Back to Front Page

የዐቢይ አህመድ ዓሊ ከራሽያ ጋር መፈራረም

የሬሳ ሳጥን ለማግኘት ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው

ሙሉጌታ ወልደገብርኤል 7-15-21

መንደርደሪያ፥ “እንዲህም ሆነ፥ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ልጅ በኢዮአታም ልጅ በአካዝ ዘመን የሶርያ ንጉሥ ረአሶን የእስራኤልም ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፥ ሊያሸንፉአትም አልቻሉም። ለዳዊትም ቤት ሶርያ ከኤፍሬም ጋር ተባብረዋል የሚል ወሬ ተነገረ፤ የእርሱም ልብ የሕዝቡም ልብ የዱር ዛፍ በነፋስ እንድትናወጥ ተናወጠ። እግዚአብሔርም ኢሳይያስን አለው አንተና ልጅህ ያሱብ አካዝን ትገናኙት ዘንድ በልብስ አጣቢው እርሻ መንገድ ወዳለው ወደ ላይኛው የኵሬ መስኖ ጫፍ ውጡ፤ እንዲህም በለው ተጠበቅ፥ ዝምም በል፤ ስለ እነዚህ ስለሚጤሱ ስለ ሁለት የእንጨት ጠለሸቶች፥ ስለ ሶርያና ስለ ረአሶን ስለ ሮሜልዩም ልጅ ቍጣ አትፍራ፥ ልብህም አይድከም። ሶርያና ኤፍሬም የሮሜልዩም ልጅ ወደ ይሁዳ እንውጣ እናስጨንቀውም፥ እንስበረውም፥ የጣብኤልንም ልጅ እናንግሥበት ብለው ክፋት ስለ መከሩብህ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ ይህ ምክር አይጸናምና አይሆንም” ይህ የሚለው ያለ መጽሐፍ ነው። እነዚህ የሚጤሱ ሁለት የእንጨት ጠለሸቶች ኢሳይያስ አፈወርቂና ዐቢይ አህመድ ዓሊ እንዲሁም ቢራቢሮዎቹ የአማራ ልሒቃን በር ዘግተው በትግራይ ህዝብ ላይ የዶለቱትና የሸረቡት ክፉ ምክር ዓይናቸው እያየ ጆሮአቸው እየሰማ በነፋስ ፊት እንደተቀመጠ አብቅ ሆኖ በኗል። የወስላቶችና የአመዝሮች አገር ጋለሞታይቱ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ወጪ በማድረግ የገዛቸው የሰው አገር ሠራዊት አስከትላ፥ ትግራይን ሰብራ የትግራይን ህዝብ እያስገበረች ለመኖር የነበራት የበከተ አጼያዊ ህልም ጭራሽ ያላለመችው ያህል ቀልድ ሆኗል። “ሰሜን ዕዝ ተጠቃ” የሚል ሐሰተኛ የፈጠራ ውንጀላ በማውለብለብ፥ ሊያስጨንቁት፣ ሊሰብሩትና ሊያጸዱት የመከሩበት ህዝብ ዛሬ አስጨናቂዎቹን ወደ ማስጨነቅ ተሸጋግሯል ብቻ ሳይሆን ዓለም እጇን በአፍዋ ላይ እስክትጭን ድረስ በራዕሲ አሉላ አባ ነጋ ስም በተሰየመው ኦፕሬሽን በቀናት ውስጥ ሰረግሎቻቸው ሰባብሮ ከህልውና ውጭ እንዲሆኑ በማድረግ ውርደትና ኪሳራ አከናንቧቸዋል።

