Hidar 2012

የኢትዮጵያ ህዝብ የኢህአድግ ስራ አስፈፃሚመግለጫ መስጠት እንደተወ ቢያቅም በአሁኑ ወቅት ግን ጠብቆ ነበር፡፡ መግለጫው ብንጠብቅ ብንጠብቅ ግን እንዳለፈው አሁንም የለም።የስራ አስፈፃሚው ቃል አቀባይናየጠቅላዩ ቢትወደድ ስዩም ተሾመ ቀድሞ ከነገረን ውጭ ምንም የለም። ቅድመ መግለጫና መግለጫ በሹክሹክታ መሆኑን ከቢትወደዱ ተምሬ ሽኩ በሉኝ ብየ ሹክ ያሉኝን እንደተለመደው ሳልቀንስ ሳልጨምር እንዳለ አቀርባለሁ።

እንደ ሽኩ ባዮቼ መረጃ የስራ አስፈፃሚው ስብሰባ ድባብ እንደ ሓምሌ ዝናብ የከበደ ነበር፡፡ ፍተሻው ለጉድ ነበር አሉ፡፡ አዲሱና እየተለመደ የመጣው ከባዱ ፍተሻ ተጠናክራል።እንዲያውም አይ.ሲ.ስ ወይም አልቃይዳ ወይም ጆሃር የውህደቱን ስብስባ ለማጥቃት ሸርቧል የሚል የተረጋገጠ መረጃ የደረሳቸው ይመስል ነበር።በኃላ ከማልቀስ ቀድሞ መጠንቀቅ የሚለው መርሖ ተከትለው ፈተሽዋቸው ከማለት ጎሮጎሩዋቸው ቢባል ሙሉ በሙሉ ባይገልፀውም የተሻለ ይገልፀዋል። ተሰብሳቢዎች ይህንን ሁሉ አልፎው የስብሰባው አደራሽ ደጃፍ ቆመው ስብሰባው እስኪጀመር ሁሉም ሰላምታ ይለዋወጣል። ሲታዘቡዋቸው ሰላምታቸው ግን ጓዳዊ ፍቅርና መነፋፈቅ ያለው ሆኖ አይታይም።ከአንገት በላይናየይስሙላ መሆኑ ያስታውቃል። ስራህን ትተህ የስነልቦና ተማራማሪ ሆንክ እንዴ አልኩት ሹክ የሚለኝን ወዳጄ። ሳቀና አበራራልኝ፡፡ ሳቃቸው የውሸት ንግግራቸው ፌዝ የተሞላበት መሆኑ ማንም ይባንነዋል አለኝ። ይህንን ለመገመት የስነልቦና ሳይንስን መማር አይጠይቅም።ለቁርስ የቀረበ ኩኪስና ውሃ የሚቀምሳቸው አልታየም። አልፈርደባቸውም! ከፈለኩ ልመርዛቹህ እችላለሁ ካለቸው እንዴት ያምኑታል፡፡ በተለይ አሁን የብልፅግና አሃዳዊ ፓርቲ  ሊቀመንበር ከሱ ውጭ ማ ይፈልገዋል ብለው ይመስለኛል ተማምነው መጠጣትና መብላት ሁሉም ትተዋል አሉ፡፡ የአደራሹ አየርም አማራጭ አልቦ ሁኖባቸው ነው ሳይወድ የሚምጉት።ጭራሽ ሰዎቹ ተገዶው እንጂ ወደ ስብሰባው ሳይጠሩ ቢቀሩ ደስተኞችናቸው እየተባለ ነው።

ወደ አጀንዳየ፡፡ የድሮው የኢህአድግ ስራ አስፈፃሚስብሰባው ተጀመረ አሉ። ከዛ የሆነው እንደወረደ ላቅርብላችሁ፡፡ አጀንዳ ማስቀመጥ ላይ ሰፊ ክርክር ተካሄደ።ከስብሰባው በፊት የጀርባ ስብስባ ላይ አጀንዳ ይሁኑ የተባሉትአገር በቀል አጀንዳዎች ብቻ በድምፅብልጫ ፀደቁ።አገር በቀል ያልሆኑትና አጣዳፊ አገራዊ አጀንዳዎች እንዲወድቁ ተደረጉ፡፡ አዲሱ አገር በቀል ዴሞክራሲ ማለት ይህ ነው ተባለ።

የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ነው። አሳሳቢ ደረጃም ላይ ደርሳልና እባካችሁ አደጋው ይታያችሁ እንደ አጀንዳ ይዘንም እንወያይበት ቢባል ሰሚ አልተገኘም፡፡ በዚህ ጉዳይ ዛሬ አንወያይም የሚል ክርክር ተደረገ። ተሰብሳቢዎቹ በሁለት ጎራ ተከፋፍሉ፡፡ በአጅንዳ መያዙ አስፈላጊ ነው የሚሉ እና አሁን አንገብጋቢው ጉዳይ ሌላ ነው በሚሉ ሃሳቦች ቀረቡ።ወደ ድምፅ እንለፍ ተብሎ ታለፈ። የህወሓት ስራ አስፈፃሚ በሙሉ እና እነ ኦቦ ለማ መገርሳ የያዘው አስር (10) የሚሆኑ ተሰብሳቢዎች አጀንዳው ላይ  እንወያይበት ቢሉም ወቅታዊ ሁኔታውን የማያሳስበው ብዙሃኑ የስራ አስፈፃሚ አባል አድሞ እምቢ አለ አሉ፡፡ 86 ሰው ሞተእዚህም እዛም ብጥብጥ አለ ብለን አንጨነቅም ሌላ አጣዳፊ ጉዳይ አለን ተብሎ አጀንዳውን ውድቅ ተደረገ አሉ፡፡ መቸም እዚህ ላይ ይሆናል የተሰብሳቢዎቹ የቁጭት ስሜቶች በፎቶ ያየናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ስብሳባው በቀጥታ የመተላለፉ ጉዳይማ እንዳአማረህ ቀረ እኮ፡፡

ሁለተኛው አጀንዳ፡- አራቱም የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ውስጣዊ ሁኔታቸው ገምግመው መጥተው ስራ አስፈፃሚውይወያይበታል ተብሎ እንደ አጀንዳ ተይዞ የነበረ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ በሃምሌው ስብሰባ ከለውጡና ከጥልቀት ተሃድሶ አንፃር አራቱም ድርጅቶች ውስጣዊ ሁኔታቸው ገምግመው እንዲመጡ በተወነው መሰረት መወያያት አለብን ተብሎ ቀረበ አሉ።ይህም የጀርባ ተሰብሳቢዎቹ መወያየት አልፈለጉም።የኢህአዴግ ፅ/ቤት ኃላፊ እጃቸውን ከፍ በማድረግ ኢንፎርመሽን ላቅርብ ብለው ፍቃድ በጠየቁት መሰረት ተፈቀዳላቸው።ከህወሓት በስተቀር ማንም ድርጅት የተባለውን ግምገማ አላደረገም።ሪፖርትም የህወሓት ብቻ ነው ብእጃችን ያለው ብለው አጀንዳውን ለማስቀረትአሳማኝ ማስረጃእንዳላቸው በኩራት አቀረቡ።ለምን አልገመገሙም? የሚለው ጥያቄ ሳይነሳ ድምፅ ይሰጥ ተብሎ ያልገመገሙት ድርጅቶች በድምፅ በልጫ ውድቅ አድርገውት ቁጭ አሉ።አገር በቀል ዴሞክራሲ ይሉሃል እንደዚህ ነው።

ሦስተኛ አጀንዳ፡- የውህደት አጀንዳ ነው፡፡ ፀደቀ።የውህደት ጥናቱ ባለሙያዎች ያጠኑት ነው ተብሎ ቀረበላቸው። ተሰብሳቢዎችም በመረጃው ፈገግታ በፈገግታሆኑ፡፡ ዝም ግን አላሉም።ከፍተኛ ክርክር አካሄዱ። የህወሓት ስራ አስፈፃሚዎች ጥልቅ የሆነ ንድፈሃሳባዊና ተግባራዊ ሁኔታዎች ከተጨባጭ የአገራችን ሁኔታና የኢህአዴግ ውስጣዊ ሁኔታ እያጣቀሱ አሁን መዋሃዱ ያለውን ጉዳት በተረጋጋ መንፈስ ግን ጠንከር ባለ ሁኔታ አስረዱ።አዴፓና ኦዲፓ ባያዳምጥዋቸውም ቅሉ ሰሚ ግን አላጡም።ውሳኔያቸውን ያስቀይራቸዋል አያሰቀይራቸውም ለጊዜው ማወቅ ባይቻልም አጋር ፓርቲዎች (በስብሰባው ድምፅ የማይሰጡ ቢሆንም)ህወሓት ያቀረበው የክርክር ሐሳብ በትኩረት ነበር የተከታተሉት።

ከአጋር ፓርቲዎቹ ሞስጠፌ ሳይቀር በጥያቄ መልክ ጥርጣሬያቸው ከፍ ያለ መሆኑ ገለፁ።ሹክ እንደተባልኩት አጋር ፓርቲዎቹካነስዋቸው ጥያቄዎች መካካል የሚከተሉት ናቸው፡፡

- 1) ህገ መንግስትና ፌድራል ስርዓቱን የማይነካ መሆኑ ዋስትናችን ምንድን ነው?

