ሟች ከመሞቱ በፊት

ግደይ ረዳ 05-25-20

መንግስት እንደ መንግስት የውድቀቱ ግዜ እየተቃረበ ሲሄድ የሚወስዳቸው እርምጃዎች በእቅድ ላይ ያልተመሰረቱ፡ መውጫ እና መግብያ ያልተበጀላቸው፡ ምን ጉዳት ምን ጥቅም ያመጣሉ ተብለው ውይይት ያልተደረገላቸው እና ለራሱም ውድቀት የሚያቀላጥፉ ናቸው፡፡

ይህም ለማየት ሩቅ መሄድ ሳያሰኬደን በደርግ ግዜ የመጨረሻው የእድሜ ዘመን ሲያከናውናቸው የነበሩ ተግባራት መጥቀስ በቂ ነው፡፡ ደርግ ሰራዊት ሲመለምል በገፈፋ መሆኑ የተለመደ ነው፡፡ ደርግ ሲፈጠር የመሰብሰብ፡ ሰላማዊ ሰልፍ የማድርግ፡ የመፃፍ እና የመናገር መብቶች በህግ እና በኣዋጅ የከለከለ ስርአት መሆኑ የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው፡፡ ደርግ አንድ ትውልድ ወጣት በቀይ ሽብር እና በነጭ ሽብር የጨረሸ ስርአት ነው፡፡

Videos From Around The World

በመጨረሻ  የጣረ ሞቱ አመታት ግን ተጨማሪ የውሸት እና አልቧልታ ዘመቻዎች ነበሩት፡፡ ድል ሳያስመዘግብ ድል አስመዘገብኩኝ፡ ስንዝር ሳይራመድ እገሌ የሚባል ቦታ ተቆጣጠርኩኝ እና ለራሱ ተደምስሶ ደመሰስኩኝ በማለት የዘወትር ጀሮአችንን ያደነቆሩ ዜናዎች ነበሩት፡፡ ደረግ ወያኔ አንድ ጀሮዋ ምንጣፏ አንድ ጀሮዋ ልብሷ እንደሆነ ለሰራዊቱ ይቀሰቅስበት ነበር፡፡ ብዙ የተማረኩ ወታደሮች ግራ ይጋቡ ነበር፡፡ “ወያኔ ስልቻው ይዞ ሊወራቹህ እየመጣ ነው” ብሎ ህዝቡን ይቀሰቅስ ስለነበር ህዝቡም ለወያኔ “መቼ ነው እንዴ የምትዘርፉን” በሎ እሰከ መጠየቅ ይደረስ ነበር፡፡

ከሀሉም በላይ ደግሞ የሁለት የህወሀት የነበሩ ታጋዮች ቃለ- መጠየቅ አስገራሚ ነበር፡፡ ሁለቱም ከህወህት ሰራዊት ከድተው ሱዳን የገቡ ነበር፡፡ ደርግም እንደምንም አድርጎ አዲስ አበባ ያመጣቸው እና በሬድዮ እና (በቴሌቪዥንም ይመስለኛል) የህዝቡን ጀሮ ያደነቁሩት ነበር፡፡ አቶ እብራሃም ያዬ እና አቦይ ገብረ መድህን ይባላሉ፡፡ የማይዋሹት ነገር የለም፡፡ ይዋሹ ይዋሹ እና የህወህት አመራሮች ምቾት ሊነግሩን ይዳዳሉ፡፡ የህወህት አመራሮች የአውሮፓ እና የአመሪካ ንሮ እንደሚኖሩ አስምስለው በመሳል ይነግሩናል፡፡ ምን ግዳቹህ የህውህት ሰራዊት ምንም ዋጋ እንደ ሌለው፡ ተገዶ ከኋላ እና ከፊት መትርየስ ተደግኖበት እንደሚዋጋ፡ የመዋጋት አቅም እንደሌለው፡ ህወህት ህዝቡ እንደሚዘርፍ፡ እንደሚገድል፡ እንዲሁም ምንም ከሰው ፍጡር ይወጣሉ የማትላቸው የውሸት ትንታኔዎች እየሰጡ ለጀሮ የሚሰቀጥጥ ውሸት ይነግሩን ነበር፡፡

ይህን ሁሉ ግን ለደርግ እንኳን ከውድቀቱ ሊያድነው ጭራሽ ወድቀቱ እያፋጠነው ሄደ፡፡ ህወህት ትግራይ ነፃ ለማውጣት 15 ዓመት ሲፈጅባት ሌሎች የኢትዮጵያ ክፈለ ሀገራት ነፃ ለማውጣት ግን የፈጃት ግዜ ሁለት አመት ብቻ ነበር፡፡ ነሓሴ መጨረሻ 1981 ዓም ማይጨው ላይ  የተጀመረው ወግያ ግንቦት 20/1983 ዓም ተጠናቀቀ፡፡

