰነው ግዚያዊ የአስቸኳይ ግዚያዊ አዋጅ በድብቅ አውጆ ኡኡታው የዓለም ህዝብ እንዳይሰማው ስልክና ኤንቱርኔት አስዘግቶ የኦሮሞ ህዝብን በኮማንድ ፖስት አሳር መከራውን እያሳየው ነው፣ የቅማንት ህዝብ ሲጨፈጨፍ ትንፍሽ አላለም፣ መስጊዶች ሲቃጠሉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ወገኖቻችን ንብረት እየተቃጠለ እንዳላየ ከሚያልፈው፣ ሚልዮኖችን ለመፈናቀል የዳረገ ሰላም የራቃት አገር እንድትሆን ካደረገ ከብልጽግና ጋር አልሰለፍም ስላለ ህወሃት በቃ አበቃለት ወደ መቃብር እየወረደ ነው ካርቸሌ ትገባለህ እያለ ይህን ሁሉ መዓት የሚወርድበት የኢትዮጵያ አንድነት አሳስቦት ነው ወይስ የሚሰጠው ኮምሽን እንዳያጣ ፓርቲዎች ከተስማሙ ለራሳቸው ነው። ካልተስማሙም ለራሳቸው እኮ ነው። በመንግስት ጉዳይ ላይ ግን የአገር ጉዳይ ስለሆነ ሁሉም በጋራ መሰለፍ ይጠበቅባቸዋል። ህወሃትም ግንኙነታችን ብህገ መንግስቱ ብቻ ይሆናል ብሎ በግልጽ አስቀምጧል። ይህ አልገባ ብሎት ነው ጃል እንዲህ እንዲንፈራገጥ ያደረገው መድረክና ኦነግስ ከብልጽግና ጋር መች አበሩና ታድያ እነሱ ላይ እንደዛ ያላላዘነው ከመሃይምነት ውጭ ምን ሊሆን ይችላል ለዚህ ነው ጉድ በይ አገሬ አመኬላዎችን አብቅለሻል የምንለው።� መሳይ ዓላማችን የየቅል ነው አብረን እንድንሰለፍ አያደርገንም ያለ ፓርቲ ጠላት ነው አይባልም። ይህ የፖለቲካ ሃሁ ነው። እሺ ይህን ይዘህ ወደ ህዝብ መቅረብህ ኢሳትን፣ ኤዜማንና ብልጽግናን አስገመትካቸው። እንዳልከውስ ብልጽግና እውነት የሰላምና የእድገት ጉዞ� ነው በዚህ ጉዳይ ግዜ አላባክንም። የተፈናቀለው ገበሬ፣ እየሞተና እየቆሰለ ያለው የዩነቨርሲቲ ተማሪ፣ እየተዘረፈ ያለው የአዲስ አበባ ህዝብ፣ ብኑሮ ውድነትና በስራ አጥነት እየተሰቃየ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ መልሱን ይስጥህ ታድያ ህወሃት ወደዚህ ካልገባህ አበቃልህ ሞትክ ይባላል ???

ለ/ መሳይ እንደ አያቶቹ እንደነ ኮለኔል መንግስቱ ሃይለማርያም የትግራይ ህዝብን ማብጠልጠልና የፌደራል መንግስት በትግራይ ህዝብ ላይ ግፍ እንዲፈጽም የማነሳሳት ስራውን ብግልጽ እያጧጧፈ ነው።