መጽሐፍ “ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘላለም አታዩአቸውም” እንዲል፤ እግዚአብሔር እስራኤልን ነጻ እንዳወጣና በሰረገሎቹና በፈረሰኞቹም ተማምኖ በእስራኤል ላይ ክፉ ምክር የፈጸመባቸው ፈርዖንና ሠራዊቱ ሥር መሰረቱ ነቆሎ ሬሳው በባህር ዳርቻ ላይ እንደጸፍጸፈው እንዲሁ ከሱዳን ጋር መክረውና ዘክረው ከኢምሬትና ከሶማሊያ የሰው ኃይልና የድሮን እርዳታ ይዘው መጥተው በትግራይ ህዝብ ላይ ወረራ የፈጸሙና ስምንት ወራት እንደ አንዲት ቀን በህጻናት፣ በሴቶችና በሽማግሌዎች ጨምሮ በገጠርና በከተማ በሚኖረው ህዝብ ሁሉ ለሰው አእምሮ የሚከብድ ግፍና በደል የፈጸሙበት፥ የኤርትራ፣ የዐቢይ አህመድ ዓሊ አረመኔያዊ ሠራዊትና የአማራ ኢንተርሃምወይ ሚኒሻና ታጣቂዎች የተገፋው የትግራይ ህዝብ ገፊዎቹ ዳግም ላያያቸው ኃፍረትና ኪሳራ አከናንቦ ከሉዓላዊ ግዛቱ መንግሎ አውጥቶቸዋል። አሁን በዚህ ሰዓት እነዚህ ከትግራይ መሬት ሙትና ሙርከኛ ሆነው በውርደት ተጠራርገው የወጡ የአስመራ፣ የአዲስ አበባና የባህር ዳር ጆቢራዎች ለጊዜውም ቢሆን ሊያደርጓት የሚችሉት አንዲት ነገር ብትኖር ሰዎቹ አስመራ፣ አዲስ አበባና ባህርዳር ተቀምጠው መቀደድ፣ ወሬና አሉባልታ ሰምቶ ለማይጠግብ ህዝባቸው ጥቁር ውሸት ማስኮምኮም ብቻ ነው። ከዚህ ውጪ ለሌላ ለምንም ነገር አይበጁም፤ አቅሙም አይፈቅድላቸውም።  በርግጥ፥ ሰውዬው ከዕለት ወደ ዕለት እየባሰበት መምጣቱ እየተነገረ ያለ የአእምሮ ጭንቀት ተከትሎ እንቅልፍ በማጣት እየተሰቃየ እንደሆነ ታውቋል። በመሆኑም፥ የገጠመው የአእምሮ በሽታ ከመስመር አስወጥቶ ቢሞክሯት እንኳ ሊደርስበት የሚችል ኪሳራ ቀድሞ ከደረሰበት ስብራትና ውርደት የከፋ ነው ሊሆን የሚችለው።

መስኮ ለዐቢይ አህመድ ዓሊ ልታበረክትለት የምትችለው ስጦታ የሬሳ ሳጥን ብቻ ነው

የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር ዐቢይ አህመድ ዓሊ መቀበርያው ጉድጓድ ከቆፈረ ሰነበብቷል። የባልቴት ጭብጨባና ጩኸት ያሰከረው ዐቢይ አህመድ ዓሊ የመጣበት መንገድ በጸሐይ ፍጥነት ረስቶ እዚህም እዚያም ሲረግጥ የከረመ ሰው ከመሆኑ በላይ የሰለጠነበት ክፉ የእብሪት መንፈስ ክፉኛ ጸንቶበትና አድጎበት ለዓይኑ ያማረውና የወደደውን ሁሉ ያለ አንዳች ከልካይ ማድረግ እንደሚችል ማመኑ ሳያንስ ዓለም ዓይኑን ይጨፍን፣ እኔን የመጠየቅ መብትና ስልጣን ያለው ማንም የለም! በሚል የተያያዘው የጥፋት ጎዳና እንግዳ የሆነባት አሜሪካ፥ አንተ ሰው እየሳትክ ነው፣ አካሄድህ ትክክል አይደለም፣ ተመለስ፥ በማለት በቀጥታም በተዘዋዋሪም ምክሯን ብለግስለትም አሻፈረኝ በማለት የተያያዘው የሞትና የጥፋት መንገድ ጭራሽ አሜሪካን ያበሸቀ መስሎት አዲስ አበባ የሚገኘው የራሽያ ኢምበሲ ደጅ በመጽናት ወደ ራሽያ እስከ መጣራት አድርሶታል።

