የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉጥንቅጥ ዉስጥ ገብቷል፡፡ አሁን የተቀመጠው ፓርላማ እድሜው አብቅቷል። ሲጀምር ህዝባዊ ቅቡልነት ሳያግኝ፤ በጉልቤ መቶ ፐርሰንት የውክልና ወንበር ዘርፎ፤ አገሪቷን ለቀውስ ዳርጋት። ኢህአዴግ መራሹ የሚፈረከርክበት ወቅት ሲደርስ አቢይ አህመድ በአቋራጭ ፊጢጥ አሉ። ግድየለም ሁለት አመት ሩቅ አይደለም እንታገሰው ይህ ሰው ወደ በጎ ዘመን ያሸጋግረን ይሆናል ተብለው በተስፋ ሲጠበቁ፤ ንጉስ ነኝ ብለው አረፉት። አንድ አመት ተኩል አገር በግርግር፤ በህዝብ እልቂትና መፈናቀል፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ደግሞ በዙረት፤ በፎቶ መነሳት፤ በውዳሴ ከንቱ ባከነ። የተፈናጠጡብትን የኢህአዴግ ፈረስ ውጉዝ ከም አርዮስ አስብለው በብጥነት ብልፅግና ፓርቲ ብለው መጡ ( molded and influenced by ideologues of the Southern United States Property Gospel) ። የኢህአዴግ በቢልዮኖች የሚቆጠር ንብረት ፤ አውታር አይቀር ሚልዮኖች ያሉበት አባልነት ወርሶ በልበ ሙሉነትና በእርግጠኝነት ጉዞ የጀመረው ብልፅግና፤ ገና ድክድክ ሳይል፤ ፍርሃት ያዘው፤ ዳገት ሳይወጣ ብርክ ብርክ አለው። እናም አቋራጭ ፈለገ፤ ምርጫውን ቢቻል በወረርሽኝ በሽታ ሳይሆን በሕገ - መንግስት ትርጉም ሰብብ አስባብ የስልጣን እድሜን ማራዝም። ኢህአዴግን ነቃቅየ ጥያሎህ ያለው ቡድን የለም የኢህአዴግ ሪፎርም ቀለም የተቀባሁ ወራሽ ነኝ ይላልበደርቁ ላጨኝ ነው ነገሩ ። ተቀናቃኞች የለም ቀልድህን አቁም፤ የባከነው ሁለት ዓመት ይቆጫል እያሉ ነው። ምርጫው በህግ በተደነገግው የፓርላማ እድሜ ማገባደጃ ይከናወን፤ ይህ ባይሆን የተቀናቃኝ ፍቃድ ያገኘ ስልጣኑ የተገደበ ባለአደራ አስተዳደር መንግስት ይረከብ፤ወይም እኛን የሚጨምር የሽግግር መንግስት ይቋቋም እያሉ ነው። ይህ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እሳቸው ላይ የተቃጣ የስልጣን ሽሚያ አርገው ወስደውታል። ጠቅላዩ ምኞታቸው የሚኮላሽ ቢመስላቸው፤ በንዴት አካኪ ዘራፍ እያሉ ነው፤ ህፃናት ያልቃሉ ፤እናቶች ያለቅሳሉ ብለው ይዝታሉ። የመንግስት አውታር ላይ ጉብ ያሉት፤ ለጊዜውም ቢሆን ፤ የፀጥታና የመከላከያ ኀይሉን የተቆጣጣሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ ናቸው። ይኼን ኃይል በመጠቀምም የስልጣን እድሜ ማራዘም ፤ ውሳኔቸውን ያልተቀበሉት፤ አለፎም የተፃረሩት ላይ ወታደራዊ ኃይል እንደሚጠቀሙ እየዛቱ ነው። አይዞህ ባይም አላጡም። ተቀናቃኞቻቸዉ ዛቻው ይቆይ፤ አያዛልቅም፤ አይበጅም እንደራደር እያሉ ሲሆን ከክልሎችም የትግራይ መንግስት ድርድር አጠላም፤ ምርጫውን ግን የፌደራል ፍቃድና ሰሌዳ አልጠብቅም፤ በክልሉ ህግ መሰረት አከናዉናሎህ እያለ ነው ( ለማስፈራራት ይሁን የምር የሚታይ ይሆናል ) ፡፡ በዚህም ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ፍጥጫ ተፈጥሯል፡፡ የአቢይ አህመድ ዛቻ ተክትሎ ( ሶሻል ሚዲያና አጫፋሪዎች እያራገቡት ) ፤ ህዝብ የጦርነት ስጋት ገብቶታል። አገር ያረጋጋሉ የተባሉት፤ አገሪቷን አምሰዋታል።

Full Website