ትግራይ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ሃብትና በቱሪስት መዳረሻነቷ በልጆቿ ጀግንነትና ታታሪነት ለአገሪቱ ኤኮኖሚ ምን አስተዋጽኦ እያደረገች እንዳለች ባለሞያዎች ሊተነትኑት እተወዋለሁ። የትግራይ ትልቁ ሃብቷ የሰለጠነ ባህልና ታሪክ ያለው ህዝቧ በዋናነት ሲጠቀስ ትላንትና ድንጋይ ሲባል የነበረ ከርሰ ምድሯ የውድ ማእድናት ሃብት ሆኖ� መገኘቱ ደግሞ ለነገይቱ ኢትዮጵያ ተስፋ ከመሆኑም በላይ ትግራይ እንደ ሌሎች ክልሎች ለአገሪቱ ኤኮኖሚ የድርሻዋን በማዋጣት ኢትዮጵያ ቆማ እንድትሃድ እያደረጉ ካሉ ክልሎች አንዷ ነች። ዓመታዊ የግብር አሰባሰብ ሰንጠረዥ መመልከት በቂ ነው።

ይህ እንዳለ ቢሆንም ግን ትላንትና አያቶቹ እነመንግስቱ ትግራይ ለጠመኔ መግዣም አስተዋጽኦ የማታደርግ ደሃ ተመጽዋች ክልል ነች ሲሏት ከርመው በትግራዮቹ ወደ መቃብር ወርዷል። አሁን ደግሞ አንድ አይነት ታሪክ ብልጆቻቸው በእነ መሳይ ታድሷል። መሳይ የትግራይ ምድር በቀጭን ትእዛዝ በኢንዱስትሪ እንዲሰምጥ ተደጓል፣ ትግራይ በበጀትና በሌሎች በጥገኝነት ያለ ክልል ነው። 85 ከመቶ� በጀቷ ከፌደራል መንግስት ነው የሚሸፈነው። ለፌደራል መንግስት የምታዋጣው ኢምንት ነው። ትግራይ በራሱ መቆም አይችልም። በሌላ ትከሻ ካልተንጠለጠለ በቀር ኣንድ ስንዝር ወደፊት ኣይንቀሳቀስም። ብሎ በድፍረት ትግራይን አብጠልጥሏል።

የጥላቻው ጥግ ሲገልጽ ደግሞ ፌደራል መንግስት አያሌ አስገዳጅ አቅሞች አሉት። ለጸጥያና ደህንነት የሚሰጠውን በጀት ብቻ በመቀነስ ትግራይን ሊያሽመደምደው ይችላል። ይልና የፌደራሉ መንግስት በትግራይ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ የትግራይን ልዩ ሃይልና የሚልሻ ሰራዊትን እንዲያፈርስ ከፍተኛ ቅስቀሳ በማድረግ የትግራይ ህዝብን በጦርነት ውስጥ ለማስገባት እየሰራ ነው። ትግራይ ውስጥ ጦርነት ተነሳ ማለት በመላ ኢትዮጵያ ሰላም የሚባል ነገር ለሽታም እንደማይገኝ እያወቀ ይህን ቅስቀሳ ማካሄዱ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ምን ያህል ቆርጦ እንደተነሳ በግልጽ አሳይቷል። ይህ ደግሞ ዓለማቸው ሆዳቸው ብቻ የሆኑ ሰዎች ሲያደርጉት በታሪካችን ደጋግመን አይተናል። ታሪካችን ያሳየን ይህ ብቻ� አይደለም። እነዚህ አይነት ሆዳሞች መጨረሻቸው ምን እንደሆነም አሳይቶናል። የአገራችን የጸጥታና የአንድነት ችግር በሰላምና በዴሞክራስያዊ መንገድ ብቻ እንጂ በሃይል፣ በአስተዳደራዊ መንገድና ትጥቅ በማስፈታት በምንም አይነት መንገድ አይታለምም። ሲጀመር ትጥቅ የሚፈታ ይኖራል ብሎ ማሰቡ ጅልነት ነው። በሃይል ለማስፈታት መሳይ እየሰጠው ያለውን ምክር የሚቀበል የመንግስት ባለስልጣን ካለ ደግሞ ይህን ምክረ ሃሳብ ለማስፈጸም ሃላፊነትና ሹመት ለደሃው የገበሬው ልጅ ሳይሆን ለመሳይ እንዲሰጠው አበክሬ እጠይቃለሁ።