2) ውህድ ፓርቲው የራሳችን ክልል ራሳችን ለማስተዳደር ከድሮው በተሻለ የሚያጠናክር መሆን አለበት።በፌደራል መንግስት ደግሞ ተሳትፎችን የሚያጠናክር መሆን አለበት። እንዲያውም አናሳ ክልሎችን በልዩ ሁኔታ ትኩረት የሚሰጥ መሆን አለበት።ይህን የሚያዳክም ከሆነ ውህደቱን አንቀበልም ብለዋል። ሰለዚህ አዲሱ ፓርቲ በህዝብ ብዛት እኛን የሚያገል እንዳይሆን የሚከለክል አሰራር አለው ወይ? 3) ሞስጠፌም አሉ ውህድ ፓርቲው አንድ ነገሩ ላይ ሶማሊ የሚያንፀባርቅ ካልሆነ በክልላችን የሚመርጠን የለም ሲል አብይ በፍርሃት ዘው ብሎ ገብቶ የጀመረው ሐሳብ ሳያስጨረሰው ራሱ ገባበት፡፡ ሶዴፓ እኮ የሶማሊ የብልፅግና ፓርቲ ይሆናል ማለት ነው።አፋር ውስጥ የአፋር ብልፅግና ፓርቲ ይኖራልአለ።በአብይ ቤት ሁሉ ነገር ቀላል ነው። አጋሮች ግን ቀጠሉ ውሁድ ፓርቲ ያስፈልጋል እያላቹሁን ስላለ እንወሃሃዳለን ግን አፈፃፀሙ ላይ አንድ በአንድ ሁሉንም ነገሮች ጥርጣሬያችንን ግምት አስገብተን እንከታተላለን አሉ። እኔ ግን ጥያቄ አለኝ ለአጋር ፓርቲዎቹ።አይረፍድም?

ክርክሩ እነደተፈለገው ተቀቋጨና ወደ ድምፅ አሰጣጥ ተገባና አዲሰ መላ ተገኘ አሉ ከአባ መላ፡፡ ሊቀመንበሩ የተቃውሞ እጆችን ከቆጠሩ በኃላ ድምፃቸውን ያልሰጡትን ሳይቆጥሩ በስድስት ተቃውሞ ብቻ ባብላጫ ድምፅ ፅድቋል ብለው ዘጉት አሉ ውህደቱ። ከህወሓት ስራ አስፈፃሚ በስተቀር አሃዳዊ ፓርትውን እንቀላቀለን የሚል ድምፅ በማግኘት ኦዲፒ አዴፓ ሊከስሙ ወሰኑ።እንግዲህ ሊቀመንበሩ እነዚህ ድምፅ ያልሰጡትን ያልቆጠርዋቸው መቁጠር ደክማቸው ይሆን? ወይስ አለመቃወም በመደመር ፍልስፍና እንደመደገፍ ስለሚቆጠር? ወይስ በድምፅ ተአቅቦ የሚወጡት እጆች ከየትኛው አባል ድርጅት እንደሆኑ እንዳይታወቅ ስለፈለጉ? እንኳን እኔ አብዛኝው የስራ አሰፈፃሚዎችም የሚያውቅት አይመስለኝም፡፡ መገመት ግን ይቻላል፡፡ በዚህኛው ስብሰባ ኦቦ ለማ ምንም አልተናገሩም አሉ። ጭራሹን ድምፃቸውም አልተሰማም።ለምን? የሚለው አሁንም የኔ ጥያቄ ነው። ከስብሰባው በኃላ በነቀምትና በመቐለ ህዝቡ ምን አለ? በሚለው እና ሁላችንም የምናውቀውን እውነታ ላስታውሳችሁ፡፡ ነቀምት ኦነግን በምርጫ ቦርድ መመዝገቡን መሰረት አድርጋ ብዙ ህዝብ የተሳተፉበት ሰለማዊ ሰልፈ አደረገች።የኦነግ አመራሮችን ፎቶግራፍ ይዛ ደስታውን ገለፀች። የነበረው መፈክርደግሞ ዳውን! ዳውን! አብይ ነበር።ስለ ውህድ ፓርቲው ምንም አላለችም። መቐለ ከውህደት ስብሰባው በኃላ ወድያውኑ በማህበራ ሚዲያ አክቲቪስቶችዋአነሳሽነት ህዝቦችዋ ፕሮፋይላቸውን የህወሓት ባንዲራ አደረጉ፡፡ ለጀግኖቻችን ምስጋናችንን በሰላማዊ ሰልፍ በመላው ትግራይ ከጫፍ ጫፍ በመሰለፍ ደስታችንን እንገልፃለን ብለው ዝግጅታቸውን ጀመሩ።

ይህ እንዲህ እንዳለ ፓርቲያቸን አክስመን እንዋሃዳለን ያሉት ፓርቲዎች የውህደት ስብሰባቸውን እሁድም ቀጠሉ።ህወሓቶች ኢህአዴግን አናፈርስም! የህዝብ የሆነ ፓርቲያችንም አናከስምም ብለው ቀና መስመራቸውን እንደጨበጡ መቐለ ተመለሱ። ሊቀመንበር አብይለብቻቹህ ላግኛቹህ ብሎም አግኝቷቸው እንደነበረም ታውቋል፡፡ በቃ ጥላቹሁኝ ጨክናቹህብኝ መሄዳቹህ ነው ብሏቸው ይሆናል። ይህ የኔ ግምት ነው። ለመገመት ለመገመትማ ማን ብሎኝ፡፡
Full Website