የብልዕግና መንግስታች እንድምታዎች የሚያሳዩት የውድቀቱ ግዜ ማመላከቻ እንጂ ጥንካሬው አይደለም፡፡ ብልፅግና ሲጀመር ከኢህአዲግ በሰላማዊ ሽግግር ስልጣን የተበረከተለት ለውጭ ሀይል ሲያገለግል የነበረ ቡድን ነው፡፡ ሲጀምር በውሸት ሲቀጥል በማጭበርበር እየኖረ ያለ ድርጅት ነው፡፡ እስቲ በዚህ መንግስት የተዋሹ እና ያጋጠሙ ክስተቶች ለማሳያ ያህል ልበል

1. በሶስት ወር ውስጥ ነዳጅ አወጣህ ብሎ ህዝቡን ያሰጨፈረ፡ ያጭበረበረ

2. ዶላር ይንበሸበሻል በማለት የዋሸ

3. ሼክ አላህሙዲን አስፈትቶ ከሳምንት በኋላ አዲስ አበባ ይገባል በማላት የዋሸን

4. የአባይ ገደብ ለፖለቲካ ፍጆታ አንጂ በ10 አመት አያልቅም በማለት ህዝቡን ያታለለ

5. የአባይ ግድብ አሻግሮ ለድርድር ያቀረበ፡ ከግብፅ ጋራ ወላሂ ወላሂ ብሎ የማለ

6. ኢትዮጵያ ባለፉት 27 አመታት በጨለማ ዘመን እንደነበረች አድረጎ ያወጀ

7. አዋቂ መስሎ ጀነራሎች ለማሰተማር የሞከረ አጭበርባሪ

8. መደመር የሚባል ፍልስፍና ሊሆን ቀርቶ የግምገማ ሪፖርትም ሊሆን የማይቸል መፅሀፍ ፅፎ በህዝብ ገንዘብ በቀጥታ ስርጭት ያስመረቀ የመጀመርያው መሪ

9. በሁሉም ሚድያዎች በቀጥታም ጭምር ተጠርጣሪ እንደ ወንጀለኛ አድርጎ በመያዝ በቢልየኖች ከሶ ሚልዮን ማስረጃ ያላገኘ

10. በሁሉም ሚድያዎቹ ትግሬዎች አሳሪ ግራፊ እና ጨፍጫፊዎች እሰከ በሽጉጥ የሚላጩ አድርጎ ያስተላለፈ፡ የተግራይ ህዝብ እንዲጠላ ያደረገ

11. ጀነራሎች እና የከልል ባለ ስልጣናት ያስገደለ

12. ኢነጅነር ስመኘው በጠራራ ፀሃይ ያስገደለ፤ እሱ ግን የጓደኛው ልደት በማክበር የነበረ፡

13. ሶሰት ሚልዮን ህዝበ ያፈናቀለ

14. 86 ሰው በሳምንት የጨፈጨፈ፡ የሞቱት በብሄር ለመከፋፈል የሞከረ

15. በእሱ ግዜ ሰላም ታጥቶ፡ ሰው ተዘቅዝቆ የታረደበት ዘመን መሆኑ ያልገባው

16. ሁለት አመት ሙሉ የአንድ ክልል መንገድ ተዘግቶ ለማሰከፈት እንኳ ያልሞከረ

17. የወለጋ ህዘብ በሄሊኮፕተር በመደብደብ ህዝብ የገደለ፡ ነገር ግን መደብደቡን እንኳ የካደ

18. ኮቪድ 19 ለፖለቲካ ትርፍ ለማዋል

a. ገና ቫይረሱ እንኳ በአግባቡ ሳይታወቅ መድሃኒት ማግኘቱ  ያወጀ

b. ለምርጫ መራዘምያ የተጠቀመበት አሁን ምን አዲስ ነገር ተከሰተ?