ሐ/ መሳይ መኮነን የህብረ ብሄራዊ ፌደራላዊ ሃይሎችን እንደ ከፍተኛ ስጋትና ጣረ ሞት ይመለከታቸዋል። ፌደራል ሃይሎች የብሄርና ብሄረ ሰቦችን ማንነት ይቀበላሉ። ህገ መንግስቱንና በህገ መንግስቱ የጸደቀውን ባንዴራን ያከብራሉ። የሃይማኖት እኩልነትን ይቀበላሉ። ይህ አመለካከት ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች ይቀበሉታል። ለእነ መሳይ የሞት ሞት ነው። እንዳይፈጸምና ወሬው እንዳይሰማ ለማዳፈንና ሌላ ቀለም ለመቀባት እየተራወጡ ነው። እዚህ ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንክሮ መከታተልና የልሙጥ ባንዲራ አምላኪዎችንና በዓላማ ከነዚህ የማይለየውን ብልጽግና ፓርቲን በካርዳችሁ ለመቅጣት መዘጋጀት ያስፈልገዋል።

መ/ የመሳይ ፍላጎት፣ ህልምና ስጋቱ ምንድን ነው

መሳይ ወደ ቀና መንገድ ተመለሱ ግዜው አልረፈደም በሚል ማማለያ ሃሳቡን አጠቃሏል። እሱ ቀና መንገድ የሚለው ደግሞ� የብልጽግና መንገድ ነው። ኤዜማን ለምን እንደማያነሳው እንኳን ብዙ ሰው ገርሞታል። ደሮ ብታልም ጥሬዋን አሉ የተለያየ ዓላማ፣ ታክቲክና ስትራተጂ የሚከተሉ ለስልጣን የሚወዳደሩ ፓርቲዎች ግዜው አላለፈም አንድ ላይ ሁኑ ለዛውም ሮድ ማፕ ከሌለው ከብልጽግና ጋር ብሎ ልመና ምን ይባላል እነዚህ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሆነው ለህዝብ ፍርድ ቢቀርቡ ችግሩ ምንድን ነው ይህ ጥያቄስ ለምንድን ነው ለሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሳይቀርብ ለህወሃት ብቻ የሚቀርበው ፓርቲዎች የተለያየ አቋም መያዛቸው ጠላቶች ሆኗል ማለት ኣይደለም። ተፎካካሪዎች ናቸው። በለስ ከቀናቸው ደግሞ የመረጡትን ዓላማ ይዘው የመንግስትን ስልጣን ለመቆጣጠር ይታገላሉ። ኣሁን ጎ ራው ተለይቷል። የጠራውን ጎራ አትደበላልቅብን። ትላንትና አብራችሁ ስለነበራችሁ ከሚል ገራገርነት የሚነሳ ከሆነ ግን መሳይ ስለፓለቲካ ትንሽ ትምህርት ብትወስድ እመክራለሁ።�

ፌደራሊስቶች ወደ ኋላ በማይመለሱበት መድረክ ላይ ደርሷል። ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊስቶች በተጠናከሩ ቁጥር ጣረ ሞቱ በልሙጥ ባንዴራ ጎታቾች አናት ላይ በከፍተኛ ፍጥነት ያንዣብብና የነሱን አመለካከት ጠራርጎ ወደ እማይመለስበት መቃብር ይሸኘዋል። እኛ ደግሞ በሙዚቃ ንግስቷ በሰላማዊት ዮሃንስ የተዘፈነውን � እምበር ተጋዳላይ � በሚለው የጀግኖች የዘመናት ዘፈን እንሸኛቸዋለን። አንባብያን ይህን ዘፈን አብራችሁ እየዘፈናችሁ የእነዚህ አመኬላዎ አመለካከትን እንድትሸኙልኝ የዘፈኑን ሊንክ ከስር አስቀምጨላችሁ አለሁ።

[ለእነሱ እንኳን ሙሾ ነው]

https://youtube/4EMBciEnfYE

ቸር ይግጠመን

Back to Front Page
Full Website