ቅሌታም ተቀብለው የበየለት ተቅበዝባዥ በማድረግ የተዋጣላቸው ራሻዎች ክፋት ጥርሳቸው የነቀሉበት ሞያ ነውና ኢትዮጵያ በተለይ በአሁን ሰዓት ከግብጽና ከምዕራቡ ዓለም ጋር ያላት የላላ ግኙንነት ፈጽሞ ለመበጠስና ሳይቸግረው በራቸው ያንኳኳ ጀርጀራ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ለማስመታት ታስቦ ባጫ ደበሌ ፋናና ኢቲቪ ላይ የለመደው መከፈት ሰፊ ተደራሽነት ባለው የአርቲ የቴሌቪዥን ጣቢያ (RT) እንዲደግመው በማድረግ፣ ዜናው በሚገባ በማራገብ፣ ሰዎቹ የተካኑበት አገርና ህዝብ ባሪያ አድርጎ የመመዝበር ሴራ እውን እያደረጉት እየተመለከትን ነው። ይህ የዐቢይ አህመድ ዓሊ መንገድ ታድያ እንግዳ ግኝት ሳይሆን ብዙዎች የሄዱበትና ጠፍተው የቀሩበት የውርደትና የኪሳራ መንገድ መሆኑን ታሪክ ይመሰክርልናል። የሱዳኑ አልበሽር ጉልበት በተሰማው ዘመን ከምዕራቡ ዓለም ጋር መሳፈጥ ሲጀምር ሩቅ ሳይሄድ ሁለመናው ሲያሽመደምዱት መሄጃ ከማጣቱ የተነሳ ወደ ራሽያ ፊቱ ማዞሩን እናስታውሳለን። በነገራችን ላይ፥ የዐቢይ አህመድ ዓሊና የኢትዮጵያ ዓይነቱ አምባገነን መንግስትና የበከቱ አገራት ከምዕራቡ ዓለም በተለይ ከአሜሪካ ጋር ተጣልተው የራሽያ በር ከማንኳኳታቸው በፊት የጨዋታው ህግ ማወቅ ይጠበቅባቸዋል። ምነው? ቢሉ ራሽያ በባዶ እጁ በርዋን የሚያንኳኳባት ለማኝና ተመጽዋች አምባገነን መንግሥትና አገር አትወድምና። የሱዳን ገጸ በረከት ምን ነበር? ያሉ እንደሆነ ታድያ፥ ፖርት ሱዳን እንዲሁ ያለ ክፍያ ለራሽያ መንግሥት ማስረከብ ነበር። የሚገርመው ግን፥ ሱዳናውያን አልበሽርን ገፍትረው ከጣሉና ከአሜሪካ ጋር ያላቸው ግኙንነት ካስተካከሉ በኋላ ለራሽያ ጭምር አናውቅልሽም አገራችን ለቀሽ ውጪ ማለታቸው ነው።

v ራሽያ፥ ምንም እንኳ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ በማምረትና በመሸጥ የምትታወቅ አገር ብትሆንም አገሪቱ እንደ ኢትዮጵያ ካሉ የሦስተኛ ዓለም ድሃ አገራት ጋር ያላት የግኙንነት ባህሪይ እኩልነት ላይ መሰረት ያደረገ አጋርነት ሳይሆን ከሌባ ተቀባይ ሌባ የሚለው አባባል በሚገባ ይገልጸዋል።

v ራሽያ፥ አሁንም በወታደራዊ ሃርድ-ዌር የማትታማ፣ ለጥቆም አገሪቱ የኒክለር ባለቤት ብትሆንም የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ላይ ጥግተኛ የሆነ ኢኮኖሚ ያላት አገር በመሆንዋ ከራስዋ አልፋ ለሌሎች አገራትና መንግስታት የምትበቃ፣ ሌሎች ከድህነት ለማውጣት የሚያስችል አቅም ያላት፣ መሰረታዊ የልማት ተቋማት በመገንባት ወይንም የፋይናንስ እርዳታ በመስጠትና በማድረግ የምትታወቅ አገር ሳትሆን ይልቁንም ከአሜሪካና ከቻይና የተራረፉ አምባገነን መንግስታትና አገራት እየቃረመች የአገራቱ ተፈጥሯዊ ሀብት በሚገርም መንገድ የምትዘርፍና ክፉ ቀንን በሚገባ መጠቀም የምታውቅበት አገር ናት።

v ራሽያ፥ ከድሃ አገራትና አምባገነን መንግስታት ጋር ያላት ልዩ መስተላጽቅ (መስተዋድድ) ሌላኛው ገጽታው የተመለከትን እንደሆነም አብዛኞቹ ከምዕራባውያን ጋር ያኮረፉ አገራትና መንግስታት ሆነው እናገኛቸዋለን። ራሽያ እንደዚህ ዓይነቱ አጋጣሚ እስከ ጥግ ድረስ በመውሰድ ለራስዋ ጥቅም በማዋል የተካነች አገር ስትሆን የብዙዎች አገራት ዕጣ ፈንታ በማበላሸትና በማኮላሸትም የሚስተካከላት የለም።