ሰሙኑ ደግሞ የአብይ መንግሰት የተቀናጀ እና በገንዘብ የተደራጀ፡ ሁሉም ሚድያዎቹ እና አክቲቪስቶቹ የተሳተፉበት በትግራይ ህዝበ እና በህወህት ዘመቻ ከፍተዋል፡፡ ይህ ሲያደርጉ ደግሞ ትንንትና እላይ የተዘረዘሩት ግፎች ጨምሮ  ከጎነደር የተፈናቀሉ፡ ንበረታቸው የተቃጠለ እና የተዘረፈ፡ የተገደሉ አና የተሰቃዩ፡ በዬኒቨርሲቲው ሲገደሉ የነበሩ ትግሬዎች  ምንም ሳይሉ ለዛሬ ደርሰው ለትግራይ ሀዝብ አሳቢ በመምሰል በቀጥታም በተዘዋዋሪም ዘመቻ ከፍተዋል፡፡ ይህ ዘመቻ የተከፈተው በምናውቃት ሰላማዊትዋ ትግራይ ነው፡፡

ሲሆን ሲሆን ሁሉም ክልሎች እንደ ትግራይ ሰላማቸው ጠብቀው እንዲሄዱ መስራት በጣም ጥሩ ነበር፡፡ የትግራይ ተሞክሮ ለሁሉም ማዳረስ ከአንድ ቀና ድርጅት የሚጠበቅ ተግባር ነበር፡፡ ነገር ግን ሰላም የሚስፈራው የአብይ መንገስት የውሸት ተንታኞች እና ረጪዎች በማሰማራት በሁሉም ሚድያዎቹ የቻለውን ሁሉ እያደረገ ነው፡፡ ግን ለምን? ምክንያቶቹ ግልፅ ናቸው፡፡

1. ይህ ሀይል መጀመርያውም ኢህዲግ መስሎ ኢህዲግ የጣለ ሀይል ነው፡፡ ኢህዲግ ሲጥል ደግሞ ዋናው የስበት ማእከል አድርጎ የወሰደው ሀይል ወያኔ ነው፡፡ እንደ ጠላት ትክከል ነበር፡፡ አሁንም የተከተለው እሱ ነው፡፡ ይህ ሀይል የትግራይ ሰላም መሆን እንደ ስጋት የሆነበት ዋና ምክንያት ህወህት ወያኔ ለስልጣኔ ትልቅ ስጋት ይሆንብኛል በማለት ነው፡፡ አጭበርባሪነቱ፡ ለሀገር የሚያሳድግ ስትራተጂ እና እቅድ አቅምም ብቃትም እንደ ሌለው ራሱም ያውቃል፡ ነገር ግን ይህን ለህዙቡ በማሳጣት ሊሰራ የሚቸል ሃይል ወያኔ ነው ብሎ ያምናል፡፡  በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የስልጣኑ ዋና ተግዳሮት ህወህት መሆኑ ተረድተዋል፡፡

2. ብልፅግና ከኦሮም ህዝብ፡ ከአማራ ህዘብ፡ ከሶማሌ ህዝብ፡ ከትግራይ ህዘብ፡ ከደቡብም ይሁን ቤንሻንጉል እንደ ተተፋ ተረድተዋል፡፡ ስለዚህ መሸሸግያ ይፈልጋል፡፡

3. ሊወጣቸው ያልቻለው ተግዳረቶች ገጥመውታል፡፡ የለውጥ ሃይል በሎ እንኳን ለውጥ ሊያመጣ አገሪቷ በመነበረችበት ፍጥነት ሊያሰኬድ አልቻለም፡፡ ኢኮኖሚ ተዳክመዋል፡፡ የዋጋ ንረቱ ሰማይ አርገዋል፡፡ የውጭ ምንዛሪው ንረዋል፡፡ ስለዚህ በህወህት በመዝመት መሸሸግ ይፈልጋል፡፡

መጨረሻውስ?

መጨረሻው ምን እንደሚሆን የተለየ መላምት ወይም ትንተና የሚያሰፈለገው አይደለም ፡፡ የፈለገው ሚድያ ይኑሮው፡ የፈለገው መድፍ ይታጠቅ ሚሳይል የአብይ መንግስት እንኳን በማጭበርበር ከዚህ በኋላ ወደ መልአክ ሁኖ ቢመጣም  የሚያመነው፡ የሚደገፈው ይሁን የሚያዘንለት ኑሮ በስልጣን የሚቆይበት እድሜ የለውም፡፡ እዋጋሎህ ቢል የሚዋጋለት ሰራዊት የለውም፡፡ ተዋጋ ቢባል  እንኳ 20 አመት የሚያውቀው፡ አብሮ የበላ የጠጣ፡ ከባሀሉ ይሁን ከልምዱ የተጋመደ የትግራይ  ሀዘብ አንኳን ሊወጋ ዱላወም አያወጣውጥለትም፡፡  ባያወቀውም እነኳ የህዘብ እሴት የሚያከበር ህዝባዊ ሰራዊት ነው፡፡ እሺ ሰራዊቱ ለመዋጋት ፍቃደኛ ቢሆን  እና በትግራይ ህዘብ አና በህወህት ውግያ ቢከፍት እነኳ የኣበይ መንገስትም ይጠፋል፡ ኢተዮጵያማ ትበታተናለች፡፡

Full Website