05-17-20

ቱ ዓመታት ኢትዮጵያ በአንድ ጊዜ ወደ ሁሉም አቅጣጫ ለመጓዝ የሞከረችበት መደመር የተሰኘ የመደናበር ረዥም ዘመን ነበር። ቀጣዮቹ አሁን ስልጣን ላይ ያሉት ሰዎችና ቡድኖች ኢህአዴግን በጦርነት አሸንፈውና ደምስሰው መምጣት የነበረባቸው ይመስላል። ምክንያቱም ምናቸውም ኢህአዴግ አይመስልም። በጦርነት አለመምጣታቸው ነው እንጂ ኢህአዴግንም አፍርሰውታል። ማፍረስ ከመደምሰስ በምን ያህል እንደሚለይ አላውቅም። ይህን የአመራር ቡድን የሚገልጸው አንድ ቃል ካለ አፍቅሮተ ስልጣን ነው። እዛ ቤት ስልጣን የላቀ ዓላማ ለማስፈጸም የሚፈለግ ሁኔታ ሳይሆን በራሱ የመጨረሻ ግብ ነው። ለዚያ ሲባል ህግ መጣስ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ይጣሳል። ተቋማትና ሹመቶች መሰረዝ፣ መደለዝ፣ መበወዝ ከጠየቀም እንዲሁ። ኢህአዴግን ማወደስ፣ ኢህአዴግን ማውገዝ፣ ሁለቱም እያቀያየሩ መጠቀም ምንም ነውር የለውም። አመራሩ ኢህአዴግን መሆን ችሏል፣ ኢህአዴግንም መግደል ችሏል። ስለዚህ “የሽግግር መንግስት ይቋቋም” የሚሉትን ዝም ለማሰኘት “እኛ ሪፎርም እንጂ አብዮት አላመጣንም” ሲሉ የኢህአዴግ አስተሳሰብና ሌጋሲ ወረሾችን ዝም ለማሰኘት ሲፈለግ ደግሞ “በናንተ ስርአት ጊዜ፣ የጨለማው ጊዜ፣ የመንግስት አሸባሪነት ጊዜ፣ የጥፍር ነቀላ ጊዜ…” እያሉ ይገልጹታል። በአገራችን በዚህ ፋርሳዊ ትእይንት የማይጠገኑ ስንጥቃቶች እተፈጠሩና እየሰፉ መሄዳቸው እርግጥ ነው። አገር የሚፈርሰው መጀመሪያ የዜጎች ጭንቅላት ላይ ነው። ከዚያም ጠላት ከግራም ከቀኝም ስንጥቆቹን በማስፋትና በመቦርቦር ላይ ይዘምትበታል። ለወትሮው ይህን መከላከል ማየትና መከላከል የሚችሉት አገር ወዳድ ምሁራንና አርበኛ ልሂቃን ነበሩ። አሁን የት እንዳሉ ኣይታወቅም። የዋልያ ዝርያን ቀድመው ከምድረ ገጽ ጠፍተውም ከሆነ የነገረን የለም። ለምሳሌ ዛሬ ስለ ህገመንግስታዊ ትርጉም ሞያዊ አስተያየት እንዲሰጡ የተጠየቁት የህግ ምሁራን ያሳዩን ቁምነገር የፋርሱና ትራጀዲው ትእይንት አካል መሆናቸውን ነው። የኮቪድ ወረረሽን በምርጫ ወቅት ተከስቶ መደበኛውን የምርጫ ሥራ ስላስተጓጎለ እና መቀየር የነበረበት መንግስት መቆየት ስላለበት ለዚህ ሲባል ህገመንግስቱን መተርጎም የተሻለ መፍትሄ ነው ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል። በኋላ ስንሰማ እነዚህ ሰዎች ነበረ አራቱን አማራጮች አጥንተውና የተሻለው አራተኛው ማለትም ህገመንግስቱን ተርጉሞ የፓርቲ ስልጣን ማስረዘም የተሻለ መሆኑን ሃሳብ ያቀረቡት እነዚሁ የህግ ምሁራን ነበሩ። በፊት በር፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህገመንግስትና ህገመንግስታዊነት ጥርሳቸውን የነቀሉ ብቁ ተመራማሪዎች ያቀረቡት ጥናት ነው በሚል አንቆለጳጰሱዋቸው። እነዚሁኑ ምሁራን በጓሮ በር በኩል ተመልሰው ይኸው ጥናት ምን ያህል ህገመንግስታዊና የተሻለ እንደሆነ የነጻ ሞያተኛ ምስክርነት ሰጡ። ወረረሽኝ ምርጫቸውን እንዲያስተላልፉ ስለተገደዱት አገሮች ሲነግሩን ላለማስተላለፍ ወስነው ኮቪድን እየተከላከሉ ምርጫንም ለማካሄድ የውሰኑ ብዙ አገሮች እንዳሉ ግን አይነግሩንም። እዚሁ ቅርባችን ያለች ማላዊ እንኳን ምርጫዋን ልታራዝም አይደለም ቀድሞ እንዲደረግ ብላ ከነሃሴ ወደ ሃምሌ አመጣችው። እነዚህ የህግ አዋቂዎች ይህንን አይነግሩንም። ብዙ አገሮች ምርጫቸውን አልሰረዙም፣ አላራዘሙም። ያራዘሙትም አብዛኞቹ መጋቢት ወራት ቆይቶ በዚሁ ክረምት እንዲደረግ ነው ቀን የቆረጡት። የኛ ምርጫ ለነሃሴ መጨረሻ ነበር ሊደረግ የታቀደው። የነሃሴ ምርጫ ለማራዘም የወሰነች አገር እስከ አሁን የለችም። የህግ አዋቂዎቹ ስለነዚህ ለምን አልነገሩንም የሚል ጥያቄ ታቀርባለች። ከህግ ምሁሩ የተሰጣት መልስ “ይህ የጤና ባለሙያዎች በሚሰጡት ግምገማ የሚወሰን ነው” የሚል ነው። ይኼ ምክንያታዊ መልስ ይመስላል። ነገር ግን ከመስከረም በኋላ በኮሮና ሰበብ ስልጣን ለማራዘም ሲፈለግ የጤና ባለሙያዎች አስተያየት አልተጠየቁም። መቸም ስልጣን ለማራዘም ግልጽ ድንጋጌና ገደብ በትርጉም ለመቀየር ማሰብ አስገራሚ ድራማ ነው። የትርጉም ጥያቄ ያቀረበው የማይመለከተው የማይገባው የተወካዮች ም ውሸት ትርክት በዝቶና ተደራርቶ መለየት እስኪያስቸግር ሆኗል። እንደቀልድ የተዘሩ ውሸቶች አሁን ጎምርተው ማህበረሰባችንን በክለውታል። በሚድያ መድረኮች ዋናውን የአየር ሰአት በሰፊው የያዙት የውሸት ታሪኮች ናቸው። ይህ ማለት በቤተሰብ ደረጃ ጥዋት በቁርስ ሰዓት የሚወራው ነገር ከውሸት የጸዳ የመሆን አነስተኛ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ራሱ ይጎመዝዛል። የአንደኛ ደረጃ ት
Full Website