v ቀደም ሲል እንደተገለጸው ከምዕራባውያን ጋር ተኳርፎና ተጣልቶ ደጅዋ የሚያንኳኳ ማንኛውም አገርና መንግስት ራሽያ የምትፈልገው ነገር ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታና ማቅማማት መስጠትና መስዋዕት ለማድረግ ዝግጅዎች ከሆኑ ማንንም የማትገፋ የአረጣ ፖለቲካ አበዳሪ አገርም ናት። የምትፈልገው ነገር ሲጓደልባት በአንጻሩ ጣፋጭነቱ እንዳለቀ መስቲካ አውላላ ሜዳ ላይ አውጥታ ለመጣል አያቅጣትም። ይህን ሐቅ ለማወቅና ለምረዳት ታሪክ ማገላበጥ እንጅ ዙምባቤ ድረስ በመሄድ ኮረኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም መጠየቅ አይጠበቅብንም። ቀለል ባለ አማርኛ ‘የጨነቀው እርጉዝ ያገባል’ እንደሚባለው፥ የዐቢይ አህመድ ዓሊ ዓይነቱ ተስፋ ያጣና የሌለው፣ ተስፋው የጨላለመባቸው አምባገነን መንግስታት በራሳቸው ጊዜ በሚፈጥሩት ችግር ውስጥ ተዘፍቀው ሲሰቃዩና ከገቡበት ጨለማ ለመውጣት አቅጧቸው የሚዙት የሚጨብጡት ሲያጡ የሚያቀጥኑት ወደ ራሽያ ነው። በድናቸው የሚቀበርበት የሬሳ ሳጥን ለማግኘት የሚፈራረሙት ከራሽያ ጋር ነው።

መንግስቱ ኃይለማያርም ሽንፈቱን ለመሸፈን ‘የጥሞና ጊዜ’ ማወጁን ያውቁ ኖሯል?

እ.አ.አ ግንቦት 5 ቀን 2011 ዓ/ም የአሜሪካ ግዙፉ የደህንነት ተቋም ምስጢራዊነቱ አብቅቶ ግላጭ ያደረገው የቆየ ሰነድ እንደሚያመላክተው የዛሬይቱ ራሽያ ሶቬት ህብረት በኤርትራ የነበረ አየር ማረፊያና የባህር በር በቁጥጥሯ ሥር ለማዋል ከነበራት ጽኑ ፍላጎት የተነሳ ኢትዮጵያ ከምዕራቡ ዓለም ሙሉ በሙሉ በመነጠል በተለይ በወቅቱ የአገሪቱ የፖለቲካ መንበረ ስልጣን ተቆናጦ የነበረ ጸረ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች የሆነ በሊቀ መንበር ኮረኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም ይመራ የነበረ ወታደራዊ መንግስት ለመገርሰስ ይካሄድ የነበረ የነጻነት ትግል ፈጽሞ እንዲከስም ለወታደራዊ መንግስቱ ከፍተኛ የጦር አማካሪዎች በመስጠትና እስከ አፍንጫው ድረስ በማስታጠቅ ቀንደኛ የስርዓቱ ደጋፊ እንደነበረች፤ ደርግ፥ በትግራይ ይንቀሳቀስ የነበረ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ እንዲሁም በኤርትራ አከባቢ የነበረ ህዝባዊ ግንባር ለመደምሰስ ያካሄዳቸው ኦፕሬሽኖች ጦር ሠራዊቱ ድጋሜ ሊያንሰራራ በማይችልበት ሁኔታ ከፍተኛ የሆነ የህይወትና የንብረት ውድመት ማስተናገዱን ተከትሎ ልክ ዛሬ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ኦፕሬሽን ራእሲ አሉላ አባ ነጋ ተከትሎ የደረሰበት ለማመን የሚከብድ ወታደራዊ ሽንፈትና ኪሳራ ለመደበቅና ለማገገም “የጥሞና ጊዜ” ሲል እንደሚለፍፈው እንዲሁ የሶቬት የምድር ጦር አዛዥ ጀኔራል ፔትሮቭ ጨምሮ የመንግስቱ ኃይለማሪያም የጦር አማካሪዎች በመሆን ይሰሩ የነበሩ የሶቬት ወታደራዊ መኮንኖች፥ በዋናነት በሠራዊቱ ውስጥ ያለው የሞራል ውድቀት/ድንጋጤ፣ በስልጠናና በታክቲክ እንዲሁም በአመራር ላይ የታየው ግልጽና ከፍተኛ የሆነ ጉድለቶች ለማረምና ለማስተካከል መንግስቱ ኃይለማሪያም በአስቸኳይ ጊዜያዊ የተኩስ ማቆም ወይም የጥሞና ጊዜ እንዲያደርግና በአስቸኳይ ሠራዊቱን ድጋሜ የማደራጀት ፕሮጀክት እንዲጀመር በጥብቅ መምክራቸው ቃል በቃል ያስነብባል። የዐቢይ አህመድ ዓሊ ሠራዊት አፈ ቀላጤ ጌትነት አዳነ ኦፕሬሽን አሉላ አባ ነጋ ተከትሎ የኢትዮጵያ መከላከያ የት ገባ? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፥ መከላከያ ሠራዊት እንደገና እያደራጀን ነው ማለታቸው ልብ ይሏል።

ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከሠላሳ ምናምን ዓመታት በኋላ ቁርጥ ያለ ተመሳሳይ ምክር ሊለግስለት የሚችል ማን ሊሆን እንደሚችል ታድያ አስበውበት ያውቃሉ? ሊሆን የሚችለው አንድም፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ዛሬም በከፍተኛ ወጪ የቀጠራቸው የራሽያ የጦር አማካሪዎቹ ናቸው አልያም፥ ትናንት የዚህ ነፍሰ ገዳይ የደርግ ሠራዊት አባላት የነበሩና ለብሔር አስተዋጽዖ ሲባል ከሙርከኝነት ወደ ጄነራልነት የመጡ ትንግርተኞች ሊሆን እንደሚችል አምናለሁ። ከነተረቱ፥ ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ ይባልየለ። ሌላው ከዚህ ጋር በተያያዘ፥ ትግራይ በኢሳይያስ አፈወርቂና በዐቢይ አህመድ ዓሊ ሠራዊት ላይ እንዲሁም በአማራ ኢንተርሃምወይ ሚኒሻና ታጣዊ ያስመዘግበችውና እያስመዘገበችው ያለ ድል ምስጢር ነው። ይኸውም፥ ከሦስትና ከዚያ በላይ ክፍለ ጦሮች የሚያሳትፍ ግንባር በዋናነት መመራት የሚገባውና ያለበት በብርጋዴልና ከዚያ በላይ ማዕረግ ያላቸው ጄኔራሎች ቢሆንም ለብሔር አስተዋጽዖ ሲባል ከአስራ አለቃ ወደ ጄኔራልነት በደብዳቤ የተሾሙ የኢትዮጵያ የሠራዊት አለቆች የቀድሞ ጌቶቻቸው ወታደራዊ አቅምና ብቃት ጠንቅቀው ስለማያውቁ ሰዎቹ ወደ ግንባር ሊወርዱ ቀርቶ ጦርነት በሚካሄድበት ወቅት ጭራሽ ወደ ትግራይ መሬት ድርሽ አይሏትም፤ ነገሩ የሚያልቀው አስመራና አዲስ አበባ ሆነው በሚሰጡት የስልክ ትዕዛዝ ነው። ከክፍለ ጦርና ከዚያ በታች የሚገኙ ኮረኔሎችና ሌሎች በየተዋረዱ የተሰገሰጉ መኮነኖችም በተመሳሳይ በትግራይ በኩል ጦርነቱን እየመሩ ያሉ ተጋሩ የጦር መሪዎች እነማን መሆናቸው አሳምረው ስለሚያውቁ የተጠጉ እንደሆነ ዕድለኞች ከሆኑ ቆስለውም ቢሆን በምርኮ ገቢ እንደሚሆኑ ካልሆነ ደግሞ ትግራይ መቀበሪያቸው እንደምትሆን ደህና አድርገው ስለሚያውቁ ወደ ግንባር ድርሽ አይሏትም፤ እነሱም እንደ አልቆቻቸው “ከወያነ ጋር ጦርነት በሩቁ ነው” እያሉ በአሥር ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ሆነው በሬድዮ በሚሰጡት ትዕዛዝ ድሃውን ግባ በለው እያሉ ስለሚያስበሉት ነው። እንደዚያም ሆኖ የክፍለ ጦር አዛዦችና መሪዎች ጭምር ከሞትና ከሙርኮ አላመለጡም።

Full Website